Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    እግዚአብሔር አካላዊ አቋም አለው

    እግዚአብሔር አካላዊ አቋም እንዳለው በወልድ አማካይነት ተገልጧል፡፡ የአብን ክብር ለመግለጥና “የባህርይው ምሳሌ ሆኖ” ክርስቶስ አዳኝ ሆኖ ወደ ዓለም መጣ፡፡ የግል አዳኝ በመሆን ወደ ሰማይ አረገ፡፡ አሁንም አዳኝ በመሆን በሰማይ ያማልዳል፡፡ “የሰው ልጅ የሚመስል ስለኛ በእግዚአብሔር ዙፋን ያገለግላል፡፡”CLAmh 174.6

    ክርስቶስ የዓለም ብርሃን ነፀብራቃዊና መለኮታዊ ክብሩን ጋርዶ በሰዎች መካከል ሰው ሆኖ ለመኖር መጣ፡፡ ይህንም ያደረገበት ምክንያት ሰዎች ጉዳት ሳይደርስባቸው ከፈጣሪያቸው ጋር እንዲተዋወቁ ነው፡፡CLAmh 174.7

    ኃጢአት ሰውንና እግዚአብሔርን ካፈራቀቀ ወዲህ በክርስቶስ አማካይነት በቀር ምንም ሰው ፊጣሪውን አላየም፡፡ በክርስቶስ አማካነት በቀር ማንም ሰው ፈጣሪውን አላየም ፡፡CLAmh 175.1

    ክርስቶስ “እኔና አብ አንድ ነን” አለ፡፡” ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፡፡ ከአብ በቀር ወልደን የሚያውያቅ የለም፡፡ “ከወልድም በቀር ወልደም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም” (ማቴዎስ 11፡27) ።CLAmh 175.2

    ክርሰቶስ ወደ ዓለም ሲመጣ እግዚአብሔር የሚፈልገውን ነገር ለሰብአዊ ፍጡር ሊያስተምር ነው፡፡ በላይ በሰማይ፤በውቅያኖሶች ላይ፤በመሬት ላይ የእግዚአብሔርን ሥራ እንመለከታለን ፡፡ ፍጥረት ሁሉ ኀይሉን ፤ፍቅሩን ፤ጥበቡን ይገልጣል ፡፡ ግን የእግኢአብሔርን ባሕርይ ክርስቶስ የገለጠልንን ያህል በከዋክብት፤ በውቅያኖስ ወይም በፏፏቴ አማካይነት ልናውቅ አንችልም፡፡CLAmh 175.3

    እግዚአብሔር ባሕርይውና አቋሙን ለሰዎች ለመግለጥ ከተፈጥሮ የበለጠ ሌላ መንገድ ማስፈለጉን አወቀ፡፡ የማይታየውን አምላክ ሁኔታ ለሰዎች የማስተዋል ችሎታቸው እሰከፈቀድላችው ድረስ ለመግለጥ ልጁን ወደ አለም ላከ፡፡CLAmh 175.4

    ክርስቶስ ከመስቀሉ በፊት በፎቁ ለደቀመዛሙሩቱ የተናገረውን እንመርምረው፡፡ የምርመራ ጊዜው እንደ ደረሰ ስላወቀ ፈተናና ችግር የተደቀነባቸውን ደቀመዛሙርቱን አጽናናቸው፡፡CLAmh 175.5

    “ልባችሁ አይታወክ በእግዚአሔር እመኑ በእኔም ደግሞ እመኑ ፡፡ በአባቴ ቤት ብዙ ሥፍራ አለ ፡፡ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር ፡፡ ሄጄም ሥፍራ አዘጋጅላቸወኋለሁ ፡፡CLAmh 175.6

    “ቶማስም ጌታ ሆይ የምትሄድበትን አናውቅም እንዴት መንገድን እናውቃለን” አለው፡፡ የሱስም እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ አለው፡፡ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም፡፡ እኔን ብታውቁኝ አባቴንም ደግሞ ባወቃችሁ ነበር፡፡ ከአሁንም ጀምሮ ታውቁታላችሁ፡፡ አይታችሁትማል አላቸው፡፡ “ፊልጶስ ጌታ ሆይ አብን አሳየንና ይበቃናል” አለው የሱስም አለው አንተ ፊልጶስ፤ ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቷል፡፡ እንዴትስ አንተ አብን አሳየ ትላለህ? እኔ በአብ እንዳለሁ እብም በአኔ እንዳለ እታምንምን? እኔ የምነግራችሁን ቃል ከራሴ አልናገርም። ነገር ግን በእኔ የሚኖረው አብ እርሱ ሥራውን ይሰራል፡፡” (ዮሐንስ 14፡1-3)CLAmh 175.7

    ደቀመዛሙርቱ አብና ወልድ ያላቸውን ግንኙነት በደንብ አላስተዋሉም ነበር፡፡ ያስተማራቸው ትምህርት ግልጥ አልሆነላቸውም ነበር፤ ክርስቶስ ስለ እግዚአብሔር የተብራራ ዕውቀት እንዲኖራቸው ፈለገ፡፡CLAmh 176.1

    “ይህን በምሳሌ ነግሬአችኋለሁ፤ነገር ግን ስለ አብ ለእናንተ በግልጥ የምናገርበት እንጂ ከዚያ ወዲያ በምሳሌ የማልናገርበት ጊዜ ይመጣል፡፡ (ዮሐንስ 16፡25) ፡፡CLAmh 176.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents