Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    23—የጸሎት ኃይል

    መጽሐፍ ቅዱስ “ሰዎች ሳይታክቱ ሁልጊዜ መጸለይ” እንዳለባቸው ይመክራል፡፡ (ሉቃስ 18፡11) ከመቼውም ይልቅ ጸሎት ማዘውተር የሚያስፈልጋቸው ሲደክሙና ለሕይወታቸው ሲያሰጋቸው ነው፡፡ ሙሉ ባለጤና የሆኑ ሰዎች በየዕለቱና በየዓመቱ የሚሰጣቸውን በረከት በመዘንጋት አምላክ ለዋለላቸው ውለታ ምስጋና ማቅረብን ይዘነጋሉ፡፡ በሽታ ሲይዛቸው ግን እግዚአብሔርን ያስታውሳሉ፡፡ ሰብአዊ ዓቅም ሲዳከም ሰዎች የአምላክ ርዳታ ትዝ ይላቸዋል፡፡ የሆነ ሆኖ ከልብ ለፈለጉት መሐሪው አምላካችን ፊቱን አያዞርም፡፡ ጤናማ ብንሆንም ብንታመምም መጠጊያችን ነው፡፡CLAmh 119.1

    በምድር ላይ የተመላለሰው ርኅሩኅ ሐኪም ክርስቶስ አሁንም ያው ነው፡፡ በእርሱ ዘንድ ለማንኛውም በሽታ የፈውስ ዘይት፣ ለድካም ሁሉ የብርታት ቅባት ይገኛል፡፡ ዘመናውያን ደቀመዛሙርት የጥንት ደቀመዛሙርቱ ለበሽተኞች ከልባቸው እንደጸለዩ መጸለይ አለባቸው፡፡ “የጻድቃን ጸሎት በሽተኞችን ስለምታድን” ፈውስ ይገኛል፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ኃይልና ጽኑ እምነት የእግዚአብሔር ተስፋ የእኛ መሆኑን ያረጋግጡልናል፡፡ “እጃቸውን በድውዮች ላይ ይጭናሉ፤ እነርሱም ይድናሉ” የሚለው የጌታ ተስፋ በሐዋርያት ዘመን የታመነ እንደነበር ዛሬም የታመነ ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ልጆች መብት በሙሉ ያረጋግጣል፡፡ በሃይማኖት መቀበል የእኛ ፋንታ ነው፡፡CLAmh 119.2

    የክርስቶስ አገልጋዮች የእርሱ አቀባይ ስለሆኑ በእነርሱ አማካይነት የፈዋሽነት ኃይሉን ሊያሳይ ይፈልጋል፡፡ የታመሙትንና የሚሰቃዩትን በሃይማኖት ክንዳችን አቅፈን ወደ አምላክ ማቅረብ ተግባራችን ነው፡፡ በታላቁ አዳኝ እንዲያምኑ ልናስተምራቸው ይገባል፡፡CLAmh 119.3

    በሽተኞችን፣ ተስፋ የቈረጡትንና የተጎሳቆሉትን ሁሉ በእርሱ እንዲመኩ እንድናደርግ መድኃኒታችን ኃላፊነት ጥሎብናል፡፡ በእምነትና በጸሎት የበሽተኛውን ክፍል “ቤቴል” ልናደርገው እንችላለን፡፡ ሐኪሞችና አስታማሚዎች በተግባራቸውና በንግግራቸው አምላክ ሊያጠፋ ሳይሆን ሊያድን በቦታው መገኘቱን በግልጽ ሊያስረዱ ይችላሉ፡፡ ክርስቶስ በቦታው መገኘቱን ለመግለጥ ስለሚፈልግ የሐኪሞችንና ያስታማሚዎቹን ልብ በፍቅሩ ይሞላል፡፡ ያስታማሚ ሕይወት ክርስቶስ በበሽተኛው አጠገብ እንዲገኝ የሚያስችል ከሆነ አዛኝ አዳኝ በቦታ መገኘቱን ያምናሉ፡፡ ይህ እምነት ራሱ ሥጋንና ነፍስን ሊፈውስ ይችላል፡፡CLAmh 119.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents