Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የምንኖረውና የምንቀሳቀሰው በእረሱ አማካይነት ነው

    የሰብአዊ አካል አሠራር በዝርዝር ሊስተዋል አይችልም፡፡ አዋቂ ነኝ የሚለውን ሁሉ የሚያስደንቅ ምስጢር ያዘለ ነው፡፡ አንዴ ካስተካከሉት ዝም ብሎ ያለማቋረጥ ሲሠራ የሚኖር መኪና አይደለም፡፡ የምንኖረው፤ የምንቀሳቀሰው በእግዚአብሔር ኃይል ነው፡፡ የልባችን ትርታ፣ የደም ሥራችን መርጨት፣ በሕያው አካላችን ውስጥ ያለው ሕዋሳትና ጡንቻ በሙሉ ምን ጊዜም በማይለየን በእግዚአብሔር ተቈጣጣሪነት ይኖራል፡፡CLAmh 173.8

    መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር በቅዱስ ዙፋኑ ላይ የተቀመጠው በሥራ ፈትነትና በብቸኝነት አለመሆኑን ይገልጥልናል፡፡ እልፍ አላፋት ቅዱሳን አገልጋዮች በዙሪያ ሆኖው ትዕዛዙን ይጠባበቃሉ፡፡ በእነዚህ መልዕክተኞች አማካይነት በግዛቱ ሁሉ ላይ የማያቋርጥ ግንኙነት አለው፡፡ በመንፈሱ በየትም የት ይገኛል፡፡ በመላዕክቱና በመንፈሱ አማካይነት የሰውን ዘር ሁሉ ያገለግላል፡፡CLAmh 173.9

    ከምድር ከፍ አድርጎ ዙፋኑን ዘርግቷል፡፡ ከመለኮታዊ ዕውቀቱ የሚሠወር ነገር የለም፡፡ በዘለዓለማዊ ሥልጣኑ ለዓለም የሚበጀውን ነገር በቅድሚያ ያዘጋጃል፡፡CLAmh 174.1

    “አቤቱ የሰው መንገድ ከራሱ እንዳይደለ አውቃለሁ፡፡ አካሄዱንም ለማቅናት ከሚራመድ ሰው አይደለም፡፡” (ኤርሚያስ 10፡23)CLAmh 174.2

    ” እነሆ፤ የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደሚፈሩት ናቸው፡፡ በምህረቱም ወደሚታመኑ፤ ነፍሳቸውን ከሞት ያድን ዘንድ፤ በራብም ጊዜ ይመግባቸው ዘንድ “(መዝሙር 30፡18-19)CLAmh 174.3

    “አቤቱ ምህረትህ በምድር ሁሉ ሞላች ሥርዓትህን አስተምረኝ፡፡ ጽድቅና ፍርድን ይወዳል የእግዚአብሔር ቸርነት ምድርን ሞላች ፡፡ ቤተ መቅደስህ ቅዱስ ነው፤ በጽድቅም ድንቅ ነው፡፡ በምድር ዳርቻ ሁሉና በሩቅ ባህር ውስጥ ላሉ ተስፋቸው የሆንህ አምላካችንና መድኃኒታችን ሆይ ስማን፡፡ በጉልበትህ ተራሮችን አፀነሃቸው፡፡ በኃይልም ታጥቀሃል፡፡ የባህሩን ጥልቀት የሞገዱንም ጩኸት ታናውጣለህ፡፡” መዝሙር (119፡64፤ 33፡5-7) ፡፡CLAmh 174.4

    ” እግዚአብሔር በቃሎቹ የታመነ ነው፡፡ በሥራው ሁሉ ጸድቅ ነው፡፡ እግዚአብሔር የተፍገመገሙትን ሁሉ ይደግፋቸዋል፡፡ የወደቁትንም ያነሣቸዋል፡፡ የሁሉ ዓይን አንተን ተስፋ ያደርጋል፡፡ አንተም ምግባቸውን በየጊዜው ትሰጣቸዋለህ፤ አንተ እጅህን ትከፍታለህ፤ ህይወት ላለውም ሁሉ መልካምን ታጠግባለህ፡፡ “(መዝ 145፡14-16)CLAmh 174.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents