Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የባልና የሚስት መተማመን

    ባልዮው ሚስቲቱን፤ ሚስቲቱም ባልዮውን የሚያስደስታቸውን ነገር ማወቅና ሕይወትን አስደሳች የሚያደርጉትን ትንንሽ የከበሬታ የርኅራኄ ድርጊቶች መፈጸም ይገባቸዋል፡፡ በባልዮውና በሚስቲቱ መካከል ሙሉ መተማመን መኖር አለበት፡፡ ኃላፊነታቸውን አብረው መወያየት አለባቸው፡፡ ለልጆቻቸው የሚጠቅመውን ነገር ሁሉ በትብብር መፈጸም አለባቸው፡፡ ልጆቹ ባሉበት ቦታ እቅዳቸውንና አስተያየታቸውን መነቃቀፍ አይገባቸውም፡፡ እናቲቱ ባልዋ ለልጆቹ ያለውን ኃላፊነት ላለማክበድ ትጠንቀቅ፡፡ ባልዮውም ሚስቱን በመምከርና በማጽናናት ይርዳት፡፡CLAmh 35.4

    በወላጆችና በልጆች መካከል የቀዘቀዘ መንፈስና አለመግባባት መኖር የለበትም፡፡ ወላጆች የልጆቻቸውን ፍላጎትና ስሜት ደህና አድርገው ማወቅና ጥሩ ጠባያቸውንም መኮትኮት አለባቸው፡፡CLAmh 35.5

    ወላጆች፤ ልጆቻችሁ እንደምትወድዋቸውና ልታስደስቷቸውም እንደምጥሩ ግልጽ ይሁንላቸው፡፡ ይህ የሆነ እንደሆነ የሚከለከሉትን ነገር መተው አያዳግታቸውም፡፡ በማቴዎስ 18፡10 “መላዕክቶቻቸው በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ” የሚለውን በማስታወስ ልጆቻችሁን በፍቅርና በጥንቃቄ አስተዳድሩ፡፡ መላእክቶቻቸው እግዚአብሔር ያሰበላቸውን እንዲያከናውኑላቸው ምኞት ካላችሁ እናንተም በበኩላችሁ ኃላፊነታችሁን ፈጽሙ፡፡CLAmh 36.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents