Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የሥጋ ምግብ ውጤት

    የሥጋ ምግብነት ውጤት በቶሎ ባለመታወቁ አይጎዳም ማለት አይቻልም፡፤ የበሉት ሥጋ ደማቸውን በክሎ የሥቃያቸው መነሻ መሆኑን ሲነግሯቸው ነገሩን አምነው የሚቀበሉት ብዙ አይደሉም፡፡ እውነተኛ ምክንያት ሳይታወቅ በሥጋ ምክንያት የሚሞቱ ብዙዎች ናቸው፡፡CLAmh 64.4

    የሥጋ ምግብ በአካል ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት በላይ መንፈሳዊ (የሞራል) ጠንቁም የዚያኑ ያህል ነው፡፡ ሥጋ መመገብ ለጤና ጠንቅ ስለሆነ አካልና አእምሮ ነፍስም ግንኙነት ስላላቸው ጉዳቱ የጋራ ነው፡፡CLAmh 64.5

    ሥጋ ለመብላት ሲባል በእንስሳት ላይ የሚፈጸመውን ጭካኔና በተመልካችም ዘንድ የሚያሳድረውን ስሜት መገመት አያዳግትም፡፤ እነዚህን የእግዚአብሔር ፍጥቶች በርኅራኄ መመልከት የሚገባንን ግዴታ በጣም ይቃወማል፡፡CLAmh 64.6

    በዚህ መሠረት ግሩም የሆነው የሰዎች የማሰብ ችሎታ ከእንስሳት የማሰብ ችሎታ ጋር ይቀራረባል፡፡ እንስሳት ይሰማሉ፣ ያፈቅራሉ፣ ይፈራሉ፣ ይሰቃያሉ፡፡ ብዙ ሰዎች የአካል ክፍሎቻቸውን በሥራ ላይ ከመያውሉት ይልቅ እንስሳት በታማኝነት ይጠቀሙባቸዋል፡፡ በሥቃይ ላይ ለሚገኙት መሰሎቻቸው ያዝኑላቸዋል፡፡ ብዙ እንስሳት ግንኙነት ካላቸው ጋር የሚያሳዩት ታማኝነት ሰዎች ከሚያሳዩት የላቀ ነው፡፡ ያለሥቃይ ሊለያቸው በማይችል ግንኙነት ከሰዎች ጋር ይተሣሠራሉ፡፡CLAmh 64.7

    ገር ልብ ካለው ያሳደጋቸውን እንስሳት፤ ይወዳቸው የነበረውንና ይተማመንባቸው የነበረውን ከብቶቹን ፈቅዶ ለቄራ የሚሸጥ ሰው ማን ነው? ሥጋቸውንስ እያጣጣመ የሚመገብ ምን ዓይነት ልቡ ደንዳና ቢሆን ነው?CLAmh 65.1

    የአካል ብርታት ሥጋን በመመገብ ይገኛል ማለት የተሳሳተ አስተሳሰብ ነው፡፡ ሥጋ ሳይበሉ የአካላት ክፍሎች የሚፈልጉትን ሊያገኙ ይችላሉ፡፡ የተፈለገው የአካል ብርታትም ይገኛል፡፡ አካል የጠራ ደም እንዲኖረው ለማድረግ ጥራጥሬ ቅጠላ ቅጠልና ፍራፍሬ በቂ ናቸው፡፡ የሰውነትን ፍላጎት ለሟሟላት ሥጋ በቂ አይደለም፡፤ የሥጋ ምግብነት ጠቃሚ ቢሆን ኖሮ ከመጀመሪያው የሰው ምግብ እንዲሆን በታዘዘ ነበር፡፤CLAmh 65.2

    ሥጋ መብላት ሲቋረጥ ብዙ ጊዜ ድካም ድካም ይላል፡፡ ብዙዎች ይህ የሚሆነው ሥጋ አስፈላጊ በመሆኑ ነው ይላሉ፡፡ ግን ሥጋ መብላት ነርቭንና ደምን ከሚገባው በላይ ስለሚያሠራ ሲቀር ሰውነት ክፍል ይደክማል፡፡ አንዳንዶች የመጠጥ ሱስ ያለበት ከጠርሙስ መላቀቅ ሞት እንደሚመስለው ሥጋ መብላት መተው የሚያስቸግራቸው አሉ፡፡ ግን ቢተዉት የበለጠ ይጠቀማሉ፡፡CLAmh 65.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents