Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ከፍተኛ የአእምሮ እድገት

    ወጣቶች ከፍተኛ የአእምሮ እድገት ለማግኘት መጣራቸው ተገቢ ነው፡፡ እግዚአብሔር ያልወሰነውን ትምህርት እኛ አንወስንም፡፡ ነገር ግን ትምህርታችን ለእግዚአብሔር ክብርና ለሰው ዘር ጥቅም ካልሆነ ዋጋ የለውም፡፡CLAmh 48.4

    የዕለት ኑሮ በሚያሻሽል እውቀት አእምሮን ማጨቅ ተገቢ አይደለም፡፡ የዚህ ዓይነት ትምህርት ለተማሪው የጊዜ ማጥፊያ ነው፡፡ የዚህ ዓይነት ጥናት ጠቃሚ ሊያደርጉት የሚችሉትን ነገሮች የማጥናት ምኞቱን ይቀንሳል፡፡ የተግባረ እድ ትምህርት ከማንኛውም የቃል ትምህርት ይበልጣል፡፡ ማወቅ ብቻውን በቂ አይደለም፡፡ ዕውቀትን በትክክል ለመጠቀም መቻል አለብን፡፡CLAmh 48.5

    ብዙዎች ለማይጠቅም ትምህርት የሚያጠፉት ጊዜና ገንዘብ የሕይወትን ቀንበር ለመሸከም የሚያስችል የሥራ ልምድ ላለበት ትምህርት ሊጠቀሙበት ይገባል፡፡ የዚህ ዓይነት ትምህርት እጅግ በጣም ከፍ ያለ ዋጋ አለው፡፡CLAmh 48.6

    አእምሯችንን የሚያጠናክርና በጠቅላላው የሚያሻሽለን ዕውቀት ያስፈልገናል፡፡ የልብ ትምህርት ከማንኛውም የመጸሐፍ ሽምደዳ የተሻለ ነው፡፡ ስለምንኖርበት ዓለም ማወቅ ተገቢ ነው፤ ነገር ግን የዘላለምን ሕይወት ችላ ካልን ልናርመው የማንችል ስህተት ሠራን ማለት ነው፡፡CLAmh 48.7

    አንድ ተማሪ ዕውቀት ለማግኘት ሙሉ ኃይሉን ይጠቀምበት ይሆናል፤ ነገር ግን ስለ እግዚአብሔር ካላወቀና የሕይወቱን አስተዳዳሪ ሕጎች ካልታዘዘ ራሱን ያጠፋል፡፡ በመጥፎ ልምድ ምክንያት ራሱን የመግታት ኃይል ያጣል፡፡ በጣም ስለሚያስፈልጉት ነገሮች ትክክል ለማሰብ አይችልም፡፡ ስለ አእምሮውና አካሉ በቂ ጥንቃቄ አያደርግም፡፡ ትክክለኛውን የሕይወት ደንብ ባለመመሥረቱ ሕይወቱ ለዚህም ሆነ ለሚመጣው አለም ገጣሚ አይደለም፡፡CLAmh 49.1

    ወጣቶች የራሳቸው ደካምነት ቢረዱ ከእግዚአብሔር ብርታት ያገኙ ነበር፡፡ ከእርሱ ለመማር ቢፈቅዱ የእርሱ ጥበብ ይሰጣቸዋል፤ ሕይወታቸውም ለዓለም ጠቃሚ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ዓለማዊ ትምህርትን ብቻ የሚፈልጉና ከእግዚአብሔር የሚርቁ ከሆነ ሕይወትን የተሟላ የሚያደርጉትን ነገሮች አያገኙም፡፡CLAmh 49.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents