Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ቀላል የፊዚዮሎጂ ትምህርቶች

    ወላጆች ልጆቻቸው የፊዚዮሎጂን ትምህርት እንዲወዱ ከሕጻንነታቸው ሊያስጀምሯቸውና ሕጉንም ሊያስጠኗቸው ይገባል፡፡ የአእምሮ፣ የአካል የመንፈስ ሐይላቸውን እንዴት አድርገው መጠበቅ እንደሚገባቸው ችሎታቸውንም ለሌሎች መጠቀሚያና ለእግዚአብሔርም መከበሪያ እንዲያደርጉ ያስተምሯቸው፡፡ ይህ ዓይነት እውቀት ለወጣቶች በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ስለሕይወትና ጤንነት የሚያገኙት ትምህርት በትምህርት ቤት ከሚያገኙት የሳይንስ ዕውቀት የበለጠ ዋናነት አለው፡፡CLAmh 31.1

    ወላጆች ለኅብረተሰብ ከሚያደርጉት የበለጠ ሕይወታቸውን ለልጆቻቸው አገልግሎት ሊያውሉት ይገባል፡፡ ስለጤንነት ማወቅና ይህንንም ዕውቀት በሥራ ላይ ማዋል ይገባል፡፡ ልጆች አመዛዝነው የሚያስቡ እንዲሆኑ ማስተማር ይገባል፡፡ ልጆች ጤንነትንና ደስታን ለማግኘት ከፈለጉ የሥነ ፍጥረትን ሕግ መጠበቅ እንዳለባቸው ማስተማር ተገቢ ነው፡፡ ምንም እንኳን እንደሚፈለገው የመሻሻል ምልክት ባጭር ጊዜ ውስጥ ባይታይም በትዕግስትና ተስፋ ባለመቁረጥ ትምህርቱን መቀጠል ያስፈልጋል፡፡CLAmh 31.2

    ልጆች ገና ከሕጸንነታቸው ጀምረው ራሳቸው የመግታት ልምድ እንዲኖራቸው አስተምሯቸው፡፡ የሥነ ፍጥረትን ውበት እንዲወዱና የአእምሮና የአካል ኃይላቸውንም ለጠቃሚ ነገር የማዋል ልምድ እዲኖራቸው ማስተማር ይገባል፡፡ ትክከለኛ ጠባይና ሞራል እንዲኖራቸው አድርጎ ማሳደግ ይገባል፡፡ የዕለት ደስታን ለማግኘት ብቻ ሳይሆን ዘላለማዊ ጥቅም ላለው ዓላማ እንድንኖር የእግዚአብሔር እቅድ መሆኑን ልጆች ገና በለጋነታቸው መማር ይገባቸዋል፡፡ ተፈትኖ መውደቅ ደካማነትና ኃጢአት መሆኑን፤ ፈተናን ማሸነፍ ግን ጉብዝና መሆኑን እንዲያውቁ ማድረግ ነው፡፡ የዚህ ዓይነት ትምህርት በጥሩ መሬት ላይ እንደወደቀ ዘር ጥሩ ፍሬ ስለሚያፈራ የወላጆችን ልብ ያስደስታል፡፡CLAmh 31.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents