Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    መታዘዝ የሕይወት መንገድ ነው

    የእግዘአብሔር ትዕዛዝ የሕይወት ጎዳና መሆኑ በግልጥ ይታወቅ፡፡ እግዚአብሔር የተፈጥን ሕግ ሲደነግግ በጭቆናና በክፋት አላወጣውም፡፡ “አታድርግ” የሚለው ማስጠንቀቂያ በሙሉ የሞራል ሕግ ቢሆን ወይም የሜዳዊ ሕግ ከተስፋ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ሕጉን ብንታዘዝ እንባረካለን፡፤ እግዚአብሔር ሕጉን እንድናከብር ባያስገድደንም ከክፉ አውጥቶ ወደ መልካም ሊመራን ይፈልጋል፡፡CLAmh 95.6

    ለእሥራኤል የተሰጡትን ሕጎች አተኩረን እንመልከታቸው፡፡ ስለ ዘወትር ኑሮአቸው እግዚአብሔር ግልጥና የማያዳግም መመሪያ ሰጥቷቸዋል፡፡ ለሥጋዊና ለመንፈሳዊ ጥቅማቸው የሚያገለግሉትን ደንቦች ዘርዝሮ አስተማራቸው፡፡ ቢታዘዙ “እግዚአብሔር በሽታን ሁሉ ከእናንተ ዘንድ ያርቃል” የሚል ተስፋ ሰጣቸው፡፡ (ዘዳ 6፡15)) “ዛሬ የምመሰክርላችሁን ቃል ሁሉ በልባችሁ አኑሩት፡፡ “ለሚያገኙት ሕይወት ለሥጋችሁ ሁሉ ፈውስ ነውና፡፡” (ዘዳ 32፡46፣ ምሳሌ 4፡22)CLAmh 95.7

    እግዚአብሔር በክርስቶስ አማካይነት ከተመደበልን የንጽሕና ደረጃ እንድንደርስ ይፈልጋል፡፤ ትክክለኛውን ነገር እንድንመርጥ፤ ከሰማይ መልእክተኞች ጋር እንድንተባበር፤ የመለኮትን አርኣያነት እንድንከተል የሚያስችሉንን ደንቦች እንድንከተል ይጠራናል፡፡CLAmh 96.1

    በተጻፈው ቃሉን በተፈጥሮ አማካይነት የሕይወትን ሥርዓት ገልጦልናል፡፡ እነዚህን ሥርዓቶች መማርና የአካልንና የመንፈስን ደኅንነት ለመጠበቅ ትእዛዙን በማክበር ከእርሱ ጋር መተባበር ተግባራችን ነው፡፡CLAmh 96.2

    ሰዎች የመታዘዝን በረከት በሙሉ ሊቀበሉ የሚችሉ በክርስቶስ ጸጋ አማካይነት መሆኑን ማወቅ አለባቸው፡፡ ሰው የእግዚአብሔርን ሕግ ሊጠብቅ የሚያስችለው ጸጋው ነው፡፡ ከፉ ልማድ መላቀቅ የሚችልም በጸጋው ነው፡፡ በትክክለኛው መንገድ ጸንቶ እንዲጓዝ የሚያስችለው ይህ ኃይል ብቻ ነው፡፡CLAmh 96.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents