Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በኃጢአት የተከሰሰችው ሴት

    የቤተ መቅደሱ ክብረ በአል አብቅቶ ነበር፡፡ ካህናቱና ሊቃውንቱ በክርስቶስ ላይ የዶለቱት ሴራ ሳይዝላቸው ቀረ፡፡ ሲመሽ ሰው ሁሉ ወደየቤቱ ሲጓዝ፤ “የሱስ ወደ ደብረዘይት ሄደ፡፡” (ዮሐንስ 7፡53 ፤ 8፡1) ፡፡CLAmh 159.4

    የሱስ ከህዝቡ ጩኸትና ግርግር ከቀናተኞቹ ሊቃውንት ገለል ብሎ በዛፍ ስር ሆኖ ከእግዚአብሔር አብ ጋር የግል ግንኙነት ያደርግ ነበር ፡፡CLAmh 159.5

    ድንገት አንድ ነገር ጸሎቱን አቋረጠበት ፡፡ ፈሪሳውያንና ሊቃውንት አንዲት የደነገጠች ሴት እየጎተቱ ስባተኛውን ትእዛዝ ተላልፋለች እያሉ ሲጮሁ ይሰሙ ነበር ፡፡ ወደ የሱስ ፊት ለማቅረብ ሴትየዋን እየገፈተሩ ግብዝና በተቀላቀለበት አክብሮት “መምህር ሆይ ይህች ሴት ስመነዝር ተገኝታ ተያዘች፡፡ ሙሴም እንደዚህ ያሉት እንዲወገሩ በህግ አዘዘን ፡፡ አንተስ ስለእርሷ ምን ትላለህ?” አሉት ፡፡ (ዮሐንስ 8፡4-5)CLAmh 159.6

    በተንኮል አክብሮት የሸፈኑት አደድማቸውን እርሱን ለማጥመድ መዘጋጀታቸውን ያጋልጥባቸው ነበር ፡፡ የሱስ ሴትየዋን በነጻ ቢያሰናብታት የሙሴን ህግ ሻረ ሊባል ነው፤ የሞት ፍርድ ቢፈርድባት ደግሞ የሮማውያንን ስልጣን ተጋፋ ሊሉት ነው ፡፡CLAmh 160.1

    የሱስ ከፍርሀት የተነሳ የምትንቀጠቀጠውን ተከሳሽና ትእቢተኞቹንና ሰብአዊ ርህራሄ የጎደላቸውን ፈሪሳውያን ተመለከተ ፡፡ ነገሩን አላዳነቀውም ነበር ፡፡ ነገሩን ሰምቶ እንዳልሰማ አንገቱን አቀርቅሮ በመሬት ላይ ይጽፍ ነበር ፡፡CLAmh 160.2

    በመዘግየቱ ነገሩን ችላ ያለው መስሏቸው ከሳሾቹ በመቅበጥበጥ ይወተውቱት ነበር ፡፡ ግን የሱስ የሚስራውን አይተው አይናቸውን ላክ ቢያደርጉ የተጻፈውን አዩና ጸጥ አሉ ፡፡CLAmh 160.3

    በድብቅ የሰሩት ኃጢአታቸው ሁሉ በጽሁፍ አማካይነት ተገለጠባቸው ፡፡ የሱስ ቀና ብሎ አድመኞቹን አለቃዎች እየተመለከተ “ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድጋይ ይውገራት” አላቸው፡፡ (ቁጥር 7) ፡፡ አሁንም ጽህፈቱን ቀጠለ፡፡CLAmh 160.4

    የሙሴን ህግ አልሻረም፤ የሮማውያንን ስልጣንም አልተጋፋም፡፡ ከሳሾቹ ተረቱ ፡፡ በማስመሰል የሚመጻደቁበት የቅዱስነት ልብሳቸው ስለተቀደደባቸው በንጹሁ ፊት ተጋልጠው ቆሙ፡፡ ተከሳሿን ከሩህሩሁ ጌታ ጋር በመተው የተደበቀው ግፋቸው በጉባኤው ፊት እንዳይጋለጥባቸው ፈርተው አፍረውና አንገታቸውን ደፍተው ሹልክ ብለው ጠፉ፡፡CLAmh 160.5

    የሱስ ጽህፈቱን ጨረሰና ቀና ብሎ ለሴትዮዪቱ “አንቺ ሴት ከሳሾችሽ የታሉ? የፈረደብሽ የለምን? አላት ፡፡ እርሷም ጌታ ሆይ አንድ ስንኳ አለች ፡፡ የሱስም እኔም አልፈርድብሽም ሂጂ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትስሪ አላት፡፡” (ቁ 10-11)CLAmh 160.6

    ሴትዮዋ በፍርሃት ድርቅ ብላ በመድህን ፊት ቆማ ነበር ፡፡ “ከእናንተ መካከል ኃጢአት የሌለበት መጀመሪያ ይውገራት” ሲል ይሙት በቃ የተፈረደባት መስሏት ነበር ፡፡ ጌታን እንኳ ቀና ብላ መመልከት ስለፈራች አቀርቅራ ሞቷን ትጠባበቅ ነበር ፡፡CLAmh 160.7

    ከሳሾቿ ትተዋት ሲሄዱ በማየቷ ተገረመች ፡፡ “እኔም አልፈርድብሽም ፤ ሂጂ ከዛሬ ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትስሪ” የሚል የተስፋ ንግግር ሰማች ፡፡ ልቧ ቀጠለ ፤ በጌታ እግር ላይ ወድቃ ከፍቅርና ከጸጸት የተነሳ እያለቀሰች ምስጋናዋን ገለጠች ፡፡CLAmh 160.8

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents