Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    30—እግዚአብሔርን እንወቅ?

    በዚህ አለም እስካልን ድረስ እንደ መድኃኒታችን እግዚአብሔርን ማገልግል አለብን ፡፤ የእግዚአብሔርን ጠባይ በመውረስ አምላክን በሥራችን አማካኝነት ለሌሎች ማሳውቅ ይገባናል ። ታድያ የእርሱን ጠባይ ለመውረስና ከእርሱ ጋር የሥራ ተባባሪ ለመሆን እርሱን በሚገባ ማውቅ ያሻል፡፡ እርሱ ራሱን በገለጠልን መሠረት ልናውቀው ይገባል ፡፡CLAmh 169.3

    እግዚአብሔርን ማወቅ የዕውነትኛ ትምህርትና የታማኝነት አገልግሎት ሁሉ መሠረት ነው። ከፈተና ለመዳን የሚያስተማምን ዋስ ነው፡፡ በጠባያችን እርሱን እንድንመስል የሚረዳን እርሱን በሚገባ ማወቃችን ነው፡፡CLAmh 169.4

    ይህ ዕውቀት ለዚህና ለወዲያኛው ኑሮ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡” (ምሳሌ 9፡10) ፡፡CLAmh 169.5

    እርሱን በማወቃችን “ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ሰጠን፡፡” (2ጴጥሮስ 1፡3) ፡፡CLAmh 170.1

    “እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ያውቁ ዘንድ ይህች የዛላለም ሕይወት ናት፡፡” (ዮሐንስ 17፡3 ፡ ኤርሚያስ 9፡23-24)CLAmh 170.2

    እግዚአብሔር ስለራሱ የገለጠልንን ራዕይ ማጥናት አለብን፡፡ “አሁን ከእርሱ ጋር ተስማማ ሰላምም ይኑርህ በዚያም በጎነት ታገኛልህ” (ኢዮብ 22፡21)CLAmh 170.3

    “የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘለዓለም ኃይሉ ደግሞም አምላክነቱም ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሠሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና፡፡” (ሮሜ 1፡20) ፡፡CLAmh 170.4

    አሁን የምናየው የተፈጥሮ ውበት የኤደንን ከብር በመጠኑ ብቻ ያስረዳናል፡፡ ኃጢአት የመሬትን ውበት አበላሽቷል፡፡ በማንኛውም ነገር ላይ የክፋት ምልክት ይታይበታል፡፡ ግን አሁንም ቢሆን ውበት ደምቆ ይታያል፡፡ በተፈጥሮ አማካይነት ኃይል የሆነ ታላቅ ምህረት፤ ደግነት ፍቅር የሞላበት ፈጣሪ መሬትን ፈጥሮ በሕይወትና በደስታ እንደሞላት ለማየት ይቻላል፡፡ ምንም ቢበላሽ ማንኛውም ፍጥረት የፈጣሪን ጥበብ መግለጡ አይቀርም፡፡ በየሄድንበት የእግዚአብሔርን ድምጽ መስማታችን፤ የደግነቱን ምልክት ማየታችን አይቀርም፡፡CLAmh 170.5

    ነጓድጓድ፤የባህር ሞግድ፤የዱር አራዊት የአየር አዕዋፍ ሳይቀሩ በተፈጥሮአቸው ፈጣሪን በማመስገን ድምጻቸውን ያስተጋባሉ፡፡CLAmh 170.6

    በየብስ፤በአየርና በባህር ላይ በተለያዩ ህብረ ቀለማት የእግዚአብሔርን ክብር እንመለከታለን፡፡ ተቃዋሚ የሆኑ ኮረብታዎች የሃይሉ ምልክት ናቸው፡፡ ለምለም ቅጠሎቻቸውን የሚያወዛውዙት ዛፎችና ውብ ቀለማቸው አይን የሚማርኩ አበቦች ፈጣሪን ያስታውሱናል፡፡CLAmh 170.7

    መሬትን እንደ ስጋጃ ያስጌጠውን ለምለም ሳር ስንመለከት አምላካችን ለሁሉ አሳቢ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ የባህር ጥለቀት የመሬት ስፋት የአምላክን ባለጠግነት ያመለክታል፡፡CLAmh 170.8

    እንቁዎችን በባህር ውስጥ፤ ዕብነ በረድን በቋጥኝ የፈጠረ አምላክ የውበት አምላክ ነው፡፡ በሰማይ አድማስ የምታወጣው ፀሀይ የፍጥረት ሁሉ ሕይወትና ብርሃን ፈጣሪ መሆኑን ታበስራለች፡፡ መሬትን የሚያስጌጠው ሰማይን የሚያበራው ውበትና ድምቀት ሁሉ ስለ እግዚአብሔር ይናገራሉ፡፡ “ክብሩ ሰማያትን ከድኗል፡፡” (ዕንባቆም 3፡3) ፡፡CLAmh 170.9

    “ምድርም ከፍጥረት ተሞላች (መዝሙር 104፡24) “ቀን ለቀን ነገር ታወጣለች፤ሌሊትም ለሌሊት እውቀትን ትናገራለች፡፡ ነገር የለም መናገርም የለም፡፡ ድምጻቸውም አይሰማም፡፡ ድምጻቸው ወደ ምድር ሁሉ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ፡፡” (መዘሙር 19፡2-4) ፡፡CLAmh 171.1

    ማንኛውም ነገር ስለ አባትነቱ ጥንቃቄና ልጆቹን ለማስደሰት ስላለው ጥረቱ ይናገራል፡፡ ተፈጥሮን የሚያሠራውና ደግፎ የሚይዘው ታላቅ ኃይል የሳይንስ ሰዎች እንደሚሉት አንድ አጋጣሚ ደንብና የሚሠራጭ ተራ መመሪያ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር መንፈስ ነው፡፡ ግን አካል አለው፡፡ ራሱን ገልጦልናልና፡፡CLAmh 171.2

    “እግዚአብሔር ግን እውነተኛ አምላክ ነው፡፡ እርሱም ሕያው አምላክና የዘለዓለም ንጉሥ ነው፡፡ ከቁጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች፡፡ አሕዛብም መዓቱን አይችሉም፡፡ እናንተም ሰማይን ምድርን ያልፈጠሩ እነዚህ አማልክት ከምደር ላይ ከሰማይም በታች ይጠፋሉ ትሏቸዋላቸሁ” ምድርን በኃይሉ የፈጠረ፤ዓለሙን በጥበቡ የመሰረተ ሰማያትንም በማስተዋሉ የዘረጋ እርሱ ነው፡፡ የያዕቆብ ዕድል ፈንታ እንደ እነዚህ አይደለም፤ እርሱ የሁሉ ፈጣሪ ነውና፤ እሥራኤልም የርስቱ ነገድ ነውና፤ስሙ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው፡፡” (ኤርምያስ 10፡11፣12፣16) ፡፡CLAmh 171.3

    እግዚአብሔር ፍጥረትን ቢፈጥርም አምላክ በተፈጥሮ ውስጥ አለ ማለት አይደለም፡፡ ግን የተፈጠሩት ነገሮች የእግዚአብሔርን ባሕርይና ኃይል ያመለክታሉ፡፡ ይሁን እንጂ ተፈጥሮን እነደ አምላክ ቆጥረን ማምለክ አይገባንም፡፡ ሰዎች በሠለጠኑበት ሥራ ለዓይን የሚያስደስቱ ብዙ ነገሮች ይሠራሉ፡፡ በተሠሩት ዕቃዎች አማካይነት የሠሪውን ጥበብ እናደንቃለን፡፡ ግን የተሠራው ዕቃ ተሠሪ እንጂ ሠሪ አይደለም፡፡CLAmh 171.4

    ክብር የሚያገኘው ሠሪው እንጂ የተሠራው እቃ አይደለም፡፡ የእግዚአብሔር ጥበብ መግለጫ ቢሆንም ልናከብር የሚገባንን ፈጣሪውን እንጂ ፍጡሩን አይደለም፡፡CLAmh 171.5

    “አዳራሹን በሰማይ የሠራ ጠፈሩንም በምድር የመሰረተ የባሕርንም ውኃ ጠርቶ በምድር ፊት ላይ የሚያፈስሰው እርሱ ነው፤ስሙም እግዚአብሔር ነው፡፡” (አሞጽ 9 ፡ 6) ፡፡CLAmh 171.6

    የፍጥረት ታሪክ በሳይንስ አማካይነት ሊብራራ አይችልም፡፡ የሕይወትን ምሥጢር ዘርዘሮ የሚያስረዳ ሳይንስ የት አለ?CLAmh 171.7

    “ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንዲዘጋጁ ስለዚህ የሚታየው ነገር ከሚታዩት እናዳልሆነ በዕምነት እናስተውላለን፡፡” (ዕብራውያን 11፡3) ፡፡CLAmh 172.1

    “ብርሃን ሠራሁ፤ጨለማውንም ፈጠርሁ፤ደኅንነትን እሠራለሁ፤ክፋትን እፈጥራለሁ፤እነዚህን ሁሉ ያደረግሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፡፡ እኔ ምድርን ሠርቻለው፤ ሰውንም በእርስዋ ላይ ፈጥሬያለሁ፡፡ እኔ በእጄ ሰማያትን ዘርግቼአለሁ፡፡ ሠራዊታቸውንም ሁሉ አዝዣለሁ፡፡CLAmh 172.2

    እጄ ምድርን መስርታለች፤ቀኜም ሰማያትን ዘርግታለች፡፡ በጠራኋቸው ጊዜ በአንድነት ይቆማሉ” (ኢሳያስ 45፡7፣12 ፤ ምዕራፍ 48፡13) ፡፡CLAmh 172.3

    እግዚአብሔር ዓለምን ሲፈጥር ዱሮ በነበረ ነገር ላይ አልነበረም፡፡ “እርሱ ተናግሮአልና ሆኑ፤እርሱ አዘዘ ጸኑም፡፡” (መዘሙር 33፡9) ፡፡CLAmh 172.4

    ረቂቅም ሆኑ ጉልህ፤መንፈሳዊም ሆነ ሥጋዊ በአምላክ ቃል ለቁም ነገር ተፈጠረ፡፡ ሰማያትና ሠራዊታቸው ምደርና በእርሷ ላይ ያሉት ሁሉ በቃሉ ተፈጠሩ፡፡CLAmh 172.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents