Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ወንጌል ለድኆች

    ክርስቶስ ከአይሁድ ታላላቅ መምህራን እንዳንዱ ሆኖ ሊከበር ይችል ነበር፤ ግን ወንጌልን ለድኆች ማዳረስን መረጠ፡፡ በመንገድ ላይና በየመተላለፊያው ያሉት ቃሉን እንዲሰሙ ከቦታ ወደ ቦታ ይዛወር ነበር፡፡ በየተራራው ሥር፤ በየባሕሩ ዳር፤ በየመንገዱ ቃለ እግዚአብሔርን ሲያብራራ ይሰማ ነበር፡፡ አረማውያን (አሕዛብ) ቃሉን እንዲሰሙ በቤተ መቅደሱ ውጪና አደባባይ ላይ እየሆነ ያስተምር ነበር፡፡CLAmh 126.6

    ጥቅስን ሲያብራራ ከጸሐፊዎችና ከፈሪሳውያን በተለየ ሁኔታ ስለነበር ብዙ አዳማጭ አገኘ፡፡ ሊቃውንቱ ያስተምሩ የነበር የሰውን ወግና ልማድ፤ በግምት ነበር፡፡ ሰዎች ስለእግዚአብሔር ቃል የጻፉት ማብራሪያ በእግዚአብሔር ቃል ምትክ ሆኖ ይነገር ነበር፡፡ የክርስቶስ የማስተማሪያ አርእስት ግን የእግዚአብሔር ቃል ነበር፡፡ ጠያቂዎችን “ተጽፏል” “መጽሐፍ እንዲህ አይልምን” “ምን ታነባለህ?” በሚሉ መጠይቃን ሐረጎች ያፋጥጣቸው ነበር፡፡ በወዳጅም ሆነ በጠላት አማካይነት ጥያቄ ሲቀርብ እግዚአብሔርን ከማስተማር አይመለስም፡፡ የወንጌልን መልዕክት በግልጥና በኃይል ያቀርብ ነበር፡፡ ቃሉ በአበውና በነቢያት ቃል ላይ አበራ፡፡ መጻሕፍት ለሰዎቹ አዲስ ሆነው ታዩአቸው፡፡ ሰሚዎቹ ከዚያ በፊት የዚያ ዓይነት ጥልቀት አይተውበት አያውቁም ነበር፡፡CLAmh 127.1

    ክርስቶስን የመሰለ ወንጌላዊ ታይቶ አይታወቅም፡፡ የሰማይ ንጉሥ ሳለ እኛን ለማስተማር ሲል እኛን እስከመምሰል ድረስ ዝቅ አለ፡፡CLAmh 127.2

    ድኃ ሆነ ሀብታም፤ ጌታ ሆነ አገልጋይ ክርስቶስ የቃል ኪዳን መልዕክተኛ የመዳንን የምሥራች ለሁሉም አወጀ፡፡ ታላቅ ፈዋሽ የመሆኑ ዜና በምድረ ፓለስቲና ተነዛ፡፡ ርዳታ ለመጠየቅ በሽተኞች በሚያልፍበት መንገድ ሁሉ ይሰበሰቡ ነበር፡፡ ብዙዎች ቃሉን ለመስማትና በእጁ እንዲዳስሳቸው ይመጡ ነበር፡፡ የክብር ንጉሥ ሰብአዊነትን ለብሶ ወንጌልን ለማስተማርና ድውያንን ለመፈወስ ከከተማ ወደ ከተማ ይዞር ነበር፡፡CLAmh 127.3

    በብሔራዊ ዓመት በዓል እየተገኘ የተለምዶ ስብከት ያሰለቸውን ሕዝብ ስለ ሰማያዊ ነገር በማስተማር ዘለዓለማዊነትን ቁልጭ አድርጎ ይገልጥለት ነበር፡፡ ለሁሉም ከጥበብ ጎተራ ክቡር መዝገብ አደላቸው፡፡ በሚያስተውሉት ቀላል ያነጋገር ዘይቤ አስረዳቸው፡፡ የግሉ በሆነ ዘዴ የተቸገሩትንና ያዘኑትን ረዳቸው፡፡ በኃጢአት በሽታ የተለከፉትን ነፍሳት በትኅትና መንፈስ አገለገላቸው፡፡ አበረታቸውም፡፡CLAmh 127.4

    የመምህራን ሁሉ የበላይ (አለቃ) የሆነው በጣም በሚያውቁት አቀራረብ ቀረባቸው፡፡ እውነትን ከእርሱ የሰሙት ሁሉ ርኅራኄው እንዳይረሳቸው አድርጎ አስተማራቸው፡፡ ያስተማራቸው ሁሉ የእርሱ ፍጹምና በልባቸው የደስታ ስሜት እንዳሳደረባቸው ተሰማቸው፡፡ ሲያስተምር ቀጥተኛ፤ ማብራሪያው ግልጥ፤ ቃላቱ ባለለዛና የሚያስደስት ስለሆነ ሰሚዎቹ ሁሉ ልባቸው ይረካል፡፡ ችግረኞችን ሲያነጋግር ግልጥና ቁም ነገረኛ ስለነበር ቃሉ ተባረከለት፡፡CLAmh 127.5

    ኑሮው ሥራ የበዛበት ነበር! በየቀኑ ወደ ድሆች ቤት እየገባ ላዘኑት ሰላምን፤ ተስፋ ለቆረጡት ተስፋን ይናገር ነበር፡፡ ቸር፣ ልበገር፣ አዛኝ ስለነበር የወደቁትን ያነሣ ያዘኑትን ያጽናና ነበር፡፡ በየሄደበት በረከትን ይሰጥ ነበር፡፡CLAmh 128.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents