Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ሰብዓዊ መብትን ማክበር

    ጌታ የሱስ የያንዳንዱን ሰው መብት እንድናከብር ይጠይቀናል።የሰዎች የማኅበራዊ መብትና የክርስትና መብታቸውን ሊታወቅላችው ይገባል። የእግዚአብሔር ልጆች በመሆናችው ሰዎች ሁሉ ሊክበሩ ይገባል።CLAmh 204.2

    ክርስትና ሰውን ጨዋ ያደርገዋል። ክርስቶስ የሚያሳድዱትን ጭምር ያክብር ነበር። እውነተኛ ተከታዮቹም የእርሱን አርአያነት ይከተላሉ። ጳውሎስ “በባለስልጣናት ፊት ሲቀርብ እንዴት ነበር። በኣግሪጳ ፊት ያደርገው ንግግር አክብሮት የሞላበትና በሚገባ የተቀነባበረ ንግግር ነበረ።CLAmh 204.3

    ወንጌል ከልብ የመነጨውን እውነተኛ አክብሮትን እንጂ ዓለም ለይምሰል የሚደረገውን ትህትና አይደግፍም ።CLAmh 204.4

    የተዛባ ፍርድን፤ አጉል ንግግር፤ ክፋትን ለመከለል ለታይታ የሚደርገው መመጻደቅ አይጠቅምም።CLAmh 204.5

    ራስን ከፍ አድርጎ መገመት ካልቀረ እውነተኛ ጨዋነት በአንድ ሰው ዘንድ ቦታ አይገኝለተም ። ፍቅር በልብ ውስጥ ማንሰራራት አለበት።CLAmh 204.6

    የእውነተኛ ክርስቶስ ምግባር የሚመነጨው ጌታን ከልቡ በማፍቀር ነው። ክርስቶስን ከልቡ ያፈቀረ እንደሆን ለውንድሞች ራስን መስዋዕት በማድረግ መልካም አገልግሎት ያበረክታል።CLAmh 204.7

    ፍቅር ጨዋነትን፤ የጠባይ ጥረትን፤ ቅንነትን ያስከትላል። ገጽን ያበራል ድምጽን ያለዝባል፤ የሰውን ሁለንተና ከፍ ያደርጋዋል። ኑሮ የተጠናቀረው ከታላላቅ መሥዋዕትና ከአስገራሚ ጀብድ አይደለም። ግን ከጥቃቅን ነገሮች ነው። በሕይወታችን ደግሞ የሆነ ክፉ ነገር የሚጋጥመን ባልጠረጠርነው ትንሽ ሰበብ ነው። መጥፎ ዐመል የሚያድርብን፤ ጠባያችን የሚያጣምመው ልንነቅላቸውን በምንላቸው ትንንሽ ነገሮች አማይካነት ነው። ከዚያ በኃላ ከፍተኛ ፈተና ሳንታጠቅ ይደርስብናል። በጭንቅና በፈተና ጊዜ ድል ልንነሳ የምንችለው በየዕለቱ በሚገጥመን ተራ ፈተና የጸናን ሆነን ስንገኝ ነው።CLAmh 204.8

    ምን ጊዜም ብቻችን አይደለም፤ ብንመርጥም ባንመርጥም ባልደርባ አለን። ምንም ብትሰሩ የትም የት ብትሆኑ እግዚአብሔር ከዚያ መኖሩን አትርሱ። የሚባለው፤ የሚደርገው ሁሉ ከእግዚአብሔር ዘንድ አይሰወርም። የምትሰራውንና የምትናገረው ሁሉ ኃጢአትን የሚጸየፈው አምላክ ያያል፤ ይሰማልም፤ ከመናገርህ ወይም ከመስራትህ በፊት በነገሩ አሰብበት። ክርስቲያን ከሆንህ የሰማያዊ ንጉስ ልጅ ነህና የንጉሳዊ ቤተሰብ አባል ነህ። ስለዚህ “ያን የተጠራህበትን መልካም ስም” የሚያጎድፍ ርካሽ ስራ አትስራ። (ያዕቆብ 2፡7) ።CLAmh 205.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents