Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በሕይወት መጽሐፍ መጻፍ

    እናት አንዳንድ ጊዜ ሥራዋ ዋጋ የሌለው አገልግሎት ይመስላታል፡፡ ስለ ሥራዋም የሚገባትን ምስጋና አታገኝም፡፡ ያለባትን ችግርና ሰቀቀንም ብዙዎች አያውቁላትም፡፡ ቀኑን ሙሉ ከአንዱ ትንሽ ሥራ ወደ ሌላው ስትጣደፍ ትውላለች፤ ይህም ሥራ ትዕግሥትን፣ ራስ መግታትን፣ የሥራ ስልትን፣ ጥበብንና ፍቅርን ይጠይቃል፤ ይሁን እንጂ ትልቅ ሥራ አከናወንሁ ብላ አትኮራም፡፡ በቤት ውስጥ ሊሠራ የሚገባውን ሁሉ በትክክል ታካሒዳለች፤ አንዳንድ ጊዜ ብታዝንና ብትበሳጭም ለልጆችዋ የርኅራኄ ቃላት ትናገራለች፤ ሥራ እንዳይፈቱና እንዲደሰቱ እያደረገች በትክክለኛው መንገድ ትመራቸዋለች፡፡ ይህንም አድርጋ ብዙ እንደሠራች አይሰማትም፡፡ ይሁን እንጂ የሠራችው ትልቅ ነው፡፡ የሰማይ መላእክት ታታሪዋን እናት ይመለከታሉ፤ በየዕለቱም የምትሸከመውን ቀንበር ያውቃሉ፡፡ ስምዋ በዓለም የታወቀ አይሆንም ይሆናል ነገር ግን በበጉ መጽሐፍ ውስጥ ስምዋ ይጻፋል፡፡CLAmh 25.2

    ልጆችዋ መጥፎውን ነገር ለመቋቋም እንዲችሉ በምታስተምረው ታማኝ እናት ላይ በሰማይ ካለው ከእግዚአብሔር ዙፋን ብርሃንና ጸጋ ይወርድላታል፡፡ በዋናነት ከእርሷ ሥራ ጋር እኩል የሚሆን የለም፡፡ እንደ ሠዓሊ በሸራ ላይ የሚቀባ፤ እንደ ደንጊያ ጠራቢም በዕብነ በረድ ላይ የሚቀረጽ ነገር የላትም፡፡ እንደ ደራሲ ሐሳብን በቃላት ኃይል አትገልጽም፡፡ እንደ አዝማሪም ስሜትን በዜማ አትገልጽም፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሔር ርዳታ ሰው በእግዚአብሔር ምሳሌነት እንዲወጣ የማድረግ ችሎታ አላት፡፡CLAmh 25.3

    ይህን ኃላፊነት በማግኘትዋ የምትደሰት እናት የተሰጣትን ዕድል ከፍ አድርጋ ትመለከተዋለች፡፡ በጠባይዋም ሆነ በትምህርት አሰጣጥዋ ልጆችዋ በጣም ከፍ ያለ ዓላማ እንዲኖራቸው ለማድረግ ከልብዋ ትመኛለች፡፡ የራስዋን ችሎታ ለማሻሻልና ልጆችዋን በምታስተምርበት ጊዜ የአእምሮን ኃይል በትክክል ልትጠቀምበት እንድትችል በታማኝነት፤ በትዕግስትና በድፍረት ትጥራለች፡፡ በእያንዳንዱ እርምጃ ላይ “እግዚአብሔር ምን ብሏል” እያለች ከልብዋ ትጠይቃለች፡፡ ቃሉንም በትጋት ታጠናለች፡፡ በየዕለቱ ተግባርዋ የእውነተኛውን ሕይወት አርአያ ለመከተል እድትችል ዓይንዋን ከክርስቶስ አትለይም፡፡CLAmh 26.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents