Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የፈጣሪነት ኃይል

    የበሰበሰውን አካል ጤና ማልበስ የፈጣሪነትን ኃይል ይጠይቃል፡፡ ሰውን ከአፈር የፈጠረው ያው ድምጽ ለድውይም ጤና አስገኘ፡፡ በፍጥረት ጊዜ “ሲናገር የሆነለት” ሲል ጸንቶ የቆመለት ” (መዝሙር 39፡9) በሃጥያት ምክንያት የተበላሸውን አካል ፈወሰው ፡፡ የአካሉ መፈወስ የሰውየውን ልብ መታደስ ያመለክታል ፡፡ ክርስቶስ ድውዩን “የሰው ልጅ በምድር ላይ ኃጢያት ማስተስረይ መቻሉን ያውቁ ዘንድ ተነሳና ሂድ” አለው፡፡CLAmh 156.2

    ድውዩ ከክርስቶስ ዘንድ መንፈሳዊና ስጋዊ ፈውስ አገኘ፡፡ አካሉ ከመዳኑ በፊት የመንፈስ ጤንነት አስፈልጎት ነበር፡፡ የስጋዊ ፈውስ ከመገኘቱ በፊት የአእምሮና የመንፈስ ደሕንነት ያሻል፡፡ ይህ ትምህርት ሊታለፍ አይገባውም፡፡ ዛሬ እንደ ድውዩ “ተነሳና አልጋህነ ተሸከመህ ሂድ ” መባል የሚወዱ ብዙ በሽተኞች አሉ፡፡CLAmh 156.3

    የበሽታው ስር ከኃጢያትና ከምኞት የተነሳ አለማረፍና መቅበጥበጥ ነው፡፡ የነፍስ አዳኝ የሆነው ካልቀረባቸው አይገላገሉም፡፡ ከአርሱ ዘንድ የሚገኘው ሰላም ለመንፈስ እረፍትን ፤ ለአካል ብርታትን ይሰጣል፡፡CLAmh 156.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents