Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    14—የቤተሰብ ልብሶች

    መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አለባበስ ይመክራል፡፡ “እንዲሁም ሴቶች በሚገባ ልብስ ከእፍረትና ራሳቸውን ከመግዛት ጋር ራሳቸውን ይሸልሙ፡፡ መልካም በማድረግ እንጂ በሹርባና በወርቅ ወይም በእንቁ ወይም ዋጋው እጅግ በከበረ ልብስ አይሸለሙ፡፡” (1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡9) ፡፡ ይህ አባባል በልብስ ከመጠን በላይ መሽቀርቀርና በቀለም ዓይነት ማምለክን፤ ወይም በብርና በወርቅCLAmh 69.7

    በአንገትና በጆሮ ጌጥ ማጌጥን ይከለክላል፡፤ በአለባበስና በጌጥ የሰውን ስሜትና ዓይን ለመማረክ የሚደረገው ማንኛውንም ጥረት እግዚአብሔር በቃሉ አውግዞታል፡፡ ልብሳችንም ዋጋው ውድ መሆን አያስፈልገውም፡፡CLAmh 70.1

    ገንዘብ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠን አደራ ነው፡፡ ጉጉታችንና የልባችን ኵራት የምናረካበት የግል መሣሪያችን አይደለም፡፤ ገንዘብ ለእግዚአብሔር ሰዎች የሚታደለው ለተራቡ ምግብ፣ ለታረዙ ልብስ እንዲሆን ነው፡፡ ለተጐሳቆሉት መጠገኛ፤ ለታመሙት መታከሚያ፤ ለምስኪኖች የወንጌል ማዳረሻ መሣሪያ ነው፡፡ ለታይታ የሚባክነውን ገንዘብ በሚገባ ብትሠራበት ያዘኑትን ሰዎች ሊያስደስት ይችላል፡፡CLAmh 70.2

    የክርስቶስን ኑሮ አስታውስ፡፡ ባሕርዩን ተመራመርና ራስህን በመካድ ለድርጊቱ ተባባሪ ሁን፡፡ የክርስቲያን ዓለም በተባለው አካባኪ የተራቡትን ለመመገብ፤ የታረዙትን ለማልበስ የሚበቃ ገንዘብ በጌጣጌጥና በውድ ልብስ ይባክናል፡፡ ድኆችንና የተቸገሩትን መርዳት የሚገባው ገንዘብ (በፋሽን) በታይታ ያልቃል፡፡ እነዚህ አጉል ድርጊቶች ለዓለም ወንጌል እንዳይዳረስ ይከለክላሉ፡፡ የክርስትና ትምህርት ሳያገኙ የሚሞቱ ብዙዎች ናቸው፡፡ በአገር ውስጥ ሆነ በውጭ አገር አሕዛብ ስለመዳን አልተማሩም፡፡CLAmh 70.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents