Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ያመስጋኝነት መንፈስ

    ከአመስጋኝነት መንፈስ የበለጠ አእምሮንና አካልን ጤናማ የሚያደርግ ሌላ ነገር አይገኝም፡፡ የትካዜንና የቅሬታን ስሜት መቋቋም ከጸሎት የማያንስ ትልቅ ተግባር ነው፡፡ ወደ ሰማይ የምንጓዝ ከሆንን እንደ አልቃሽ እየተከዝንና እያዘንን እንዴት ወደ ሰማያዊ አባታችን ቤት አንሄዳለን?CLAmh 112.3

    ደስታ ኀጢአት የሚመስላቸውና ሁልጊዜ አንገታቸው ደፍተው የሚኖሩ ክርስቲያናት ነን ባዮች የክርስቶስ ትርጉምና አልገባቸውም፡፡ በዓለም ውስጥ አሳዛኝ በሆነው ነገር ብቻ ደስታ ያለ የሚመስላቸው፤ የተዋቡትን ሕያው አበባዎች በመቅጠፍ ፈንታ የረገፈ ቅጠል መመልከት የሚያስደስታቸው፤ በለመለመ መስክና በከፍተኛ ተራራ የማይደሰቱ፤ የተፈጥሮ ድምፅ ጣዕመ ዜማ ሲያሰማቸው የማያዳምጡ ሰዎች ሁሉ ከክርስቶስ ጋር አንድነት የላቸውም፡፡ የጽድቅ ፀሐይ በልባቸው ውስጥ ጮራውን ሊበትን ሲችል በጨለማ ተከበው ይኖራሉ፡፡CLAmh 112.4

    በሕመም ምክንያት አስተሳሰባችሁ ሊዳምን ይችላል፡፡ ያን ጊዜ በአሳብ አትድከሙ፡፡ የሱስ እንደሚወዳችሁ ታውቃላችሁ፡፡ ደካምነታችሁን ያውቃል፡፡ በክንዱ ላይ በማረፍ ብቻ ፈቃዱን ፈጸማችሁ ማለት ነው፡፡CLAmh 113.1

    ስሜታችንና አስተሳሰባችን ስናጽናናው መበርታቱና መደፋፈሩ የተፈጥሮ ሕግ ነው፡፡ ቃላት የአሳብ መግለጫ መሆኑ ቢታመንም አስተሳሰብ በንግግር መመራቱም አይካድም፡፡ ስለ ሃይማኖታችን ብንናገር፤ በእግዚአብሔር ምሕረትና ፍቅር በበለጠ ደስ ቢለን እምነታችን ከአሁኑ በበለጠ እንደሚበረታ አይጠረጠርም፡፡ የእግዚአብሔርን ቸርነትና ፍቅር በማመስገን ለሚገኘው ታላቅ በረከት መግለጫ ቃል አይገኝለትም፡፡ ከእግዚአብሔር ዙፋን ዘንድ የሚወርደው ምንጭ ሰለሚያጠጣን በምድር ሳለንም እንደወንዝ የማያቋርጥ ደስታ ይኖረናል፡፡CLAmh 113.2

    ልባችንና ከናፍራችን እግዚአብሔርን ወሰን ለሌለው ፍቅሩ እንዲያመሰግን እናሰልጥነው፡፡ ነፍሳችን ደስተኛ እንድትሆንና በቀራንዮ መስቀል ላይ ተስፋዋን እንድታሳርፍ እናድርግ፡፤ የሰማያዊ ንጉስ ልጆች፤ የሠራዊት ጌታ ወንዶችና ሴቶች ልጆች መሆናችንን አንርሳ፡፡ በእግዚአብሔር ላይ ረጋ ያለ እምነት እዲኖረን መብት አለን፡፤CLAmh 113.3

    “የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይግዛ፤ የምታመሰግኑ ሁኑ፡፡” ቆለሳይስ 3፡15፡፡ የራሳችን ችግርና መከራ ረስተን ለስሙ ክብር እንድንኖር ለሰጠን መብት እግዚአብሔርን እናመስግነው፡፡ ለፍቅሩ መግለጫ በየእለቱ የሚፈጽሙልን በጎ ሥራዎች በልባችን ያመስጋኝነት መንፈስ ያሳድሩብን፡፡ ጧት ዓይናችሁን ስትገልጡ ሌሊቱን በሙሉ በሰላም ስለጠቃችሁ አምላክን አመስግኑት፡፡ በልባችሁ ሰላም ስላሳደረ አመስግኑት፡፡ ጧት፣ ቀንና ማታ ምስጋናችሁ መልካም መዓዛ እንዳለው ሽቱ ወደ ሰማይ ይውጣ፡፡CLAmh 113.4

    ሰው እንደምን አላችሁ ሲላችሁ አንዲያዝንልን ብላችሁ ችግራችሁን ለመዘርዘር አትሞክሩ፡፡ የሃይማኖታችሁን ጉድለት፤ ኀዘናችሁንና ችግራችሁን አትዘርዝሩ፤ ፈታኙ የዚህ ዓይነት ቃላት ሲሰማ ደስ ይለዋል፡፡ የሠይጣን ኃይል ድል እንዲነሣን ምቹ ሆነን መኖር የለብንም፡፡ ስለ መጥፎ ነገር በምትነጋገሩበት ጊዜ እያከበራችሁት ነው፡፡ ስለኃይለኛነቱ በመነጋገር እጃችንን እንሰጠዋለን፡፡CLAmh 113.5

    በዚያ ፋንታ ከአምላክ ጋር የቀረበ ግንኙነት እንዲኖረን ስለ ታላቁ የእግዚአብሔር ኃይል እንነጋገር፡፡ ወደር ስለሌለው የክርስቶስ ኃይል ተናገሩ፤ ስለ ክብሩም ተወያዩ፡፡ የሰማይ ሠራዊት በሙሉ የእኛን መዳን ይፈልጋል፡፡ እልፍ አእላፋት የሆኑት የሰማይ መላእክት የመንግሥቱ ወራሽ የሆኑትን ቆመው ያገለግላሉ፡፡ ከክፉ ሁሉ ይጠብቁናል፤ ሊያጠፋን የሚቃጣውን የጨለማ ኃይል ሁሉ ይከለክሉልናል፡፡ በመንገዳችን ላይ እንኳ እንቅፋት ቢደቀንብን በየጊዜው የምናመሰግንበት ምክንያት እናጣለን እንዴ?CLAmh 114.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents