Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ከልክ ያለፈ ምግብ

    አንዳንድ ሰዎች ምግባቸው ቀላልና ለጤና ተስማሚ ከሆነ ያለልክ መብላት የሚገባቸው መስሎ ይሰማቸዋል፡፡ ከመጠን በላይ ቁንጣን እስቲይዛቸው ይበላሉ፡፡ ይህ አደገኛ ስህተት ነው፡፡CLAmh 58.7

    ምግብ የሚያዋህደው የአካል ክፍል ሥራውን በሚያሰናክል የምግብ ዓይነት ወይም ብዛት መጎዳት የለበትም፡፡

    አንዳንድ ጊዜ ከመጠን በላይ መብላት ጉዳቱ ወዲያውኑ ይሰማል፡፡ በሌላ ጊዜ ግን ለጊዜው ሕመም ባይሰማም ምግብን የሚያዋህደው ክፍል ሲጎዳ የአካላችን ብርታት ይዛባል፡፡CLAmh 59.1

    ከልክ በላይ የሆነው ምግብ በሰውነት ላይ የበሽታንና የቅሬታን ስሜት ይፈጥራል፡፡ ወደ ሆዳችን ብዙ ደም እንዲፈስ በማድረግ ሌላው የሰውነት ክፍላችን እንዲቀዘቅዝ ያደርገዋል፡፡ ምግብን ለሚያዋህደው አካል ክፍል ተጨማሪ ሥራ ያስከትላል፡፡ እነዚህ የሰውነት ክፍሎች ተግባራቸውን ካከናወኑ በኋላ ሞላው የአካል ክፍላችን ይዝላል፡፡CLAmh 59.2

    ሁልጊዜ ከመጠን በላይ የሚበሉ ሰዎች የዚህን ዓይነት ስሜት ከረሀብ ይቆጥሩታል፡፡ ግን ስሜቱ የተፈጠረው ምግብ አዋሃጁ የአካል ክፍል ከሚገባው በላይ ስለሠራ ነው፡፡CLAmh 59.3

    በዚያን ጊዜ አእምሮ ይደንዛል፤ የጉልበትም ሆነ የአእምሮ ሥራ መሥራት አያስመኝም፡፡CLAmh 59.4

    ይህ ሁሉ ስሜት የሚመጣው ተፈጥሮ ከሕግ ውጪ ሥራዋን እንድታካሂድ ስለተገደደችና በጣም ስለደከመች ነው፡፡ ጨጓራ “እባካችሁ ልረፍ” ይላል፡፡ ብዙዎቹ ግን ድካሙን በምግብ ፍላጎት ስሜት ይተረጉሙታል፡፡ ስለዚህ ጨጓራን በማሳረፍ ፋንታ ተጨማሪ ሥራ ይጭኑታል፡፡ ስለዚህ የምግብ ማዋሀጃው ክፍል የሚጠበቅበትን ሥራ መሥራት ይሳነዋል፡፡CLAmh 59.5

    በሰንበት ቀን ከሌላው ቀን የተለየ ብዙና ልዩ ልዩ የምግብ ዓይነት ማዘጋጀት አያስፈልግም፡፡ እንዲያውም ምግቡ ከዘወትሩ የቀለለና መጠነኛ መሆን ይገባዋል፡፡ ይህም መደረግ ያለበት አእምሯችን መንፈሳዊ ነገርን ለማስተዋል እንዲችል ነው፡፡ ሆዳችን ከመጠን በላይ ከሞላ አዕምሯችን ተዘጋ ማለት ነው፡፡ ባልተገባ ምግብ አእምሯችንም ስለተወናበደ የከበሩትን ቃላት ሰምተን ማስተዋል ያቅተናል፡፡CLAmh 59.6

    በሰንበት ቀን ብዙ በመብላታቸው ብዙ ሰዎች ከሚያስቡት በላይ የሰንበትን በረከት ያጣሉ፡፡CLAmh 59.7

    ምግቡ ቀላል ቢሆንም ብሉኝ ብሉኝ የሚል ይሁን፡፡ እንዲያውም ልጆች ባሉበት ቤተሰብ እንደ አዲስ የሚቆጠር የምግብ ዓይነት ቢቀርብ መልካም ነው፡፡CLAmh 60.1

    መጥፎ ያመጋገብ ልምድ ያለበት ቤተሰብ ወይም ግለሰብ መጥፎ አመሉን ከማሻሻል ወደኋላ አይበል፡፡ ለሁሉ አጋጣሚ የሚበጅ ደንብ ማውጣት ችግር ነው፡፡ ግን የአመጋገብን ደንብ በሚገባ በማክበር ታላቅ መሻሻል ሊያደርግ ይችላል፡፤ ምግብ አዘጋጅዋ (አብሳይዋ) ሁልጊዜ የበላተኛውን የምግብ ፍላጎት የሚያስጎመጅ ምግብ ለመሥራት ጥረት ማድረግ የለባትም፡፡ አመጋገብን መቆጣጠር ለአካልና ለአእምሮ ብረታት ይሰጣል፡፡CLAmh 60.2

    ስሜታችን ለመቆጣጠርም ይረዳናል፡፡ ከመጠን በላይ መብላት በተለይ መሻታቸውን መግዛት ለማይችሉ ሰዎች ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል፡፡ የዚህ ዓይነት ሰዎች በመጠኑ እየበሉ ብዙ የአካል ማጠንከሪያ ልምምድ ያድርጉ፡፡CLAmh 60.3

    በተፈጥሮአቸው ግሩም ችሎታ እያላቸው አመጋገባቸው ያልተስተካከለ በመሆኑ ሊሠሩት ከሚገባቸው ግማሹን እንኳ የማያደርጉ ሴቶችም ወንዶችም አሉ፡፡CLAmh 60.4

    ብዙ ደራስያንና ተናጋሪዎች ጉድለታቸው እዚህ ላይ ነው፡፡ ከባድ ምግብ ከበሉ በኋላ የአካል ማጠንከሪያ ልምድ (የጉልበት ሥራ) በመሥራት ፋንታ እንደማንበብ፣ እንደመጸፍ የመሳሰሉትን የቅምጥ ሥራዎች ይቀጥላሉ፡፡ ስለዚህ የአሳብና ቃላት ምንጫቸው ይዘጋል፡፡ የሰዎችን አሳብ የሚነካ ጽሑፍ ለማዘጋጀት ወይም ንግግር ለማድረግ አይችሉም፡፡ ጥረታቸውና ድካማቸው ዋጋ ቢስ ይሆናል፡፡CLAmh 60.5

    ከባድ ኃላፊነት የተጣለባቸው ሰዎች በተለይም መንፈሳውያን መሪዎች የሰላ አስተሳሰብና ፈጣን የማስተዋል ችሎታ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ከዚያም በላይ በምግብ አበላላቸው መጠነኛ መሆን አለባቸው፡፡ የድሎትና የቅንጦት ምግብ በገበታቸው ላይ መታየት የለበትም፡፡CLAmh 60.6

    ኃላፊነት ያለባቸው ሰዎች ለታላላቅ ጉዳዮች ውሳኔ ይሳጣሉ፡፡ በቶሎ ማሰብ ስላለባቸው ይህን ማድረግ የሚችሉ የተስተካከለ የአመጋገብ ደንብ የተከተሉ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ የማሰብ ችሎታችን የሚጠነክረው ለአካላችንና ለአእምሯችን ተገቢ መከባከብ ያደረግን እንደሆነ ነው፡፡CLAmh 60.7

    የታወከ ሆድ የተዘበራረቀና ከሥርዓት ውጪ የሆነ አስተሳሰብ ያስከትላል፡፡ ብስጭትን፣ ጭካኔን፣ ከሕግ ውጭ መሥራትን ያስከትላል፡፡ በመጥፎ አመጋገብ ምክንያት፤ በታወከ ጤና ጠንቅ ለዓለም በረከት መሆን ይችሉ የነበሩ ዕቅዶች ችላ ተበለው ያልቀኑ የጭካኔ ተግባሮች ተካሂደዋል፡፡CLAmh 60.8

    የአእምሮና የቅምጥ ሥራ ለሚሰሩ ሰዎች ሁሉ ምክር እነሆ፤CLAmh 61.1

    ራሳቸውን መግዛት የሚችሉና በቂ የሞራል ድፍረት ያላቸው ሰዎች ይሞክሩት፡፡ በአንድ የምግብ ጊዜ ሁለት ወይም ሶስት ቀላል የምግብ ዓይነቶች ብቻ ተመገቡ፡፡ የምግብ ፍላጎታችሁ ጋብ ካለ መብላት አቁሙ፡፡ በየቀኑ የአካል ማጠንከሪያ ልምምድ አድርጉ፡፡ እስኪ ይህን አድርጋችሁ መጥቀም አለመጥቀሙን ሞክሩት፡፡CLAmh 61.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents