Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የወላጆች የመጀመሪያ ተግባር

    ልጆቻችንን ወደ ትክክለኛው አቅጣጫ እንድንመራ በኛ በክርስቲያን ወላጆች ላይ አደራ ተጥሎብናል፡፡ እንደ ክርስቶስ ያሉ አገልጋዮች እንዲሆኑ በጥንቃቄ፣ በጥበብና በእርጋታ መመራት አለባቸው፡፡ ልጆቻችንን ለእግዚአብሔር አገልግሎት እንድናሳድግ የተቀደሰ ቃል ኪዳን ገብተናል፡፡ የአገልግሎት ሕይወትን እንዲመርጡ በሚያደርጋቸው ሁናቴ ማሳደግና የሚያስፈልገውንም ትምህርት መስጠት የመጀመሪያ ተግባራችን ነው፡፡CLAmh 37.3

    “እግዚአብሔር እኛ እንዳንጠፋ ግን የዘላለም ሕይወት እናገኝ ዘንድ ዓለሙን ስለወደደ አንድ ልጆን ሰጠ፡፡” ክርስቶስ ደግሞ እንደወደደን ራሱንም ስለኛ አሳልፎ እንደሰጠ፡፡” ዮሐ 3፡16፤ ኤፌ 5፡2፡፡ ፍቅር ካለን እንሰጣለን፡፡ ልንማረው ላናስተምረው የሚገባን “መገልገል ሳይሆን ማገልገል” ነው፡፡ ማቴ 20፡28CLAmh 37.4

    ልጆች የራሳቸው አለመሆናቸው ሊገባቸው ይገባል፡፡ የክርስቶስ ናቸው፡፡ በደሙ የተገዙ የፍቅሩ ገንዘቦች ናቸው፡፡ በኃይሉ ስለሚጠብቃቸው ይኖራሉ፤ ጊዜያቸው፣ ጉልበታቸውና ችሎታቸው የእርሱ ናቸው፤ እንዲጠቀምባቸውም መዳበርና መሠልጠን አለባቸው፡፡CLAmh 37.5

    “ከመላዕክት ቀጥሎ በእግዚአብሄር አምሳል የተፈጠረው ሰብአዊ ቤተሰብ ከፍጥረት ሁሉ እጅግ ብልጫ ያለው ነው፡፡ እግዚአብሔርም እንዲቻል ባደረገው መሠረት ሊሆኑ የሚገባቸውን እንዲሆኑና በሰጣቸውም ኃይል የተቻላቸውን እንዲያደርጉ ይመኛል፡፡CLAmh 38.1

    ሕይወት ምሥጢራዊና የተቀደሰ ነው፡፡ የሕይወት ሁሉ ምንጭ ለሆነው እግዚአብሔር ማስታወቂያ ነው፡፡ በሕይወት ውስጥ ያሉት ዕድሎች የተከበሩ ናቸው፡፡ ሊሻሻሉም ይገባል፡፡ እነዚህም ዕድሎች አንድ ጊዜ ካመለጡ ለሁልጊዜም አይገኙም ማለት ነው፡፡CLAmh 38.2

    እግዚአብሔር የዘለዓለምን ሕይወት እውነተኛት ከፊታችን ደቅኖልናል፤ የማያልፈውንና የማይጠፋውንም ነገር ልናገኘው እድንችል አድርጓል፡፡ በመላው ችሎታችን ዘላቂ የሆነውን ነገር በመፈለግ በማያሰጋውና እውነተኛ በሆነው መንገድ ላይ እንድንገኝ ጠቃሚና አስከባሪ የሆነ እውነት አቅርቦልናል፡፡CLAmh 38.3

    እግዚአብሔር ራሱ ወደቀረጻት ትንሽ ዘር ይመለከታል፤ በውስጧም የተጠቀለለውን የተዋበ አበባ፤ ቁጥቋጦውንም ወይም የተንሰራፋውን ዛፍ ያያል፡፡ እንደዚሁም በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ ያለውን ችሎታ ሁሉ ያያል፡፡ የምንኖረው ለተወሰነ ዓላማ ነው፡፡ እግዚአብሔር ለሕይወታችን ያለውን ፕላን(እቅድ) ሰጥቶናል፤ ወደከፍተኛው የእድገት ደረጃም እንድንደርስ ይመኛል፡፡CLAmh 38.4

    በቅድስና፣ በደስታና በጠቃሚነት ዘወትር እንድናድግ ምኞቱ ነው፡፡ ሁሉም የተሰጣቸው ችሎታ የተቀደሰ መሆኑን እንዲያስተውሉ፤ እግዚአብሔርንም ስለ ስጦታው እንዲያመሰግኑትና ስጦታቸውንም በትክክለኛው መንገድ እንዲጠቀሙበት መማር አለባቸው፡፡ እያንዳንዱ ወጣት ሙሉ ኃይሉን እንዲያደራጅና ችሎታውንም በትጋት እንዲጠቀምበት የእግዚአብሄር ምኞት ነው፡፡ በዚህ ዓለም ጠቃሚና የተከበረ በሆነው ነገር እንዲደሰቱ፣ ደግ እንዲሆኑ፣ ደግ እንዲያደርጉና ለመጭው ሕይወት በሰማይ መዝገብ እንዲያከማቹ ምኞቱ ነው፡፡CLAmh 38.5

    ራስን ወዳድ በማያደርጉትና በተከበሩት ነገሮች የማደግ ምኞት ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ምሳሌአቸው ወደሆነው ወደ ክርስቶስ ይመልከቱ፡፡ እርሱ በሕይወቱ የገለጸው የተቀደሰ ዓላማ ሊኖራቸው ይገባል፤ ይህም ዓላማ እነሱ ስለሚኖሩባት ዓለም የተሻለች እንድተሆን ነው፡፡ የተጠሩት ለዚህ ዓይነት ተግባር ነው፡፡CLAmh 38.6

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents