Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    12—ምርጥ ምግብ መመገብ

    ለሰው የተሰጠው የመጀመሪያው የምግብ ዓይነት ሥጋን አያጠቃልልም ነበር፡፡ ከጥፋት ውሃ በኋላ ግን አትክልትና ዕፀዋት ስለወደሙ ሥጋ ለምግብነት ተፈቀደ፡፡CLAmh 62.1

    በኤድን ገነት ለሰዎች ምግብን ሲያዘጋጅም ሆነ በምድረ በዳ ቤተ-እሥራኤልን ሲመራ አምላክ ፍሬፍሬንና አትክልትን እንዲበሉ መረጠላቸው፡፡ እሥራኤሎችን ከግብፅ ምድር አውጥቶ የራሱ ሕዝብ እንዲሆኑ አሠለጠናቸው፡፡ በእነርሱ አማካይነት ዓለምን ሁሉ መገናኘትና መባረክ ፈለገ፡፡ ይህንንም አሳቡን ከግብ ለማድረስ ያዘዘላቸው ምግብ መና እንጂ ሥጋ አልነበረም፡፡CLAmh 62.2

    ሥጋ የሰጣቸው ስላጉረመረሙና በግብጽ የነበረው በጉፈጅ ትዝ አለን ስላሉ ነበር፡፡ ሥጋውን የቀመሱ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች የሞትና የሕመም አደጋ ደረሰባቸው፡፡ ግን ሥጋ ብቻ መመገባቸው አላስደሰታቸውም ነበር፡፡ ማጉረምረማቸውን በድብቅና በግልጥ ቀጠሉ፡፡ ስለዚህ ሥጋ ብቻ መመገባቸው ዘላቂ አልሆነም፡፡CLAmh 62.3

    የእሥራኤል ልጆች ምድረ ከነዓንን ሲወርሱ ሥጋ እንዲበሉ ቢፈቅድላቸውም የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ ጥብቅ ቁጥጥር ነበረበት፡፡ እሪያ (አሳማን) የመሳሳሉትንና አንዳንድ ርኩስ ተብለው የሚቆጠሩ የእንስሳት፤ የአእዕዋፍና የዓሣዎች ሥጋ ክልክል ነበር፡፡CLAmh 62.4

    ከተፈቀደው የሥጋ ዓይነትም ሞራ (ስብና) ደም በፍጹም የተከለከለ ነው፡፡CLAmh 62.5

    ለእርድ የሚያገለግሉትም እንስሳት በተሟላ ጤና የሚገኙት ብቻ መሆን አለባቸው፡፡ በአውሬ የተገደለ፣ ሞተበፈቃዱ (የበከተ) እንስሳ በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ሥጋው እርም ነው፡፡CLAmh 62.6

    ጌታ ከፈቀደላቸው የአመጋገብ ሥነ ሥርዓት ስላፈነገጡ እሥራኤሎች ከጉዳት ላይ ወደቁ፡፡ የሥጋ ምግብ ስለአጓጓቸው ዋጋቸውን ተቀበሉ፡፡ የተጠበቀባቸውን ሳያሟሉ ቀሩ፤ እንደ እግዚአብሔር አሳብ መኖር አቃታቸው፡፡CLAmh 63.1

    “የለመኑትን ሰጣቸው፤ ለነፍሳቸው ግን ክሳት ላከባቸው” (መዝሙር 106፡15) ምድራዊውን ከሰማያዊው አብልጠው ተመለከቱ፤ ያቀደላቸውን ቅዱስ አሳብ መቀበል አቃታቸው፡፡ ሥጋ የሚበሉ ሰዎች አትክልትን በእጅ አዙር መመገባቸው ነው፡፡ ምክንያቱም እንስሳው አትክልት በመመገብ አካሉን ያዳብራል፡፡ በአትክልት የነበረው ሕይወት ወደ እንስሳት ይተላለፋል፡፡ ያን ሕይወት በእንስሳው አማካይነት ይቀበላሉ፡፡CLAmh 63.2

    ታድያ ጥቅሙን በተዘዋዋሪ ከመቀበል ይልቅ በቀጥታ ከአተትክልቱ ማግኘቱ እንዴት ይበጃል!CLAmh 63.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents