Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ኃይል ነው

    ደፋሮችና ተስፋ የማንቆርጥ እንሁን፡፡ ለእግዚአብሔር ሠርቻለሁና ይህን ማግኘት አለብኝ፤ ያን መቀበል አለብኝ ማለት ኃጢአትና ቂልነት ነው፡፡ ፍላጎታችንን በሙሉ ያውቃል፡፡ ሁሉን አዋቂ የሆነውና የነገስታት ንጉስ የሆነው አምላካችን እንደ ቸር እረኛ ለበጎቹ አዛኝ ነው፡፡ ኃይሉ ወሰን የለውም፤ ለሚያምኑበት ሁሉ ቃል ኪዳኑን ከመፈፀም ወደ ኋላ አይልም፡፡CLAmh 198.2

    ለችግራችን ሁሉ መፍትሔ አለው፡፡ የሚያገለግሉትንና በተስፋው የሚያምኑ ሁሉ ፤ ሁሉ ነገር አይጓደልባቸውም፡፡ የእርሱ ፍቅር ሰማይ ከመሬት የሚራራቀውን ያህል ከተራ ፍቅር በጣም የራቀ ነው፡፡CLAmh 198.3

    በዘለዓለማዊና በማይሰፈር ፍቅር ልጆቹን ይወዳቸዋል፡፡CLAmh 198.4

    ቀኑ ሲጨልም፤ ነገሩ ሁሉ የማያዋጣ ሲመስልህ በእግዚአብሔር እመን፡፡ ሁልጊዜ ለተከታዮቹ በጎ ያስብላቸዋል፡፡ የሚወዱትና የሚያገለግሉት ሰዎች ብርታት በየዕለቱ ይታደሣል፡፡CLAmh 198.5

    የሚያስፈልጋቸውን ርዳታ ለተከታዮቹ ለማደል ይፈቅዳል፤ ይችላልም፡፡ ሁሉን ፈትኖ ያየው ሐዋሪያው ጳውሎስ” እርሱም ፡— ፀጋዬ ይበቃሃል፤ ሀይሌ በድካም ይፈፀማልና አለኝ፡፡ “እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ፡፡ ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድከም በመንገላታትም፤ በችግርም ፤ በስደትም በጭንቀትም ደስ ይለኛል፡፡ ስደክም ምን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና” ይላል፡፡ (2ኛ ቆርንቶስ 12፡9-10) ፡፡CLAmh 198.6

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents