Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የከተማ ኑሮ አደገኛነት

    በሞራላቸው ለደከሙ የከተማ ኑሮ አደገኛ ነው፡፡ የምግብ ፍላጎታቸውን መቆጣጠር የማይችሉ በሽተኞች በከተማ ውስጥ ከባድ ፈተና ይገጥማቸዋል፡፡ አስተሳሰባቸውን በሚለውጥ ባዲስ አካባቢ ውስጥ መኖር ይገባቸዋል፡፡ ሕይወታቸውን ካዛባው ነገር ተጽዕኖ ርቀው መኖር አለባቸው፡፡ ለጊዜው ከአምላክ ከሚለያቸው አጉል ቦታ ርቀው ንጹሕ በሆነ አካባቢ ይኑሩ፡፡CLAmh 116.2

    በሽተኞች የሚገለገሉባቸው ድርጅቶች ከከተማ ራቅ ብለው ቢቋቋሙ የበለጠ ይከናወንላቸው ነበር፡፡CLAmh 116.3

    ጤናቸው እንዲሻሻል የሚፈልጉ ሰዎች ሁሉ ንጹህ አየር በሚያገኙበትና እንደልባቸው በሚናፈሱበት የገጠር አካባቢ ይኑሩ፡፡ እግዚአብሔር ያዘጋጀልን ሐኪም ተፈጥሮ ነው፡፡ ንጹህ አየር፤ ብሩህ የፀሐይ ጮራ፤ ከቤት ውጭ የሚደረገው ያካል ማዳበሪ ልምምድ፤ ጤናን ያድሳሉ፤ ዕድሜን ያረዝማሉ፡፡CLAmh 116.4

    ሐኪሞች አስታማሚዎች በሽተኞቻቸው ወጣ እያሉ እንዲናፈሱ ማግባባት አለባቸው፡፡ ብዙ በሽተኞች ሊፈወሱ የሚችሉት ወጣ እያሉ በመናፈስ ነው፡፡ የገጠር ኑሮ በከተማ ጭንቅንቅ ኑሮ የተበደለውን የጤና ይዞታ የማሻሻል ችሎታ አለው፡፤ የከተማ ኑሮ ጭንቀት፤ የመብራቱ መብለጭለጭ፤ የከተማው ጩኸት ላጠቃቸው በሽተኞች የገጠሩ ጸጥታና ነፃነት ደስ ያሰኛቸዋል! የተፈጥሮን ትርኢት በጉጉት ይመለከታሉ! በነፋሻው ሜዳ ላይ ተቀምጠው የአበባውንና የሳሩን መዓዛ ሲጣርሙ ነፍሳቸው ትረካለች! የጥዱ፤ የዝግባውና የሌሎችም ዛፎች መዓዛ ሕይወትን ያድሳል፡፡CLAmh 117.1

    የዘወትር በሽተኛ ለሆነ ሰው ከገጠር ኑሮ የበለጠ ሕይወትን የሚያድስ ነገር የለም፡፡ በጣም በሽታ ያጠቃቸው ሳይቀሩ በዛፉ ጥላ መቀመጥ ወይም መጋደም ይችላሉ፡፡ የሚያዩት ሁሉ ለምለም ብቻ ነው፡፡ ነፋስ የሚያወዛውዘውን የቅርንጫፎች ድምፅ ሲሰሙ ሰላምና ብርታት ይሰማቸዋል፡፡ የወደቀው መንፈሳቸው ይነሣል፡፡ የቀነሰው ብርታታቸው ይታደሳል፡፡ ሳያስቡት በአእምሮአቸው ውስጥ ሰላም ይሰፍናል፡፡ ንዝረታቸው (ፐልስ) መደበኛ ሥራውን ይቀጥላል፡፡ በሽተኛው እየበረታ ሲሄድ አምላክ ለወደቁት ልጆች የላከላቸውን የፍቅር መግለጫ አበባዎች መቅጠፍ ይይዛል፡፡CLAmh 117.2

    በሽተኞችን ወደ ውጭ የማቆየት ፕሮግራም ሊዘጋጅ ይገባል፡፤ በመጠኑ መሥራት ለሚችሉ ቀላል ሥራ ይዘጋጅላቸው፡፡ የሥራን አስደሳችነትና ጠቃሚነት አስረዱአቸው፡፡ ንጹህ አየር እንዲተነፍሱ አደፋፍሩአቸው፡፤ በደንብ እንዲተነፍሱ ምከሩአቸው፡፡ በመተንፈስና በመሥራት የሆዳቸውን ጡንቻ እንዲያበረቱት አግባቡአቸው፡፡ በሽተኞች አበባዎችን ይኮትኩቱ፤ አትክልት ያሳድጉ፤ የአትክልት ቦታ ያበጃጁ፡፡ ከቤት ወጥተው አበባን ሲኮተኩቱና አትክልት ሲተክሉ (ስለራሳቸውና ስለ በሽታቸው ማሰላሰል ይተዋሉ) ፡፡ በሽተኛው ወደ ውጭ ሲወጣ የሚደረግለት ጥንቃቄ አይበዛም፡፡ በአካባቢው ያለው ነገር የሚያስደስት ከሆነ በልቡ ተስፋ ያድርበታል፡፡ በቤት ውስጥ ከዋለ ግን ምን በምቾት ቢያዝ ኀዘንና ትካዜ አይለየውም፡፤CLAmh 117.3

    በተፈጥሮ ውበት ከተከበበ ግን የአበባዎችን ውበት ካየና የወፎችን መዝሙር ከሰማ በሽተኛው የመዘመር ስሜት በልቡ ያድርበታል፡፡ ለአእምሮው ዕረፍት፤ ለአካሉ ብርታት ያገኛል፡፡ የማስተዋል ችሎታው ይዳብራል፤ አስተሳሰቡ ይታደሳል፡፡ አእምሮው የእዚአብሔርን ቃል ውበት ማድነቅ ይችላል፡፡CLAmh 117.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents