Go to full page →

“ኑ…ዕረፉ” CLAmh 144

የሱስ የመከሩን ስፋትና የሠራተኞችን ማነስ ለደቀመዛሙርቱ ሲነግራቸው ያለዕረፍት እንዲሠሩ አላስገደዳቸውም፡፡ “የመከሩ ጌታ ሠራተኞችን እንዲልክ ጸልዩ” አላቸው፡፡ (ማቴዎስ 9፡38) ፡፡ CLAmh 144.3

ያን ጊዜ ለነበሩት ደቀመዛሙርት ያዘነላቸውን ያህል ለዘመኑ ሠራተኞችም “ኑ ለብቻ ሆናችሁ ዕረፉ፡፡” ይላቸዋል፡፡ እግዚአብሔርን በጸሎት አማካይነት መገናኘት ያሻቸዋል፡፡ በኑሮአቸው ከዓለም ጋር አንድ ያልሆነ ጠባይ ለማሳየት የእግዚአብሔርን ፈቃድ በሚገባ ማወቅ አለባቸው፡፡ ለየግል ልባችን ሲናገረን ማዳመጥ መቻል ይገባናል፡፡ አካባቢው ጸጥ ሲል፤ በጸጥታ እርሱን እንጠባበቃለን፡፡ በሰውነታችን ውስጥ ጸጥታ ስናገኝ የእግዚአብሔር ድምጽ ጎልቶ ይሰማናል፡፡ CLAmh 144.4

“ዕረፉ እኔም አምላክ እንደሆንሁ ዕወቁ” ይለናል፡፡ (መዝሙር 46፡10) CLAmh 144.5

የእርሱ ሠራተኞች ለሆኑት ሁሉ ይህ ዓይነት ዝግጅት ያስፈልጋቸዋል፡፡ በሕዝብ ትርምስ መካከል በኑሮ ውዝግብ ሲጣደፍ የኖረ ሰው ዕረፍት ሲያገኝ ብርሃንና ሰላም ይከበዋል፡፡ የአእምሮና የአካል ብርታት ይሰማዋል፡፡ ሕይወቱ መልካም መዓዛ ይሆናል፡፡ በእርሱ አማካይነት የመለኮት ኃይል ተገልጦ የሰዎችን ልብ ይነካል፡፡ CLAmh 144.6