Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ለእርዳታ የተዘረጋ እጅ

    ቤቶቻችን ፈተና ለደረሰባቸው ወጣቶች ሁሉ መከለያ ምሽግ መሆን አለባቸው፡፡ ብዙ ወጣቶች በመንታ መንገድ ላይ ቆመዋል፡፡ የሚደረግላቸው ወይም የሚነገራቸው ነገር ሁሉ በያዝነውም ሆነ በሚቀጥለው ሕይወት የት እንደሚደርሱ ይወስናል፡፡ ሰይጣን ያድማቸዋል፡፡ የሚያታልልባቸውን ነገሮች የሚያጭበረብሩና የሚያጓጉ ናቸው፡፡ በነዚህ ፈተናዎች የሚታለለውን ሁሉ እንኳን ደህና መጣህ ብሎ ይቀበለዋል፡፡ ቤተሰብ በማጣት ወይም በማይረባ ቤተሰብ ምክንያት ባካባቢያችን ወጣቶች ይበላሻሉ፡፡ በበራችን አጠገብ ወደ ጥፋት ይሄዳሉ፡፡CLAmh 11.4

    እነዚህ ወጣቶች ለእርዳታ የርኅራኄ እጅ ሊዘረጋላቸው ይገባል፡፡ ጥቂት የርኅራኄ ቃላት ቢነገራቸውና ትንሽ የእርዳታ መንፈስ ቢያሳዩአቸው የከበባቸው የፈተና ደመና በተነሳላቸው ነበር፡፡ የክርስቶስ ጣፋጭ ቃላትና የፍቅር መንፈስ የሚያሻቸውን ልቦች ከሰማይ በወረደ ሰራጭ ኃይል ለመክፈት ይቻላል፡፡ ወጣቶችን ብናፈቅራቸው፣ ወደ ቤታችን ብናድማቸውና የረዳትነትና የደስታ መንፈስ ብናሳያቸው ብዙዎች በደስታ ወደ ላይ ወደሚወስደው መንገድ በተመለሱ ነበር፡፡CLAmh 12.1

    እዚህ የምንኖረው ሕይወት አጭር ነው፡፡ በዚህ አለም የምናልፈው አንድ ጊዜ ብቻ ስለሆነ በሙሉው እንጠቀምበት፤ የሕይወት መመሪያ ለሆኑት መለኮታዊ ደንቦች ቤታችንና ልባችንን ብንከፍት ሕይወት ሰጪ ለሆነ ኃይል መተላለፊያ እንሆን ነበር፡፡ ድርቅ ለመታውም ሕይወት ሁሉ የፈውስና የውበት ምንጭ ከቤታችን ይፈልቅ ነበር፡፡CLAmh 12.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents