Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የዘርና የማዕረግ ልዩነት የለም

    ክርስቶስ በዘር፣ በማዕረግና በደረጃ ልዩነት አላደረገም፡፡ ጸሐፎችና ፈሪሣውያን በዓለም ያሉትን የእግዚአብሔር ቤተሰቦች በማግለል በሰማያዊ ስጦታ የአገር የወገን ጥቅም ለማግኘት ይፈልጉ ነበር፡፡ ክርስቶስ ግን የመለያውን ግድግዳ ሁሉ ሊያፈራርስ መጣ፡፡CLAmh 128.5

    ምሕረቱ እንደ አየር፤ ብርሃና ዝናብ አገር የማይለይ መሆኑን ሊያሳይ መጣ፡፡CLAmh 128.6

    የክርስቶስ ሕይወት አሕዛብና አይሁድ የማይለይ ያንድነት ሃይማኖት ቆረቆረ (አቋቋመ)፡፡ ሁሉም በወንድማማችነት በእግዚአብሔር ፊት እኩል ነው፡፡ ሥራው የሰዎች ወግና ልማድ ተጽዕኖ አልነበረበትም፡፡CLAmh 128.7

    በጎረቤትና በእንግዳ፤ በጠላትና በወዳጅ መካከል ልዩነት አላሳየም፡፡ እርሱን የሚያስደስተው የሕይወትን ውኃ የተጠማ ነፍስ ነበር፡፡CLAmh 128.8

    ማንንም ሰው ንቆ ሳያልፍ ነፍሳትን ሁሉ በምሕረቱ ሊያድናቸው ፈለገ፡፡ በማንኛውም ቦታ ቢሆን ለሁሉ ገጣሚና ተገቢ የሆነ ትምህርት ያስተምር ነበር፡፤ ሰዎች ጓደኞቻቸውን ሲንቁና ሲሰድቡ ሲያይ እነዚያ ግብዝ ሰዎች መለኮታዊ እርዳታውን በበለጠ እንደሚሹ ይገባዋል፡፡ ነውር የሌለበት ኑሮ በመኖር ክፉዎችንና በጣም የተበላሹትን በአምላክ ፊት የቀኑ ሆነው እንዲገኙ ይገፋፋቸዋል፡፡ በሰይጣን ወጥመድ የተያዙትንና ከእርሱ ክንድ ማምለጥ ያቃታቸውን ብዙ ጊዜ ያገኛቸው ነበር፡፡ ተስፋ ለቆረጠው፣ ለታመመው፣ ፈተና ላጠቃውና ለወደቀው የሱስ በሚያጽናና በሚያበረታታ ቃል ይናገረዋል፡፡ አንዳንዶችም ከነፍስ ጠላት ጋር የጨበጣ ጦርነት ሲዋጉ ያገኛቸው ነበር፡፡ እንደሚያሸንፉ በማረጋገጥ እንዲበረቱ ይነግራቸው ነበር፡፡ መላእክት በአጠገባቸው ስለተሰለፉ ድል የእነርሱ መሆኑ እንደማይቀር አስገነዘባቸው፡፡CLAmh 129.1

    በቀራጮች ድግስ ላይ የክብር እንግዳ ሆኖ ተገኘ፡፡ የሰውን ክብር መገንዘቡንም አሳየ፡፡CLAmh 129.2

    ሰዎችም ለእርሱ ታማኝነታቸውን ለማሳየት ይፈልጉ ነበር፡፡ ቃላቱ ለተጠማው ልባቸው በረከትንና ኃይልን ይሰጡ ነበር፡፡ አዲስ ኃይል አገኙ፤ የተናቁት ሁሉ አዲስ ሕይወት አገኙ፡፡CLAmh 129.3

    የሱስ አይሁዳዊ ቢሆንም የወገኖቹ የፈሪሣውያን ልማድ ከቁም ነገር ሳይቆጥር ከሳምራውያን ጋር አብሮ ይውል ነበር፡፡ የእነርሱን አጉል ልማድ ችላ ብሎ የተናቁት ሰዎች ሲጋብዙት ይሄድ ነበር፡፡ ከማዕዳቸው ይበላ ነበር፡፡ ያዘጋጁትን ምግብ ይመገብ ነበር፡፡ ያስተምራቸውና በርኅራኄ ያክማቸው ነበር፡፡CLAmh 129.4

    በሰብአዊ ርኅራኄ ልባቸውን ከልቡ ጋር ሲያስተሳስር መለኮታዊ ጸጋው አይሁዶች ችላ ያሉትን መዳን እስገኘላቸው፡፡CLAmh 129.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents