Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    34—ከሌሎች ጋር መኖር

    በማህበራዊ ኑሮ ውስጥ ራስን መቆጣጠር፤ ትዕግሥትን መታዘዝ ሊኖር ያሻል፡፡ በአቋም፤ በትምህርት፤ በልምድ የተለያየን ስንሆን ስለ አንድ ነገር ያለን የየግል አስተያየትም በዚያው ልክ ይለያያል፡፡CLAmh 199.1

    ፍርድ አሰጣጣችን የተለያየ ነው፡፡ ስለ እውነት ያለን አስተሳሰብ፤ ስለኑሮ አመራር ያለን እምነት አይመሳሰልም፡፡ የአንዱ የኑሮ ትግል ከሌላው ጋር ፈጽሞ ተመሰሰይነት የለውም፡፡ ለአንዱ ችግር መስሎ የሚታየው ለሌላው አይከብደውም፡፡ ለአንዱ እንደ ቀላል የሚቆጠረው የሥራ ዓይነት ሌላውን ግራ ያጋባዋል፡፡CLAmh 199.2

    የሰው ተፈጥሮ ደካማ፤ ቀላል የማያስተውል በመሆኑ አለመግባባት በቀላሉ ሊፈጠር ስለሚችል አንዱ የሌላውን ስሜት እንዳይጎዳ መጠንቀቅ አለበት፡፡ የእኛ አድራጎት በሌላው ሰው ኑሮ ላይ ምን ያህል ተጽዕኖ እንዳለው በሚገባ አናውቅም፡፡ የምንሠራውን ወይም የምንናገረውን ከግምት ውስጥ አናገባውም ይሆናል፤ ግን ጠለቅ አድርገን ብንመረምር ደግሞ ክፉ ውጤት ማስከተሉን እንገነዘባለን፡፡CLAmh 199.3

    ብዙዎች ሽክም ስላልከበዳቸው፤ ልባቸው ኀዘንን ቀምሶ ስለማያውቅ፤ ስለሌሎች የደረሰባቸው ችግርና ድንግርግር ባለመኖሩ፤ እውነተኛ ቀንበር የወደቀበት ሰው ችግር አይገባቸውም፡፡ ልጅ ለአባቱ ድካምና ጭንቀት ዋጋ እንደማይሰጠው ሁሉ እነርሱም የሌላው ድካም አይገባቸውም፡፡ አባቱ ሲሰጋና ግራ ሲገባው ልጁ ምክንያቱ አይሰተዋለውም፡፡ እርሱ ከነገሩ ገለልተኛ ነው፡፡CLAmh 199.4

    ግን ዕድሜው እየገፋ ሲሄድ፤ ኃለፊነት ሲሰማው፤ ወደ ጥንቱ ዘወር ይልና ዱሮ ያልተስተዋለውን የአባቱን ድካም ያስተውላል፡፡ የደረሰበት ጭንቅ መምህር ሆኖ ያስተምረዋል፡፡CLAmh 199.5

    የብዙ ኃላፊዎች ሥራ እስኪሞቱ ድረስ አይታወቅላቸውም፡፡ ሌሎች በእነርሱ እግር ተተክተው እነርሱ የቀመሱትን የችግር እፍታ ሲቀምሱ ያን ጊዜ ሞያቸውን ያውቁላቸዋል፡፡ ዱሮ በሌሎች ይታዩአቸው የነበሩትን የጎሉ ስህተቶች እንደሌሉ ይቆጥሩአቸዋል፡፡ በእነርሱ ሲደርስባቸው ብቻ ለሌሎች ማዘንን ይማራሉ፡፡ እግዚአብሔር ሰዎችን የኃላፊነት ቦታ እንዲይዙ ይፈልጋል፡፡CLAmh 200.1

    ሲሳሳቱ ሊያርማቸው ወይም ከሥልጣን ሊነቅላቸው ሥልጣን አለው፡፡ ፍርድ የእግዚአብሔር ብቻ ነውና በአምላክ ሥራ ገብተን ለመፍረድ እንዳንሞክር መጠንቀቅ አለብን፡፡CLAmh 200.2

    ጌታችን “እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ፤ በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋልና፤ በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፍርባችኋል” ሲል አስጠንቅቆናል፡፡ (ማቴዎስ 7፡1-2) ፡፡CLAmh 200.3

    የሠራችሁት ሁሉ መዝገብ በእግዚአብሔር ፊት መቅረቡን አትርሱ፡፡ “አንተ የምትፈርድ ሰው ሆይ፤በሌላው በምትፈርድበት ነገር ራስህን ትኮንናከህ” መባሉን አንርሳ፡፡ (ሮሜ. 2፡1) ፡፡CLAmh 200.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents