Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ከየሱስ ጋር በተራራው ላይ

    ደቀ ደመዛሙርቱም ወደ ተግባራቸው ከመላካቸው በፊት ጠራቸው፡፡ የጴንጤቆስጤ ኃይልና ክብር ከመገለጡ በፊት ደቀመዛሙርቱ ከጌታ ጋር የጌታን ራት አብረው ተሳተፉ፤ በገሊላ ተራራ ተገናኙት፤ በደብረዘይት ተገኝተው ሸኙት፤ መላዕክት ተስፋ ሰጡአቸው፤ በአንድ ቤት ተሰብስበው በመፀለይ ለብዙ ቀናት ቆዩ፡፡CLAmh 209.4

    የሱስ ከፍ ያለ ፈተና ሲመጣበት ወይም ከፍተኛ ሥራ ሲያጋጥመው ብቻውን ወደ ተራራ በመሄድ ከአብ ጋራ በፀሎት ይገናኝ ነበር፡፡CLAmh 209.5

    ሐዋሪያት ሊመረቁ ሲሉ፤ በተራራ ላይ የሆነውን ስብከት የሱስ ሊያስተምር ሲል፤ በተራራው ላይ ሙሴና ኤልያስን ሊገናኝ ሲል፤ ከፍርዱና ከመሰቀሉ በፊት ከትንሳኤ በፊት ሲፀልይ ታድሯል፡፡CLAmh 209.6

    እኛም መንፈሳዊያን በረከት ለመቀበል ለፀሎት የተለየ ጊዜ መወሰን አለብን፡፡ የፀሎት ጠቃሚነትና ተፈላጊነት የሚገባንን ያህል አናውቅም፡፡ በምድር ያለውን ማንኛውንም ኃይል ሊያከናውን የማይችለውን ሥራ ፀሎትና እምነት ሊፈጽም ይችላል፡፡ በየቀኑ አዲስ ፈተናና ችግር ስለሚያጋጥመን ላለፈው የኑሮ ልምዳችን መሪነት ለመተማመን አንችልም፡፡ ከእግዚአብሔር ዘንድ የማያቋርጥ ብርሃን ዘወትር መቀበል አለብን፡፡ ክርስቶስ ድምፁን ለሚሰሙት ሁልጊዜ መልዕክት ይልክላቸዋል፡፡ በጌቴሴማኒ ያን ሌሊት ኀዘን ሲወድቅባቸው ደቀ መዛሙርቱ የየሱስን ድምጽ አላዳመጡም ነበር፡፡ መላእክት በቦታው መገኘታቸውን አልተገነዘቡም ነበር፡፡ ስለዚህ ያን ጊዜ ሊያገኙት ይችሉ የነበረውን ኃይልና ክብር አጡ፡፡ ስለሰነፉና ስላንቀላፉ ለጭንቀት ጊዜ ሊያገለግለቸው ይችል የነበር ኃይል ቀረባቸው፡፡ ከአምላክ ጋር ግኑኝነት ስለሌላቸው መለኮታዊ ርዳታ በጥብቅ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ባዶ እጃቸውን ይቀራሉ፡፡CLAmh 209.7

    በየቀኑ ፈተና ስለሚገጥመን የፀሎት ኃይል ያስፈልገናል፡፡ በየመንገዱ አደጋ ያጋጥመናል፡፡ ሌሎችን ከጥፋት ከክፋት ለማዳን የሚሞክሩ በተለይ ፈተና ይበዛባቸዋል፡፡ ክፉን ሲጋፈጡ ኃይል እንዲኖራቸው በፀሎት ካልበረቱ ለራሳቸውም ያሰጋቸዋል፡፡ ሰዎች ከላይ ወደታች ለመውረድ ብዙ ጊዜ አይወስድባቸውም፡፡ ከክብር ወደ ውርደት የሚያመራው መንገድ አጭርና አቋራጭ ነው፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥ አንድን ሰው ሁኔታ ለዘለዓለም የሚወሰን ምርጫ ማድረግ ይችላል፡፡ አንድ ያልተስተካከለ ጉድለት ሰውየውን ከጉዳት ላይ ሊጥለው ይችላል፡፡ አንድ መጥፎ ልምድ በቶሎ ካልታረመ ሰውየውን እንደ ሰንሰለት ሊያስረው ይችላል፡፡CLAmh 210.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents