Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    10—ጤና ከቤተሰብ ይጀምራል

    ሥጋዊ አካልን የማፋፋት ዋና ዓላማ አካልን የእግዚአብሔር መቅደስና የክብሩ ማኅደር ለማድረግ መሆን አለበት፡፡ እግዚአብሔር አስገራሚ አድርጎ የሠራውን አካላችንን እንድናጠናው፤ የሚገባውን ነገር እንድናደርግለትና በተቻለንም መጠን ከሚጐዳውና ከሚያረክሰው ነገር እንድንጠብቀው ያዘናል፡፡CLAmh 49.3

    ጥሩ ጤና እንዲኖረን ከፈለግን ንጹህ ደም ሊኖረን ይገባል፤ ደምም የሕይወት ፈሳሽ ነው፡፡ የተበላሸውን ያድሳል፣ አካልንም ይመግባል፡፡ የሚያስፈልገውን ምግብ ከያዘና በንጹሕ አየር ከታደሰ ለእያንዳንዱ የአካል ክፍል ጥንካሬና ሕይወት ይሰጣል፡፡ የደም መዘዋወር ትክክል እንደሆነ መጠን ይህ ዓይነት ሥራ ደህና ይካሄዳል፡፡CLAmh 49.4

    በእያንዳንዱ የልብ ትርታ ደም ወደ አካል ሁሉ ክፍል መዳረስ አለበት፡፡ በሚያጠብቅ ልብስና እጅና እግርን በማራቆት ምክንያት የደም መዘዋወር መሰናከል የለበትም፡፡CLAmh 49.5

    የደምን መዘዋወር የሚያውክ ነገር ሁሉ ደሙ ወደ ዋና ብልቶች ተመልሶ እንዲጠራቀም ያደርጋል፡፡ በዚህም ምክንያት የራስ ምታት፣ ሳል፣ የልብ ቶሎ ቶሎ መምታት ወይም የምግብ አለመፈጨት ይከተላል፡፡

    ጥሩ ደም እዲኖረን ደህና አድርገን መተንፈስ አለብን፡፡ ሳንባን በሕይወት ደጋፊ አየር (ኦክስጅን) የሚሞላ አተነፋፈስ ደምን ንጹህ ያደርጋል፡፡ ይህም አየር ደምን ቀይ እንዲሆን ያደርግና ለአካል ክፍሎች ሁሉ ሕይወት ሰጭ ያደርገዋል፡፡ ንጹሕ አየር ነርቭን ያረጋጋል፣ የምግብ ፍላጎት ያሻሸላል፣ ምግብ በደንብ እንዲፈጭ ያደርጋል፣ እዲሁም ጥሩ እንቅልፍ ያስተኛል፡፡CLAmh 50.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents