Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የተፈጥሮን ምሥጢር ማስተዋል

    ክርስቶስ በድህነት ቤተሰብ ያሳለፈው የልጅነት ጊዜው በዘመኑ ክፋት አልተበከለም ነበር፡፡ በአናጢው መሥሪያ ቤት ውስጥ ሲሠራ በመዋል፤ በቤት ውስጥ በመላላክ፤ ታዛዥነትንና ሥራን በመማር፤ በተፈጥሮ መካከል በመንሸራሸርና በመዝናናት፤ ዕውቀቱን አዳበረ፡፡ የተፈጥሮንም ምሥጢር ጠንቅቆና ዘልቆ አወቀ፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል አጠና፡፡ ከሁሉም በበለጠ ደስ የሚለው የዕለት ሥራውን ጨርሶ ወደ ኮረብታ ዘወር ብሎ ወይም በጫካ ውስጥ ተንበርክኮ ከአብ ጋር በሚገናኝበት ጊዜ ነበር፡፡CLAmh 142.2

    ጧት ጎህ ሲቀድ ዘወር ባለ ቦታ ሆኖ መጽሐፍን ማጥናት፤ ወይም መጸለይ ልማዱ ነበር፡፡ ንጋትን የሚቀበለው በመዝሙር ነበር፡፡ በሥራ ጊዜም ደስታውን በዜማ ይገልጥ ነበር፡፡ የደከሙትንና የዛሉትን ሰዎች በመዝሙር አማካይነት በልባቸው ሰላም እንዲኖር ይረዳቸዋል፡፡CLAmh 142.3

    በሚያስተምርበት ጊዜ ክርስቶስ ብዙ ጊዜ በውጭ ይኖር ነበር፡፡ ከቦታ ወደ ቦታ ሲዘዋወር በእግሩ ነበር፤ ብዙ ጉባዔም በሜዳ ላይ ሰብስቦ አስተምሯል፡፡CLAmh 142.4

    ደቀመዛሙርቱን ሲያሠለጥን ከከተማው ግርግር ገለል አድርጎ ወደ ገጠር ይወስዳቸው ነበር፡፡ ራስን መካድ፣ ሃይማኖትን፣ በልክ መኖርን ያስጠናቸው ነበር፡፡ ደቀመዛሙርቱ የሐዋርያነት ሥልጣን የተቀበሉና የተራራው ስብከት የሆነበት ሥፍራ ከገሊላ ባሕር ራቅ ብሎ በዛፎች ሥር ነበር፡፡CLAmh 142.5

    ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱንና ሕዝቡን ከጠራው ሰማይ በታች፤ በመስክ ላይ ወይም በሐይቅ ዳር ሰብስቦ ያስተምር ነበር፡፡ በዙሪያው ያለውን የእጁን ፍጥረት በማሳየት ሰው ሠራሹን ትተው የእግዚአብሔርን ሥራ እንዲያደንቁ አደረጋቸው፡፡ የመንግሥቱ አቋም የሚገለጠው በተፈጥሮ ሥነ ሥርዓትና ይዞታ ነው፡፡ ሰዎች የእግዚአብሔርን ሥራ ሲመለከቱ የመለኮትን እውነት ሊያስተውሉ ይችላሉ፡፡ ለወደፊቱም መለኮታዊ ምሥጢር በተፈጥሮ አማካይነት ይከለስላቸዋል፡፡ አእምሮአቸው ይጎለምስላቸዋል፤ በልባቸውም ሰላም ይሰፍናል፡፡CLAmh 142.6

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents