Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    21—የአእምሮ ስሜት

    በአካልና በአእምሮ መካከል ያለው ግንኙነት በጣም የጠበቀና የቀረበ ነው፡፡ አንዱ ሲጎዳ ሌላው ይሰማዋል፡፡ የአእምሮ ይዞታ ሰዎች ከሚጠብቁት በላይ ለጤና መሟላት ወይም መታወክ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ ኀዘን፣ ሲቃ፣ መከፋት፣ የሕሊና ወቀሳ፣ አለመተማመን፣ የኑሮን አቋም አቃውሰው የሕመምና የሞት ጠንቅ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡CLAmh 105.3

    በሽታ በአእምሮ ዘንድ የበለጠ ያስጊነት ስሜትን ያሳድራል፡፡ ብዙዎች ከመጥፎ ስሜታቸው የተነሣ ዕድሜ ልካቸውን ድውያን ሆነው የሚቀሩ አሉ፡፡ ብዙ ሰዎች ማንኛውም አጋጣሚ የበሽታ ጠንቅ ስለሚመስላቸው የፈሩት አይለቃቸውም፡፡ አንዳንዶች በፍርሃት ብቻ ሕይወታቸው ይቀጫል፡፡CLAmh 106.1

    ድፍረት፣ ተስፋ፣ ሃይማኖት፣ መተዛዘን፣ ፍቅር ጤናን አሟልተው ዕድሜ ይቀጥላሉ፡፡ የሚደሰት አእምሮ ሰላም ያለው መንፈስ ለአካል ጤናን፤ ለመንፈስ ሰላምን ይሰጣል፡፡ “ደስ ያላት ልብ መልካም መድኃኒት ናት፡፡” ምሳሌ 17፡29)CLAmh 106.2

    በሽተኛን ሲያስታምሙ (ሲያክሙ) የአእምሮ ይዞታው ችላ መባል የለበትም፡፡ የአእምሮ ይዞታው በሚገባ ከታሰበበት በሽታን ለመከላከል በጣም ይጠቅማል፡፡ በአንድ በኩል ደግሞ በምክር በኩል የሚደረገው የሕክምና ዘዴ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡CLAmh 106.3

    በዚህ ዓይነት ሳይንሣዊ ዘዴ የአንዱ አስተሳሰብ በሌላው ይዋጣል፤ (ይጨቆናል)፡፡ ደከም ያለ አስተሳሰብ ያለው የግል መብትና ማመዛዘን የተሻለ አስተሳሰብ ባለው ሰው ይነጠቃል፡፡ አንዱ ሰው የሌላውን ምርጫና ፈቃድ ይመራል፡፡ በዚህ ይዞታ አስተሳሰብ እንደሚለወጥ የጤና ይዞታ እንደሚሻሻል፤ በሽተኞች በሽታን ተቋቁመው እንደሚያሸንፉ የሚያምኑ አሉ፡፡CLAmh 106.4

    የዚህን ዓይነት የሕክምና ዘዴ የሚሠሩበት ውጤቱንና መድረሻውን ያልተረዱ፤ በሽተናው ይጠቅማል ብለው የሚያስቡ ናቸው፡፡ ግን ይህ በስመ ሳይንስ የሚጠራ የሕክምና ዘዴ የተሳሳተ መሠረተ ሐሳብ የያዘ ነው፡፡ በክርስቶስ ዘንድ ያልተደገፈና ለእርሱ ባዕድ የሆነ ነው፡፡ ሕይወትና መድኅን ወደሆነው ወደ እርሱ አያደርስም፡፡ የሰዎችን አስተሳሰብ ወደራሱ የሚስብ ሰው እውነተኛ ብርታትን ሰጭ ከሆነው ከክርስቶስ ያርቃቸዋል፡፡CLAmh 106.5

    አንድ ሰው የግል የማሰብና የማመዛዘን መብቱን ለሌላው እንዲያስረክብ እግዚአብሔር አይፈቅድም፡፡ የሌላው መሣሪያ እንዲሆንም አይፈልግም፡፡ የአንዱ ግለሰብነት በሌላው እንዲዋጥ አይፈቅድም፡፡ ሰው ሰውን የመዳን ምንጭ አድርጎ አይመለከተውም፡፡ ሙሉ ዕምነቱን በእግዚአብሔር ላይ ይጣል፡፡ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠውን የሰብአዊነት ክብር ለእግዚአብሔር ያስገዛ፡፡ ለሰው ጥበብና ዕውቀት አይስገድ፡፡CLAmh 106.6

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents