Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    “ሕጻናትን አትከልክሏቸው”

    እነዚያ እናቶች የገረጡ፣ የደከሙ፣ ያዘኑ ቢሆኑም ቆራጦችና የማይሰለቹ ነበሩ፡፡ የመከራ ቀንበራቸውን እንደተሸከሙ መድኃኒታቸውን ይፈልጉ ነበር፡፡ ከጉባዔው በስተኋላ ስለሆኑ የሱስ ቀስ በቀስ ተጉዞ ከአጠገባቸው ይገኛል፡፡ ልባቸው በደስታና በተስፋ ሞቅ ይላል፡፡ ሲያዩት የደስታ እንባ ይተናነቃቸዋል፡፡ በኀዘንና በርኅራኄ ሲያያቸው ልባቸው ተነካ፡፡CLAmh 135.1

    ከጉባኤው መካከል አንዷን ለይቶ ጠርቶ “ምን ላድርግልሽ” ይላታል፡፡ የልቧን ፍላጎት በጋለ ስሜት በመግለጥ “ጌታ ሆይ ልጄን አድንልኝ” ትለዋለች፡፡ የሱስ ሕፃኑን ከእናቱ ተቀብሎ ሲዳብሰው በሽታው እንዳልነበረ ይሆናል፡፡ የሞት ጥላ ከእርሱ ይሸሻል፡፡ የሕይወት ጅረት በደም ሥሩ ይመላለሳል፡፡ ጡንቻዎቹ ይበረታሉ፡፡ እናትየዋን የሰላምና የተስፋ ቃል ነግሮ ይሸኛታል፡፡ ወዲያው ደግሞ ጊዜ የማይሰጥ በሽታ የያዘው ሕፃን ይቀርብለታል፡፡ ክርስቶስ እንደገና ሕይወት ሰጭ የሆነ ኃይሉን በሥራ ላይ ያውለዋል፡፡ ይህን ግሩም ሥራ የሚያከናውነውን ክርስቶስ ሁሉም ያከብሩታል፤ ያመሰግኑታልም፡፡CLAmh 135.2

    ሁላችንም የምንኖረው በክርስቶስ ታላቅ የሕይወት ፈለግ ነው፡፡ የሠራቸውን ድንቅ ነገሮችና የፈጸማቸውን ታምራት እንናገራለን፡፡ ግን ጥቃቅን የተባሉትን ነገሮች ንቆ አለማለፉ ለታላቅነቱ የበለጠ ማስረጃ ነው፡፡CLAmh 135.3

    ደቀመዛሙርቱ ግን መድኃኒታችን ብዙ ጠቃሚ ሥራ ስለሚሰራ ሕፃናትን በመቀበል ጊዜ እንዳያባክን አሰቡ፡፡ እናቶች ሕፃናትን ለማስባረክ ሲመጡ በመልካም ዓይን አልተመለከቷቸውም፡፡ ሕፃናቱ ከየሱስ ዘንድ በረከት ለመቀበል ያልበቁ መስለው ስለአዩአቸው የሱስ ወደ እርሱ እንዲቀርቡ የማይፈቅድ መሰላቸው፡፡CLAmh 135.4

    ክርስቶስ ግን ልጃቸውን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ለማሳደግ ለሚፈልጉት እናቶች ጭንቀትና ሸክም ተሰማው፡፡ ጸሎታቸውን ሰምቷል፡፡ ራሱ ወደ እርሱ እዲቀርቡ ጋብዟቸው ነበር፡፡CLAmh 135.5

    አንዲት እናት የሱስን ለማግኘት ብላ ልጅዋን ይዛ ከቤቷ ወጣች፡፡ በመንገድ ነገሩን ለጎረቤቶቿ ስለገለጠች የእርሷን አርኣያነት ተከትለው ወደ እርሱ መጡ፡፡ ብዙ እናቶች ከልጆቻቸው ጋር መጡ፡፡ አንዳንዶቹ ልጆች ከሕፃንነት ዕድሜአቸው አልፈው ወደ ወጣትነት ደረጃ ተቃርበው ነበር፡፡ እናቶች ሲጠይቁት በዓይነ አፋርነትና በፍርሃት የለመኑትን ልመና በርኅራኄና በአዛኝነት ተቀበላቸው፡፡ ግን የደቀመዛሙርቱን አስተያየት ለማወቅ ይጠባበቅ ነበር፡፡ ደቀመዛሙርቱ እናቶችን እየገፈተሩና እየገላመጡ ከእርሱ ሲመልሷቸው የረዱት መስሏቸው ነበር፡፡ ግን ስህተት መሥራታቸውን “ሕፃናትን ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ተዉ አትከልክሏቸው የእግዚአብሔር መንግስት እደነዚህ ላሉት ናትና” ብሎ በመገሰጽ አስታወቃቸው፡፡ ልጆችን አቀፋቸው፡፡ እጆቹን በራሳቸው ላይ ጭኖ ባረካቸው፡፡CLAmh 135.6

    እናቶች በጣም ተደሰቱ፡፡ በክርስቶስ ቃል በርትተውና ተባርከው ወደየቤታቸው ተመለሱ፡፡ ሸክማቸውን ለመሸከም ቻሉ፡፡ ልጆቻቸውንም በተስፋ ማሳደግ ቀጠሉ፡፡CLAmh 136.1

    እነዚያ ሰዎች ከዚያ በኋላ የኖሩት ኑሮ ቢገለጥልን እናቶች ለልጃቸው ያችን ታሪካዊት ጊዜ ሲያስታውሱአቸውና የሱስ የተናገራቸውን ክቡር ቃላት ሲደጋግሙላቸው በተመለከትን ነበር፡፡ የእነዚህ ክቡር ቃላት መሪነት ወጣቶችን ለዳኑት ከተዘጋጀው መንገድ እንዳይወጡ ረዳቸው፡፡CLAmh 136.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents