Go to full page →

የመወያያ ጥያቄዎች ክየመ 20

1. ኃጢያት ወደዚች ዓለም ከመግባቱ በፊት ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር በደስታ የተሞላና ፊት ለፊት የሆነ ህብረት ነበራቸው፡፡ በዚህ ግንኙነት ላይና በሰዎች ተፈጥሮ ላይ ኃጢያት ያስከለተው ለውጥ ምንድን ነው?
2. ልባቸው በእግዚብሔር ፍቅር ላልታደሰ ሰዎች ሰማይ የስቃይና ደስታ የሌለበት ስፍራ ይሆን የነበረው ለምንድን ነው? “ከላይ የተወለዱ» እንደሆኑ እንዴት ማወቅ ይችላሉ? ሕዝ 36:25-26 ን ያንብቡ፡፡
3. እግዚአብሔር የጠፉ ልጆቹን እንደገና የራሱ ለማድረግ ያደረገውን ታላቅ ጥረትና ያፈሰሰውን ጉልበት ቤተሰቦችዎ እንዲሁም የቅርብ ወዳጆችዎ እንዲረዱትና እንዲያመሰግኑት ለማድረግ በምን አይነት መንገድ ይረዷቸዋል? ክየመ 20.3