Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የእናቶች ረዳት

    ክርስቶስ ዛሬም በምድር ላይ በነበረበት ጊዜ እንደነበረው አዛኝ መድኃኒት ነው፡፡ በይሁዳ ሕፃናትን ያቅፍ እንደነበር ዛሬም የወላጆች (የእናቶች) ረዳት ነው፡፡ የዘመኑ ልጆች ያን ጊዜ እንደነበሩት ልጆች በደሙ ተገዝተዋል፡፡CLAmh 136.3

    የሱስ የእያዳንዱን እናት ችግር ያውቃል፡፡ እናቱ በድኅነትና በችግር ታግላ ስላሳደገችው የእናትን ጭንቀት አይረሳውም፡፡ የከነዓንን ሴት ጭንቀት ለማቃለል ረዥም መንገድ መጓዙ የእናቶችን ጭንቀት በማስተዋሉ ነው፡፡ ለናይን ሴት አንድ ልጅዋን ከሞት ያስመለሰ፤ በጭንቅ ላይ ሆኖ እናቱን ያልረሳ፤ ዛሬም የእናት ሀዘን ምን መሆኑን ያውቃል፡፡CLAmh 136.4

    ያዘኑትን ያጽናናል፤ የተቸገሩትን ይረዳል፡፡ እናቶች ችግራቸውን ለየሱስ ያቅርቡ፡፡ በልጅ አስተዳደግ በኩል ለሚገጥማቸው ችግር ሁሉ መፍትሄ ያገኛሉ፡፡ ችግሯን በመድኅን እግር ለመጣል ለምትፈልግ እናት ሁሉ መንገዱ (በሩ) ክፍት ነው፡፡ “ተዉ ልጆችን አትከልክሏቸው ወደ እኔ ይምጡ” ያለው ጌታ ዛሬም እናቶች ልጆቻቸውን ወደ እርሱ አቅርበው እንዲያስባርኩ ይጋብዛቸዋል፡፡CLAmh 136.5

    ክርስቶስ ወደ እርሱ የቀረቡት ልጆ ሲያድጉ በጸጋው የመንግሥቱ ተካፋይ እንደሚሆኑ፤ አንዳንዶቹም ስለ እርሱ ሰማዕታት እንደሚሆኑ የወደፊቱ ታየው፡፡ አዋቂዎች ነን ከሚሉት ምሁራን ይልቅ እነዚያ ሕፃናት አዳኝነቱን አምነው እንደሚቀበሉት አወቀ፡፡ ሲያስተምራቸው እንዲገባቸው አድርጎ አብራርቶ ገለጠላቸው፡፡CLAmh 137.1

    የሰማይ ግርማ ሞገስ የሆነው የሱስ ትልቁን ቁም ነገር ለሕፃናት አእምሮ በሚስተዋል ቀላል አገላለጽ ገለጠላቸው፡፡ ከጊዜ በኋላ አድጎ የዘለዓለም ፍሬ የሚያፈራውን መልካም ዘር በአእምሯቸው ዘራው፡፡CLAmh 137.2

    ክርስቶስ ደቀመዛሙርቱን ሕፃናትን ወደ እርሱ ከመምጣት እንዳይከለክሏቸው ሲያዝ በዘመኑ ሁሉ ለሚኖሩት ተከታዮቹ ማስጠንቀቁ ነበር፡፡ የቤተክርስቲያንን ሹማምንት ቀሳውስትን፣ዲያቆናትን፣ ክርስቲያናትንም ያጠቃልላል፡፡CLAmh 137.3

    የሱስ ሕፃናትን ያቀርባል፡፡ “አትከልክሏቸው” ይለናል፡፡ በሌላ አነጋገር ካልከለከሏቸው ወደ እኔ ይመጣሉ ማለቱ ነው፡፡CLAmh 137.4

    ከክርስትና መንገድ የወጣው ጠባያችሁ የክርስቶስን ማንነት አያጥፋባችው፡፡ በግዴለሽነታችሁና በጫካኔአችሁ ህፃናትን ከእርሱ አታርቋቸው፡፡ የእናንተ በሰማይ መገኘት የሰማይ ደስታቸውን የሚቀንስባቸው መስሎ አይሰማቸው፡፡ ሃይማኖትን ልጆች የማያስተውሉት ሚስጥር አስመስላችሁ አትናገሩ፡፡ በተግባራችሁም ህፃናት በልጅነት ወራታቸው የሱስን መቀበል የማያስፈልጋቸው አታስመስሉ፡፡ የክርስቶስን ሃይማኖት የትካዜ ኑሮ በማስመሰል ልጆች የክርስቶስ ተከታዮች ለመሆን የልጅነት ደስታቸውን ማጨለም የሚያስፈልጋቸው አስመስላችሁ አትናገሩ፡፡CLAmh 137.5

    መንፈስ ቅዱስ የወጣቶችን ልብ ሲያነሳሳ በሥራው ተባበሩ፡፡ ጌታ እየጠራቸው መሆኑን አረጋግጡላቸው፡፡ ወጣቶች በአበባ ጊዜያቸው ልባቸውን ለጌታ ሲሰጡ ከማየት የበለጠ ሌላ ነገር ክርስቶስን አያስደስተውም፡፡CLAmh 137.6

    ክርስቶስ በደሙ የገዛቸውን ነፍሳት በበጎ ዓይን ይመለከታቸዋል፡፡ የፍቅሩ ፍሬዎች ናቸው፡፡ በከፍተኛ ናፍቆትና ጉጉት ይመለከታቸዋል፡፡ በጥሩ አስተዳደግ አድገው ጨዋ የሆኑትን ልጆች ብቻ ሳይሆን እንደአጋጣሚ በዘርም ሆነ በአስተዳደግ ተበድለው መጥፎ ዐመል ያላቸውን ልጆችም ይወዳል፡፡CLAmh 137.7

    ብዙ ወላጆች የልጆቻቸው ጠባይ በመበላሸቱ በኃላፊነት የሚጠየቁ መሆናቸውን ይዘነጉታል፡፡ ዐመላቸው እንዲዛባ ካደረጉ በኋላ የተጣመመውን ጠባያቸውን ለማረቅና ለማቃናት ጥበብና ትዕግሥት ይጎድላቸዋል፡፡ የሱስ ግን እነዚህን ልጆች በርኅራኄ ይመለከታቸዋል፡፡ ለዐመላቸው መበላሸት ጠንቅ የሆነውን ነገር ለይቶ ያውቀዋል፡፡CLAmh 138.1

    ክርሰቲያን የሆነ ሠራተኛ ወጣቶችን ወደ ክርስቶስ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ በጥበብና በዘዴ እንዲወዱት ሊያደርግ ይችላል፡፡ ሊያደፋፍራቸውና ተስፋ ሊያሳድርባቸው ይችላል፡፡ በክርስቶስ ጸጋ አማካይነት ሊለወጡ ይችላሉ፡፡ “መንግሥተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉት ናት” ይባልላቸዋል፡፡CLAmh 138.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents