Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ውሃን በሚገባ መጠቀም

    በጤናም ጊዜ ሆነ ሲታመሙ ውኃ አምላክ ከሰጠን በረከቶች ታላቁ ነው፡፡ በሚገባ ከተገለገሉበት ለጤና መድኅን ነው፡፡ የሰዎችንና የእንስሳትን ጥማት (ጥም) ለማርካት ከአምላክ ዘንድ የተሰጠ መጠጥ ነው፡፡CLAmh 99.5

    በነፃ ተጠጥቶ ለአካል ተፈላጊ የሆነውን ነገር ለማቅረብ፤ አካል በሽታን እንዲቋቋም ይረዳል፡፡ ውኃን ለንጽህና ማዋል (መታጠብ) የደምን መዘዋወር ከሚረዱት ነገሮች ከፍተኛው ነው፡፡ በቀዝቃዛ ውሃ ገላን መታጠብ ለጡንቻዎች መፍታታት ዋና ነገር ነው፡፡ በሙቅ ውኃ መታጠብ ደግሞ የቆዳን ቀዳዳዎች ከፍቶ ከአካል ውስጥ ቆሻሻው እንዲጣራ ይረዳል፡፤ በሞቀ ወይም በቀዝቃዛ ውኃ መታጠብ ነርቮችን አነቃቅቶ የደምን መዘዋወር ያስተካክላል፡፡CLAmh 99.6

    ውኃ በሚገባ ሲሠራበት የሚሰጠውን ጥቅም በደንብ ስለማያውቁ ብዙዎች እንደ ጠላት ይፈሩታል፡፡ የውኃ ሕክምና የሚገባውን ያህል ተወዳጅነት አላገኘም፤ ከአገልግሎት ላይ ለማዋልም ብዙዎች ሊያሳዩት የማይፈልጉትን ትልቅ ጥረትና ዕውቀት ይጠይቃል፡፡ ግን ማንም ቢሆን ያን የሕክምና ዘዴ ባለማወቅ ወይም በቸልተኛነት አሳቦ ለመተው ምክንያት የለውም፡፡ በቤት ውስጥ በውኃ አማካይነት የሚሰጠውን ሕክምና ማንም ሊያውቀው ይገባል፤ በተለይ እናቶች ለጤነኛና ለበሽተኛ የቤተሰብ አባሎች እንዴት መጠንቀቅ እንደሚገባቸው ሊያውቁ ይገባል፡፡CLAmh 99.7

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents