Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የኃጢአት መድኅን

    ከኃጢአት ኑሮ ወደ ንጽህና ሕይወት ለመሸጋገር የሚታገል ማንኛውም ሰው ኃይል የሚያገኘው “ከሰማይ በታች እንደ እርሱ ያለ ስም ለሌላ ካተሰጠው ልንድንበት ከምንችለው” ዘንድ ነው፡፡ (የሐዋርያት ሥራ 4፡12) ፡፡ ክርስቶስ ማንም ዕረፍትንና ከኃጢአት መዳንን “ቢጠማ ወደ እኔ ይምጣ፤ ይጠጣም” ይላል፡፡ (ዮሐንስ 7፡37)፡፡ ለኃጢአት ዋናው መድኅን የክርስቶስ ኃይልና ጸጋ ብቻ ነው፡፡CLAmh 92.6

    ሰው በራሱ ብቻውን የሚወስነው ውሳኔ ዋጋ አይኖረውም፡፡ ሰው ቢምል ቢገዘት ከክፉ ልማድ ሊላቀቅ አይችልም፡፡ በመለኮት ጸጋ ልባቸው ካልታደሰ ሰዎች መሻታቸውን ሊገዙ አይችሉም፡፡CLAmh 92.7

    ለቅጽበትም ቢሆን ራሳችንን በራሳችን ከኃጢአት ነፃ ልናወጣ አንችልም፡፡ ምን ጊዜም ቢሆን ከእግዚአብሔር እጅ አንወጣም፡፡CLAmh 93.1

    እውነተኛ መሻሻል የሚጀምረው ሕይወትን በማንጻት ነው፡፡ ለተሰናከሉት የምናቀርበው እርዳታ የተስተካከለ የሚሆነው ወደ ክርስቶስ የቀረበውን ሰው ጠባይ አምላክ ሲያሳምረው ብቻ ነው፡፡CLAmh 93.2

    ክርስቶስ በሕይወቱ የእግዚአብሔርን ሕግ ሙሉ በሙሉ በመታዘዙ ለሰብአዊ ፍጡር ሁሉ መልካም አርኣያነት ትቷል፡፡ በእርሱ መሪነትና ኃይል በዚህ ምድር የኖረውን ዓይነት ኑሮ እንድንኖር ይፈልግብናል፡፡ የተሰናከሉትን ስናስተምር የእግዚአብሔርን ሕግ ተፈላጊነትና የታማኝነትን ዋጋ ጠበቅ አድርገን መንገር ያስፈልጋል፡፡CLAmh 93.3

    እግዚአብሔርን በሚያገለግልና በማያገለግል መካከል ቁልጭ ያለ ልዩነት መኖሩን ማስረዳት ችላ አትበሉ፡፡ እግዚአብሔር ፍቅር ነው፤ ይሁን እጂ ሕጉን ሆነ ብሎ የሚያፈርሰውን በዋዛ አያልፈውም፡፡ በእግዚአብሄር መንግሰት ዘንድ ወስላቶች እንደዋጋቸው የሚከፈሉበት ደንብ አለ፡፡ የሚያከብሩትን ብቻ ያከብራል፡፡ ሰው በዚህ ዓለም የሚያሳየው ጠባዩ የዘለዓለም መዳረሻው ይወስንለታል፤ ወይም ይወስንበታል፡፡ የዘራውን ያጭዳል፤ የከመረውን ይወቃል፡፡CLAmh 93.4

    እግዚአብሔር የሚፈልገው ፍጹም ታዛዥነት ነው፡፡ ትዕዛዙን በደፈናው ሳይገልጥ አልተወውም፡፡ ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር ለማስማማት ብቻ ሲል ያልተፈለገውን ነገር አልደነገገም፡፡CLAmh 93.5

    መድኃኒታችን ራሱ የሰዎችን ደካማነት ለብሶ ኃጢአት የሌለበት ኑሮ በመኖር ሰዎች በሰብአዊ ደካማነት ምክንያት ኃጢአትን ድል መንሣት አንችልም እንዳይሉ ምሳሌ ሆኖአቸዋል፡፡ ክርስቶስ የመጣው የመለኮት ባሕሪይ ተካፋይ ሊያደርገን ነው፡፡ በሕይወቱም በመለኮታዊነት የተደገፈ ሰብአዊነት ኃጢአት አለመስራቱን ገለጠልን፡፡CLAmh 93.6

    ሰው እንዴት ድል መንሣት እንደሚችል ለማሳየት መድኃኒታችን ድል ነሣ፡፡ ክርስቶስ የሰይጣንን ፈተና በሙሉ በእግዚአብሔር ቃል መሣሪያነት ተከላከለው፡፡ በእግዚአብሔር ተስፋ በመተማመን ሕጉን የሚጠብቅበትን ኃይል ስለተቀበለ ሰይጣን ሳይቀናው ቀረ፡፡ ለፈተናው ሁሉ ክርስቶስ የሰጠው መልስ “ተጽፏል” የሚል ነበር፡፡ ክፉን እንድንከላከልበት እግዚአብሔር ቃሉን ለእኛም ሰጥቶናል፡፡ “ስለ ክፉ ምኞት በዓለም ካለው ጥፋት አምልጣችሁ ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች በተስፋ ቃል እንድትሆኑ በእነዚያ ክብርና በጎነት የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋን ሰጠን፡፡ (2ኛጴጥ 1፡4)CLAmh 93.7

    ፈታኙ የእግዚአብሔርን ቃል ኃይል እንጂ፤ የጊዜን አጋጣሚ፤ የእናንተን ድካም፤ የፈተናውን ከባድነት እንዲመለከት አትፍቀዱለት፡፡ የቃሉ ብርታት እኛን ይረዳል፡፡ ባለመዝሙሩ ዳዊት “አንተን እንዳልበድል ቃልህን በልቤ ሰወርሁ፡፡” ይላል፡፡ (መዝሙር 119፡11፣ 17፡4)CLAmh 94.1

    ሰዎችን አበርቱ፤ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር አቅርቧቸው፡፡ በፈተና የወደቁ ሰዎች በውድቀታቸው ተስፋ ይቆርጣሉ፡፤ ወደ እግዚአብሔር ሊቀርቡም የማይችሉ መሆናቸው ይሰማቸዋል፡፡ ይህ አስተሳሰብ ግን በጠላት ተንኮል የተጠነሰሰ ነው፡፡ ኃጢአት ሠርተው መጸለይ ከንቱ ነው ብለው ለሚያስቡ ሰዎች ሊጸልዩ የሚገባቸው ያን ጊዜ መሆኑን ንገሯቸው፡፡ ሐፍረትና ውርደት ተሰምቷቸው ሊሆን ይችላል፤ ቢሆንም ከጸለዩ ምን ጊዜም ታጋሽ የሆነው አምላክ ጸሎቸውን አዳምጦ ኃጢአታቸውን ይቅር ይላቸዋል፡፡CLAmh 94.2

    ርዳታ ቢያሻውም የራሱን ከንቱነት አምኖ በክርስቶስ ላይ የሚተማመን ሰው ቢገፉትም አይወድቅ፡፡ በጸሎት ቃሉን በማጥናት፤ በእርሱ በማመን በጣም ደካማ የሆኑ ሰዎች ከክርስቶስ ጋር አንድ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እርሱም ከያዘ በማይለቅ እጁ ይይዛቸዋል፡፡CLAmh 94.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents