Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    24—የሰብአዊ ዘር አገልጋይ

    ጌታችን የሱስ ክርስቶስ ወደዚች ምድር የመጣ የሰውን ፍላጎት ለማሟላት ነበር፡፡ “እርሱ ድካማችንን ተቀበለ ደዌያችንም ሁሉ ተሸከመ፡፡” (ማቴዎስ 8፡17) ይህንንም ያደረገበት ምክንያት የሰውን ችግር በሙሉ ለማቃለል ነው፡፡ የኃጢአትን ቀንበር፤ ጉስቁልናንና በሽታን ሊያጠፋ መጣ፡፡ ሰውን ሙሉ ለማድረግ ቆርጦ የመጣበት ዓላማው ነበር፡፡ ጤናን፣ ሰላምን፣ የጠባይን ፍጽምና ሊሰጣቸው መጣ፡፡CLAmh 125.1

    የእርሱን እርዳታ የፈለጉት ሰዎች ፍላጎታቸውና ሁኔታቸው የተለያየ ቢሆንም ማንም የፈለገውን ሳያገኝ አልተመለሰም፡፡CLAmh 125.2

    ከእርሱ ዘንድ የሚፈውስ ኃይል ይፈስ ነበር፡፡ ሰዎችም የአካል፣ የአእምሮና የመንፈስ ጤና አገኙ፡፡ የመድኅንን ሥራ ጊዜና ቦታ አይወስነውም ነበር፡፡ ርኅራኄው ወሰን የለውም፡፡ የሚያስተምረውና የሚያክመው ሕዝብ ከመብዛቱ የተነሣ በኢየሩሳሌም ከተማ ለጉባዔው የሚበቃ ትልቅ ቤት አልተገኘም ነበር፡፡ ሜዳው፣ ኮረብታው፣ ምኩራቡ፣ እንደሆስፒታል ያገለግል ነበር፡፡ ባለፈበት ከተማና መንደር ሁሉ በበሽተኞች ላይ እጁን ሲጭንባቸው ይድኑ ነበር፡፡CLAmh 125.3

    መልእክቱን ለመቀበል ፈቃደኛ ለሆኑት ሁሉ የሰማይ አባታቸው ፍቅር በማረጋገጥ ያጽናናቸው ነበር፡፡ በየዕለቱ ወደ እርሱ የሚመጡትን ያገለግል ነበር፡፡ ማታ ማታ ቀን ለዕለት ጉርሳቸው ሲሠሩ የሚውሉትን ይጐበኝና ያስተምር ነበር፡፡CLAmh 125.4

    ክርስቶስ ሰው ለማዳን ከባድ ኃላፊነት ተጥሎበት ነበር፡፡ በሰዎች አሳብና አመራር ከፍተኛ ለውጥ ካልተደረገ የሰው ዘር በሙሉ እንደሚጠፋ አላጣውም፡፡ ይህ የዘወትር ሸክሙ ቢሆንም አድራጐቱን አመስግኖ የተቀበለለት ሰው አልነበረም፡፡ በልጅነቱ፤ በወጣትነቱና በጐልማሳነቱ ብቸኛ ነበር፡፡ ግን የሰማይ ሠራዊት አልተለየውም፡፡ በየቀኑ ፈተናና ችግር ያጋጥመው ነበር፤ በየዕለቱ ክፉ ነገር ይጋፈጠው ነበር፡፡ ሊያድናቸው በሚጥርላቸው ላይ ክፋት ያለው ኃይልም ተመለከተ፡፡ ቢሆንም አልተሸነፈም፤ ተስፋም አልቆረጠም፡፡CLAmh 125.5

    በማንኛውም ነገር ምኞቱን አሸንፎ ለመጣበት ተግባር ታጥቆ ቆመ፡፡ ሁሉን ነገር ለአብ ፈቃድ በማስገዛት ሕይወቱን አስረከበ፡፡ በልጅነቱ እናቱ ከሊቃውንቱ ጋር አግኝታው “ልጄ፤ ለምን እንዲህ አደረግህ” ብትለው ለሥራው ቁልፍ የሆነውን መልስ “የአባቴን ሥራ መሥራት እንዳለብኝ አታውቂምን” አለ፡፡ ሉቃስ 2፡48-49CLAmh 125.6

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents