Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    “ኑ…ዕረፉ”

    የሱስ የመከሩን ስፋትና የሠራተኞችን ማነስ ለደቀመዛሙርቱ ሲነግራቸው ያለዕረፍት እንዲሠሩ አላስገደዳቸውም፡፡ “የመከሩ ጌታ ሠራተኞችን እንዲልክ ጸልዩ” አላቸው፡፡ (ማቴዎስ 9፡38) ፡፡CLAmh 144.3

    ያን ጊዜ ለነበሩት ደቀመዛሙርት ያዘነላቸውን ያህል ለዘመኑ ሠራተኞችም “ኑ ለብቻ ሆናችሁ ዕረፉ፡፡” ይላቸዋል፡፡ እግዚአብሔርን በጸሎት አማካይነት መገናኘት ያሻቸዋል፡፡ በኑሮአቸው ከዓለም ጋር አንድ ያልሆነ ጠባይ ለማሳየት የእግዚአብሔርን ፈቃድ በሚገባ ማወቅ አለባቸው፡፡ ለየግል ልባችን ሲናገረን ማዳመጥ መቻል ይገባናል፡፡ አካባቢው ጸጥ ሲል፤ በጸጥታ እርሱን እንጠባበቃለን፡፡ በሰውነታችን ውስጥ ጸጥታ ስናገኝ የእግዚአብሔር ድምጽ ጎልቶ ይሰማናል፡፡CLAmh 144.4

    “ዕረፉ እኔም አምላክ እንደሆንሁ ዕወቁ” ይለናል፡፡ (መዝሙር 46፡10)CLAmh 144.5

    የእርሱ ሠራተኞች ለሆኑት ሁሉ ይህ ዓይነት ዝግጅት ያስፈልጋቸዋል፡፡ በሕዝብ ትርምስ መካከል በኑሮ ውዝግብ ሲጣደፍ የኖረ ሰው ዕረፍት ሲያገኝ ብርሃንና ሰላም ይከበዋል፡፡ የአእምሮና የአካል ብርታት ይሰማዋል፡፡ ሕይወቱ መልካም መዓዛ ይሆናል፡፡ በእርሱ አማካይነት የመለኮት ኃይል ተገልጦ የሰዎችን ልብ ይነካል፡፡CLAmh 144.6

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents