Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የተፈጥሮ ሳይንስ ጥናት

    ስለእግዚአብሔርና ስለቃሉ የጠለቀ እውቀት ያለው ሰው ቅዱሳት መጽሐፍት መለኮታዊ መሆናቸውን በጥብቅ ያምናሉ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል እውነት መሆኑን ከመረዳቱም በላይ እውነት እርስ በእርሱ እንደማይነቃቀፍ ያውቃል፡፡CLAmh 186.3

    የመጽሐፍ ቅዱስን እውነተኛነት በሰው ሰራሽ ሳይንስ አማካይነት ለመፈተን አይሞክሩም፡፡ አስተሳሰቡን ወደ ማይሳሳተው መመሪያ ከፍ ለማድረግ ይሞክራሉ፡፡ እውነተኛ ሳይንስ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር እንደ ማይፈራረቅ ያውቃል፡፡ የሁለቱም ደራሲ አንድ አምላክ በመሆኑ በደንብ ላስተዋላቸው ሰው አንድነታቸው የማያከራክር ይሆናል፡፡CLAmh 186.4

    የሳይንስ ምርምር ተብሎ የሚጠራው ከቃለ እግዚአብሔር ጋር አልስማማ የሚል ሳይንስ በሰው ግምት ብቻ ሲመራ ነው፡፡CLAmh 186.5

    ሳይንስና ቃለ እግዚአብሔርን በአንድ ላይ የሚያጠና ተማሪ በሳይንስ ምርምር አማካይነት ብዙ መረጃና የጠለቀ አሳብ ያገኛል፡፡ የተፈጥሮ መጽሐፍና የተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል አንዱ ሌላው ያብራራል፡፡ ሁለቱም የእግዚአብሐርን ፍጥረትና የፍጥረት ህጉን ስለሚገልጡለት ከአምላክ ጋር በበለጠ ያስተዋውቁታል፡፡CLAmh 186.6

    የባለመዝሙሩን የህይወት ታሪክ ተፈጥሮንና የእግዚአብሔርን ቃል አጣምረው ያጠኑ ሰዎች ኑሮ ዋና ምሳሌ ነው፡፡ እንዲህ ይላል፡፡CLAmh 186.7

    “አቤቱ በሥራህ ደስ አሰኝተኸኛልና ፤ በእጅህም ደስ ይለኛልና፡፡ “(መዝሙር 92፡4) “አቤቱ ምህረትህ በሰማይ ነው፤ ጽድቅህም እንደ እግዚአብሔር ተራሮች፤ ፍርድህም እጅግ ጥልቅ ናት፡፡CLAmh 186.8

    አቤቱ ሰውንና! እንስሳትን ታድናለህ፡፡ አቤቱ ምህረትህን እንዴት አበዛህ! የሰው ልጆች በክንፎችህ ጥላ ይታመናሉ፡፡ (መዝሙር 36፡5-7) “በመንገዳቸው ንፁህ የሆኑ በእግዚአብሔርም ህግ የሚሄዱ ምስጉኖች ናቸው፡፡ ”CLAmh 187.1

    “ጎልማሳ መንገዱን በምን ያነፃል? ቃልህን በመጠበቅ ነው፡፡ የእውነትህን መንገድ መረጥሁ ፍርድህንም አልረሣም፡፡ (መዝሙር 119፡1፣ 2፣ 9፣ 30) ፡፡CLAmh 187.2

    “አንተን እንዳልበድል ቃልህን በልቤ ጠበቅሁ፡፡” (መዝሙር 119፡11) ፡፡CLAmh 187.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents