Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የተስፋ ቃላት

    የጌታ ደንብ መመሪያ በሚያደርጉ ሁሉ ዘንድ የተስፋው ቃላት የተከበሩ ናቸው፡፡CLAmh 71.9

    “ስለ ልብስ ለምን ትጨነቃላችሁ? እግዚአብሔር ዛሬ ያለውን ነገ ግን ወደ እቶን እሳት የሚጣለውን የሚዳን ሣር እንዲህ የሚያለብስ ከሆነ እናንተ እምነት የጎደላችሁ እናንተማ ይልቁንም እንዴታ? ይህ ሁሉ እንደሚያስፈልጋችሁ የሰማይ አባታችሁ ያውቃልና፡፡ ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግስት ጽድቁንም እሹ እንጂ ይህ ሁሉ ይጨመርላችኋል፡፡” (ማቴ 6፡28፣ 30-33)CLAmh 71.10

    “ባንተ ላይ ታምናለችና በአንተ ለምትደገፍ ነፍስ ፈጽመህ በሰላ ትጠብቃታለህ፡፡” (ኢሣይያስ 26፡3)CLAmh 72.1

    ከአለባበስ ዘይቤ ከሚመጣው መታከት፤ መጎሳቆልና ጤና ማጣት ጋር ሲመዛዘን ይህ ተስፋ እንዴት የራቀና የመጠቀ ነው! ዘመኑ የወለዳቸው የልብስ ይዞታዎች እግዚአብሔር ከደነገገው ሥርዓት እንዴት የራቁ ናቸው?CLAmh 72.2

    ባለፉት መቶ ዓመታት ወይም አሥር አመታት ውስጥ ይለበሱ የነበሩትን የልብስ ዓይነቶች ብታስተውሉ በፋሽን (አቢይ-መጥ) አስተያየት ካልሆነ በቀር ማነው ተስማሚ አይደሉም ብሎ የሚያወግዛቸው? እግዚአብሔርን ለሚያከብሩ ሴቶች ተገቢ አይደሉም የሚል ማነው?CLAmh 72.3

    ለፋሽን ብሎ የአለባበስን ዘይቤ መለዋወጥ በእግዚአብሔር ቃል የተደገፈ አይደለም፡፡ የጌጣጌጥ መብዛት የልብስ ዓይነት በየጊዜው መለዋወጥ የባለጸጋዎችን ገንዘብና ጊዜ ያባክናል፡፡ የመንፈስና የአእምሮ ኃይልም ይበዘብዛል፡፡ በተራው ሕዝብ ላይም ሸክምና ችግርን ይጭናሉ፡፡CLAmh 72.4

    ህጻናት ገና ከመወለዳቸው የፋሽን ተጽዕኖ ይይዛቸዋል፡፡ ስለ መድኅን ከሚሰሙት ይልቅ ስለ ልብስ የሚነገራቸው ይበዛል፡፡ እናቶቻቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ ይልቅ የፋሽኑን ሰንጠረዥ አዘውትረው ሲያነሱ ይመለከታሉ፡፡ ከጠባይ ማነጽ ይልቅ የልብስ ትርዒት ከፍተኛ ግምት ይሰጠዋል፡፡ ወላጆችና ልጆች የኑሮን ጣዕምና ለዛ፤ እውነተኛነቱንም ይነፈጋሉ (ይበዘበዛሉ)፡፡ በፋሽን ምክንያት ስለሚመጣው ዓለም ከመዘጋጀት ይታቀባሉ፡፡ (ይታገዳሉ)፡፡CLAmh 72.5

    ተለዋዋጭ የሆነውን የፋሽን ዘይቤ ያመጣ የእውነት ሁሉ ተቃዋሚ የሆነው የማይተኛው ጠላት ነው፡፡ ሰብአዊን ፍጡር በማሠቃየትና በማጥፋት እግዚአብሔርን ከማሳዘንና ከማዋረድ ሌላ የሚመኘው ነገር የለውም፡፡ ይህን ዓላማውን ከግብ የሚያደርስበት አንዱ መሣሪያው አካልን የሚያደክመው፤ አእምሮን የሚያቀጭጨው፤ መንፈስንም የሚያዋርደው ተለዋዋጩ ፋሽን ነው፡፡CLAmh 72.6

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents