Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    22—የገጠር ኑሮ ጥቅም

    ፈጣሪ ለመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን ያዘጋጀላቸው ቦታ ለጤና ተስማሚና አስደሳች ነበር፡፡ በቤተ መንግስት ውስጥ አላስቀመጣቸውም ነበር፤ ወይም ሰዎች ዛሬ ሊያገኙት የሚሻሙበትን ጌጣጌጥና ብልጭልጭ ነገር አልሰጣቸውም ነበር፡፡ ከተፈጥሮና ከሰማይ ቅዱሳን ጋር የቅርብ ግንኙነት እንዲኖራቸው አደረገ፡፡CLAmh 115.5

    እግዚአብሔር ለልጆቹ ባዘጋጀላቸው ቤት በየአቅጣጫው ቢዞሩ ለምለም ቅጠልና የተዋበ አበባ ይታይ ነበር፡፡ በመልካም ፍሬ የዘመሙ ዛፎች በየትም ነበሩ፡፡ በየቅርንጫፎቹ ወፎች ደስታ ጩኸት በማሰማት ቱርቱር ይሉ ነበር፡፤ በሥራቸው የምድር እንስሳት ያለፍርሃት ይዘሉ ነበር፡፡CLAmh 115.6

    አዳምና ሔዋን ባላደፈው ንጽህናቸው ሆነው በኤድን ውስጥ በሚያዩትና በሚሰሙት ይደሰቱ ነበር፡፡ እግዚአብሔር “የኤድንን የአትክልት ቦታ እንዲያበጁና እንዲኮተኩቱ ሥራ ሠጥቷቸው ነበር፡፡” ዘፍጥረት 2፡15፡፡ የየዕለቱ ሥራ ደስታና ጤና ይሰጣቸው ነበር፡፡ ቀኑ ቀዝቀዝ ሲል ፈጣሪያቸው ሲጎበኛቸው በደስታ ይቀበሉት ነበር፡፡ አምላክ በየቀኑ ያስተምራቸው ነበር፡፡ ለመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን እግዚአብሔር የመደበላቸው የአኗኗር ዘዴ ለእኛም ጠቃሚ ትምህርት አለበት፡፡CLAmh 115.7

    ምንም እንኳን ኃጢአት ጥላውን ቢያጠላ እግዚአብሔር ሰዎች በእጆቹ ሥራ እንዲደሰቱ አሁንም ይፈልጋል፡፡ እርሱ የደነገገልንን የአኗኗር ደንብ እንደተከተልን መጠን ያለብንን ችግር ያቃለልልናል፡፡ በሽተኞች ከተፈጥሮ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ሊኖራቸው ይገባል፡፡ የገጠር ኑሮና ተፈጥሮ ለበሽታ ታምር ይሠራሉ፡፡ የከተማ ግርግርና ሰው ሠራሽ ብልጭልጭ ለበሽተኛ ተጨማሪ በሽታ ይሆኑበታል፡፡ በጭስ፤ በመርዘኛ ጋዝ በበሽታ ተውሳክ የተሞላው የከተማ አየር በሽተኞችን በበለጠ ያደክማል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ በቤት ውስጥ የሚኖሩ በሽተኞች የታሠሩ ይመስላቸዋል፡፡ የሚጣደፉትን ብዙ ሰዎች፤ መንገዱን፣ ቤቶችን ብቅ ብለው ሲመለከቱ የጠራ ሰማይና የፀሐይ ጮራ፤ ሣር ወይም አበባ የማየት ዕድል አያገኙም፡፡ እንደዚህ ተዘግተው ሲውሉ በአሳብ በመዋኘት ችግራቸውንና ኀዘናቸውን ሲያሰላስሉ የጭንቀት ተገዥ ሆነው ይቀራሉ፡፡CLAmh 116.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents