Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ለእግዚአብሔር ሁሉን ማስረከብ

    ዛሬም ጌታ ጴጥሮስን፤ ማቴዎስንና ዮሐንስን ለሥራው እንደጠራ ሁሉ እኛንም ይጠራናል፡፡ ልባችን በፍቅሩ ተነካ ለእርሱ ስንል ለተወሰነው ነገር ሁሉ ካሣ አንጠየቅም፡፡ የእርሱ የሥራ ባልደረባ በመሆናችን እንደሰታለን፤ በእርሱ እናምናለን እንጂ አንጠራጠርበትም፡፡ በእግዚአብሔር ከተመካን የግዴታንና ራስን የመካድን ትርጉም እናስተውላለን፡፡CLAmh 197.3

    አስተሳሰባችን በከፍተኛ ቁም ነገር ስለሚያዝ ለተራው ነገር ግድየለሾች እንሆናለን፡፡CLAmh 197.4

    የክርስቶስ ተከታዮች ነን የሚሉ ብዙዎች ራሳቸውን ለእግዚአብሔር አደራ ስለማይሰጡ የሽብርና የስጋት ኑሮ ይኖራሉ፡፡ የሚመጣውን ውጤት ስለሚጠራጠሩ ራሣቸውን ለእግዚአብሔር ሙሉ ለሙሉ አያስረክቡም፡፡CLAmh 197.5

    ዓለም ከደረሰበት መድረስ ስለሚሹ በልባቸው የሚጨነቁ አሉ፡፡ ዓለምን ማገልገል ድንግርግርን መርጠዋል፤ ዓለማዊ ልምዶችንም ሸምተዋል፡፡ ስለዚህ ጠባያቸው ይበላሻል ፤ ኑሮአቸው ይጎሳቆላል፡፡ የማያቋርጠው ጭንቀታቸው የመኖር ሀይላቸውን ያደክመዋል፡፡ ጌታችን ይህን ቀንበራቸውን አዋርደው እንዲጥሉት ይለምናቸዋል፡፡ በዚህ ፋንታ የእርሱን ቀንበር እንዲሸከሙ ይጠይቃቸዋል፡፡CLAmh 197.6

    “ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና” (ማቲዎስ 11፡30) ጭንቀት ዕውር ስለሆነ የወደፊቱ አይታየውም፡፡ የሱስ ግን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ሁሉንም ያያል፡፡ ማንኛውንም ችግር የሚያቃልልበት የራሱ ዘዴ አለው፡፡ “እግዚአብሔር በቅንነት የሚሄዱትን ከመልካም ነገር አያሳጣቸውም፡፡” (መዝሙር 84፡11) ፡፡CLAmh 197.7

    እኛ አናውቀውም እንጂ የሰማይ አባታችን እኛን የሚረዳበት ብዙ መንገድ አለው፡፡ ለእግዚአብሔር ሥራ ቅድሚያ ለሚሰጡት ሁሉ የከበደው ይቀልላቸዋል፡፡CLAmh 197.8

    ዛሬ ተግባርን አጠናቅቆ መገኘት ለነገው ፈተና ዝግጁ ያደርጋል፡፡ የነገውን ጭንቀትና ጥርጣሬ አንድ ላይ አስራችሁ ከዛሬው ተግባራችሁ ጋር መሸከም አትሞክሩ፡፡ “ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል፡፡” (ማቲዎስ 6፥34)CLAmh 198.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents