Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ክርስቶስ ድል እንደነሣ ድል መንሣት

    አስተሳሰባችን በእግዚአብሔር መመራት ይገባዋል፡፡ የተፈጥሮአችንን ክፉ ዝንባሌ ለማስወገድ ከልባችን መጣር አለብን፡፡ ጥረታችን፤ ራሳችን መካዳችንና ትጋታችን ልናገኝ የምንፈልገውን ዋና ነገር ሊያስገኝ የሚችል መሆን አለበት፡፡CLAmh 182.1

    ክርስቶስ ድል እንደነሳ ድልን ስንቀዳጅ ብቻ አክሊል ልንጭን እንችላለን፡፡CLAmh 182.2

    ሰው ከአደጋ ላይ ሊወድቅ የሚችል ራሱን ሲያታልል ፤ በራሱ ሲመካና የኃይል ሁሉ ምንጭ የሆነውን እግዚአብሔር ችላ ብሎ ከአምላክ ሲለይ ነው፡፡CLAmh 182.3

    የተፈጥሮ ዝንባሌያችን በመንፈስ ቅዱስ መካሪነት ካልታረመ በቀር የሞራል ውድቀትን ያስከትላል፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር የጠበቀ ግንኙነት ካልኖርን በቀር ራስን መውደድን፤ በአጉል ደስታ መታለልን፤የኃጢአትን ፈተና ልንቋቋም አንችልም፡፡CLAmh 182.4

    ክርስቶስ እንዲረዳን ከፈለግን ጉድለታችን መገንዘብ አለብን፡፡ ማንነታችንን በሚገባ ማወቅ ይኖርብናል፡፡ ክርስቶስ ሊያድነው የሚችል ማንነቱን የተረዳውን ኃጢአተኛ ብቻ ነው፡፡ በመለኮታዊ ኃይል ሙሉ ዕምነት መመካትን ስንተው ነው፡፡CLAmh 182.5

    በራሳችን መመካትን መተው የሚገባን ክርስትናን ወዲያው እንደ ጀመርን ብቻ አይደለም፡፡ በሞላው የክርስትና ሕይወታችን ሊቀጥል ይገባዋል፡፡ መልካም ሥራ ልንሠራ የምንችለው እኔ ብርቱ ነኝ የሚለው የትዕቢት ስሜት ከአሳባችን ሲፋቅ ነው፡፡CLAmh 182.6

    ስለዚህ ከልባችን ሁል ጊዜ እግዚአብሔርን መሻት አለብን፤ ኃጢአታችንን በመናዘዝም በትህትና ወደ እርሱ እንቅርብ፡፡ መከራና ጭንቅ ከቦናል፡፡ ከጭንቅ ልናመልጥ የምንችል ድካማችን ተገንዝበን ኃይሉን መድኀናችንን በሃይማኖት ስንጨብጠው ነው፡፡CLAmh 182.7

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents