Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ለራሴ የማይል ኑሮ

    ሁልጊዜ ለእኔ በማይል የኑሮ ፈር ይመራ ነበር፡፡ ወዳጆቹ በእንግድነት መልክ ይቀበሉት ነበር እንጂ ቤት አልነበረውም፡፡ በእኛ ፈንታ ሊደኸይ መጣ፤ ከችግረኞችና ሥቃይ ከደረሰባቸው ጋር ይኖር ነበር፡፡CLAmh 126.1

    ደግ በሠራላቸው ሰዎች መካከል ሲወጣና ሲገባ ሳይታወቅና ሳይከበር ኖረ፡፡ ታጋሽና ደስተኛ ስለነበር፤ የተቸገሩት የሕይወትና የሰላም መልዕክተኛ ይሉት ነበር፡፡ የወንዶችና የሴቶች፤ የአዋቂዎችና የልጆች ችግር ይገባው ነበር፡፡ ሁሉንም “ወደእኔ ኑ” እያለ ይጋብዛቸው ነበር፡፡CLAmh 126.2

    ክርስቶስ በአገልግሎት ዘመኑ ከስብከት ይልቅ በሽተኞችን በመፈወስ የበለጠ ጊዜ ያሳልፍ ነበር፡፡ ታምራቱ ሊያድን እንጂ ሊያጠፋ አለመምጣቱን አረጋገጠለት፡፡ ባለፈበት ሁሉ የራራላቸው ሰዎች ሙሉ ባለጤና ሆነው አዲስ ያገኙትን ኃይል ሲሞክሩ ይታዩ ነበር፡፡ ጌታ የሠራውን ታምር ሲናገሩ ሕዝብ ተሰብስቦ ያዳምጣቸው ነበር፡፡ ብዙዎች መጀመሪያ የሰሙት የእርሱን ድምፅ፤ የተናገሩት ቃል የእርሱን ስም፤ የተመለከቱት የመጀመሪያ ነገር የእርሱ ፊት ነበር፡፡ ታድያ አይወዱትና አያመሰግኑት እንዴት ይሁኑ? በየከተማው ሲያልፍ ሲያገድም ሕይወትንና ደስታን የሚነዛ ኃይል ነበረው፡፡CLAmh 126.3

    “የዛቢሎን ምድር የንፍታሌም ምድር፤ የባሕር መንገድ በዮርዳኖስ ማዶ የአሕዛብ ገሊላ በጨለማ የተቀመጠው ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፤ በሞት አገርና ጥላ ለተቀመጡትም ብርሃን ወጣላቸው፡፡” (ማቴዎስ 4፡15፣16) ፡፡ መድህን ሰውን በሚፈውስበት ጊዜ መለኮታዊን መመሪያ በተፈዋሹ አእምሮና ልቦና ውስጥ ይመሠርት ነበር፡፡CLAmh 126.4

    የሥራው ዓላማ ይህ ነበር፡፡ የጸጋውን ወንጌል ሰዎች እንዲቀበሉ ምድራዊ በረከትን አጐናጸፋቸው፡፡CLAmh 126.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents