Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    13—የተመጣጠነ ምግብ

    በምግብ መሻሻል እናምናለን ለሚሉ ሁሉ ከልባቸው አሳቡን አይደግፉም፡፡ በአንዳዶቹ አስተሳሰብ የምግብን ይዞታ ማሻሻል አንዳንድ ለጤና ተስማሚ ያልሆኑትን የምግብ ዓይነቶች በማውገዝ ብቻ የተወሰነ ነው፡፡ ስለጤና ሕግ በሚገባ አልተረዱም፡፡ የምግብ ገበታቸው ለጤና ተስማሚ ባልሆኑ ምግቦች የተሞሉ ስለሆኑ ለክርስትና መሻትን መግዛት አርኣያነት ሊጠቀሱ አይበቁም፡፡CLAmh 67.1

    ሌሎች ደግሞ በራሳቸው አሳብ አርኣያ መሆን ሲፈልጉ በጣም ያበዙታል፡፡ ሌሎች ደግሞ ጠቃሚ የሆኑትን የምግብ ዓይነቶች ማግኘት ስለሚያዳግታቸው በአሰስ ገሰስ ከርሳቸውን ይሞላሉ፡፡ በሚመገቡበት ምግብ ውስጥ ለሰውነት የሚጠቅም አልሚ ንጥረ ነገር የለበትም፡፤ ጤናቸው ይጎሳቆላል፤ አገልግሎታቸው ይቀንሳል፤ ለምግብ መሻሻል ብለው የወጠኑት ፕሮግራም ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡CLAmh 67.2

    አንዳንዶች ደግሞ ለጤና የሚያስፈልግ ቀላል ምግብ ስለሆነ ባመራረጥና በዝግጅት መጨነቅ አያሻም ይላሉ፡፡ ስለዚህ በቂ ምግብ አይበሉም፤ ወይም የሚበሉት ምግብ እንደነገሩ በመሆኑ ጉዳት ይደርስባቸዋል፡፡CLAmh 67.3

    ስለ ምግብ መሻሻል ያላቸው ዕውቀት ጥራዝ ነጠቅ የሆኑ ሰዎች በአስተሳሰባቸውና ሌሎችንም ለማስረዳት በሚያደርጉት ጥረት ጭፍን ሙግት ናቸው፡፡CLAmh 67.4

    በራሳቸው ላይ የደረሰውን የጤና መታወክ በበመልከት ሌሎች የምግብን ደንብ መቀበል አሻፈረን ይላሉ፡፡CLAmh 67.5

    ነገር ግን የጤናን ደንብና የአመጋገብን ሥነ ሥርዓት በሚገባ የተረዱ ሰዎች ሁለቱንም ወገን አይከተሉም፡፡ በቁንጣን ወይም በችጋር አይጎዱም ማለት ነው፡፤ ምግባቸውን የሚመርጡት ለአፍ ጣፋጭ በመሆኑ ብቻ ሳይሆን ለአካል የሚሰጠውን ጥቅም ጭምር በማመዛዘን ነው፡፡CLAmh 67.6

    እግዚአብሔርንና ሰውን በደንብ ለማገልገል ብርታታቸውን በሚገባ መከባከብ ይፈልጋሉ፡፡ የምግብ ፍላጎታቸውን በማመዛዘንና በህሊናቸው ይቆጣጠሩታል፡፡ ስለዚህ አካላቸው ጤነኛ፤ አእምሯቸው አስተዋይ ይሆንላቸዋል፡፡ በቃል ሌሎችን ተከታይ ለማድረግ ባያስገድዱም በገቢር የሚገለጠው አርኣያነታቸው የበለጠ ምሥክር ይሆናል፡፤ እነዚህ ሰዎች መልካም ተደማጭነት ያገኛሉ፡፡CLAmh 67.7

    በምግብ ማሻሻል ደንብ ዘንድ የሚደገፍ አስተሳሰብ አለበት፡፡ አርእስቱ በሚገባ መጠናት አለበት፡፡ ለምን ከእኔ ጋር አይስማማም በማለት አንዱ ሌላውን መተቸት ተገቢ አይደለም፡፡ የሰውን ሁሉ የዕለት አኗኗር አንድ ለማድረግ ስለማይቻል ማንም ሰው ሁሉ እኔን መከተል ይገባዋል ሊል አይችልም፡፡ ሰው ሁሉ አንድ ዓይነት ምግብ ሊበላ አይችልም፡፡ ለአንዱ ጣፋጭና ተስማሚ የሆነው ምግብ ለሌላው የማይጥምና ጎጂ ሊሆን ይችላል፤ አንዳንዶች ወተት ሲጠሉ ሌሎች ይጋደሉበታል፤ (ከመጠን በላይ ይወዱታል) ፡፡ አንዳንዶች ሰዎች አተር፤ ባቄላ መብላት አይወዱም፤ ሌሎች ደግሞ ሆዴን አይሉም፡፡ (አያማቸውም)፡፡ አንዳንድ ሰዎች ጥራጥሬ ሲቀርብላቸው ይወዱ እንደሆነ ሌሎች ሰዎች አያስደስታቸውም፡፡CLAmh 68.1

    የምግብ መሻሻል ደንብ የማያቋርጥ ሊሆን ይገባል፡፡ የእንስሳት በሽታ እየበረከተ ሲሄድ የወተትና የእንቁላል ምግብነት አጠራጣሪ ይሆናል፡፤ በእነዚህ የምግብ ዓይነቶች ፋንታ ሌላ መጠነኛ ዋጋ ያላቸውና ለጤና ተስማሚ የሆኑ የምግብ ዓይነቶች መፈለግ ሊኖርብን ነው፡፡CLAmh 68.2

    ሰዎች የምግቡ ጣዕምና ጠቃሚነት ሳይቀንስ ያለ እቁላልና ያለ ወተት ምግብ እንዴት ማዘጋጀት እንደሚችሉ መማር አለባቸው፡፡CLAmh 68.3

    በጠቅላላ አነጋገር በቀን ሁለት ጊዜ ብቻ መብላት ለጤና ተስማሚ ሆኖ ተገኝቷል፤ በአንዳንድ አጋጣሚ ሦስተኛ መመገብ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ይኖራሉ፡፡CLAmh 68.4

    ሶስተኛ መመገብ የሚያስፈልግ ሆኖ ከተገኘ በቀላሉ መበላት አለበት፡፡ ደግሞም የምግቡ ዓይነት በሰውነት ውስጥ በቀላሉ የሚዋሀድ መሆን ያስፈልገዋል፡፡ ሾርባ፣ ብስኩት፣ በእህል የተፈላ ሻይ ለማታ ምግብነት ይስማማሉ፡፡CLAmh 68.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents