Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ወደ ዴቃጶሊዮስ የተላኩ የመጀምሪያዎቹ የወንጌል መልዕክተኞች

    ከበሸታ የዳኑት ዴቃጶሊዮሳውያን ክርስቶስ ወደ ዴቃጶሊዮስ የላካቸው የመጀመሪያዎቹ የወንጌል መልዕክተኞች ነበሩ፡፡ እነዚህ ሰዎች የሱስ ሲናገር የሰሙት ለአጭር ጊዜ ብቻ ነበር፡፡ ለሕዝብ በጉባኤ ሲያስተምር አንድም ጊዜ አልሰሙትም ነበር፡፡ በየዕለቱ ከየሱስ ጋር ይኖሩ እንደነበሩት ደቀመዛሙርት አድርገው ማስተማር አይችሉም ይሆናል፡፡ ግን ያዩትን፤የሰሙትን በራሳቸው ላይ የተገለጠውን የክርስቶስን ኃይል ለሰዎች መናገር አያቅታቸውም፡፡ ልቡ በእግዚአብሔር ጸጋ ከተነካ ማንም ሰው ይህንን ማድረግ ይችላል፡፡ በዓለም ስለ ሌለ ለዓለም ጥፋት ምክንያት የሚሆነውና ጌታችን እንድንመሰከር የሚጠበቅብን ምስክርነት ይህ ነው፡፡CLAmh 165.4

    ወንጌል ሕይወትን የሚለውጥ ኃይል ሆኖ መታየት እንጂ እንደ ጥቅመ ቢስ አፈ ታሪክ መቈጠር የለበትም፡፡ እግዚአብሔር ከአገልጋዮቹ የሚጠባበቀው ሰዎች በእግዚአብሔር ጸጋ የክርስቶስን አኗኗር መኖር እንደሚችሉና በታላቁ ፍቅሩ እንደሚደሰቱ ለሌሎች እንዲመሰክሩ ነው፡፡CLAmh 166.1

    ማንኛውም ሰው የተቀደሰውን መብቱን ተገንዝቦ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን እስከሚያውቅ ድረስ እንድንመሰክር ይጠብቅብናል፡፡ እግዚአብሔር የከፋ ስራ ሲሰራ የኖረ ሰው ከተመለሰ ይቀበለዋል፡፡ ሲናዘዙ መለኮታዊ እርዳታ ይሰጣቸዋል፡፡ ምህረቱን እንዲሹ ጉድለታቸውን ያስገነዝባቸዋል፡፡ የሠይጣን መሣሪያ ሆነው የኖሩ ሰዎች በክርስቶስ ኃይል አማካይነት የጽድቅ መልዕክተኞች በመሆን እግዚአብሔር ታላላቅ ነገሮች እንደፈጸመላቸውና እንደራራላቸው ይናገራሉ፡፡CLAmh 166.2

    ያቺ የቅፍርናሆም ሴት የልበሱን ዘርፍ በመንካት ብቻ ከበሽታዋ በተፈወሰች ጊዜ ክርስቶስ ያገኘችውን በረከት እንድታስተውል ፈልጎ ነበር፡፡ በወንጌል አማካይነት የተገኙት ስጦታዎች ሚስጥር ሆነው መቀመጥ የለባቸውም፡፡ “ስለዚህ እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ እኔ አምላክ ነኝ” (ኢሳያስ 43፡12)CLAmh 166.3

    ታማኝነታችን መመስከር እግዚአብሔር የመረጠልን ታላቅ ወኪልነት ነው፡፡ የጥንት ቅዱሳን ሰዎች የገለጡልንን ጸጋውን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ከሁሉ የበለጠው ግን የየግል ምስክርነታችን ነው፡፡ የአንዱ ኑሮ ከሌላው ፈጽሞ የተለየ ነው ስለዚህ በህይወት የሚያጋጥመው አጋጣሚ አይምሳሰልም፡፡ እግዚአብሔር የየግል ምስጋናችንን ስናቀርብ ይደሰታል፡፡ ከእውነተኛ የክርስትና ኑሮ ጋር የተጣመረ የዚሀ አይነት ምስጋና ነፍሳትን ለመመለስ ዋና መሳሪያ ነው፡፡CLAmh 166.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents