Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በእግዚአብሔር ብርታት መመካት

    የወደፊቱን አክብደን በመጠባበቅ፤ አጨልመን በመመልከት ልባችንን አናድክመው፤ ጉልበታችንን ብርክ አናስይዘው፤ እጃችንን አናዝለው፡፡ ኃያሉ አምላክ “ጉልበቴን ይያዝ፤ ጌልበቴን ይያዝ፤ ከእኔ ጋር ሰላም ያድርግ፤ ከእኔ ጋር ሰላም ያድርግ” ይላል፡፡ (ኢሣይያስ 27፡5)፡፡ ሕይወታቸውን ለእርሱ ያስረከቡና በቅን ልቦና የሚያገለግሉት ጠባቂነቱ አይለያቸውም፡፡ ቃሉን ፈጻሚዎች ከሆንን የመጣ ቢመጣብን በመንገዳችን ሁሉ የሚመራን መሪ አለን፡፡CLAmh 111.3

    ምንም ቢደናገረን የታመነ አማካሪ አለን፡፡ ምንም ዓይነት ብቸኛነት ኀዘንና ትካዜ ቢያጋጠመን አዛኝና ርኅሩኅ ወደጅ አለን፡፡CLAmh 111.4

    ባለማወቅ ብንሳሳት አዳኛችን አይተወንም፡፡ ብቻችንን ነን ብለን መስጋት አያሻንም፡፤ የመላዕክት ባልደረቦች አሉን፡፡ ክርስቶስ በእርሱ ፋንታ እልከዋለሁ ብሎ ቃል የገባልን አጽናኝ ከእኛ አይለይም፡፡ ወደ እግዚአብሔር ከተማ በሚመራው ጐዳና ላይ ያሉትን እንቅፋቶች ሁሉ በእርሱ የሚያምኑ ሁሉ አይሰናከሉባቸውም፡፡ ከአደጋ ሁሉ ማምለጥ ይችላሉ፡፡ እርሱ መፍትሄ የማያገኝለት ኀዘን፣ ትካዜ፣ ሰብአዊ ጉድለት የለም፡፡CLAmh 111.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents