Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    25—በሽተኞችንና ችግረኞችን ማገልገል

    በቅፍርናሆም በሚገኘው የጴጥሮስ ቤት ውስጥ የጴጥሮስ አማት ወባ ክፉኛ አሟት ነበር፡፡ ይህንም ለየሱስ ነገሩት፡፡ “የሱስም እጅዋን ነካት ወባውም ለቀቃት፡፡” ተነስታም የሱስንና ደቀመዛሙርቱን አስተናገደች፡፡ ሉቃስ 4፡38 ማርቆስ 1፡30፤ ማቴዎስ 8፡15CLAmh 130.3

    የምሥራቹ በየቦታው ተዳረሰ፡፡ ታምሩ የተፈጸመ በሰንበት ቀን ስለ ነበር ሕዝቡ ፈሪሳውያንን በመፍራት ፀሐይ ሳትጠልቅ በፊት ሊታከሙ አልመጡም ነበር፡፡ ከየቤታቸው፣ ከገበያ ሥፍና ከየሱቁ የሚጎርፈው ሕዝብ የሱስ የነበረበትን ጎጆ አጣበባት፡፡ በሽተኞች በቃሬዛ ሆነው፤ በምርኩዝ ተደግፈውና ሰው ደግፎአቸው ይመጡ ነበር፡፡CLAmh 130.4

    ለብዙ ሰዓታት የታከመው ሲመለስ ሌላው ይመጣ ነበር፡፡ ምክንያቱም ፈዋሹ ነገም መገኘት አለመገኘቱን የሚያውቅ ማንም አልነበረም፡፡ በቅፍርናሆም እንደዚያ ያለ ታሪክ ከዚያ በፊት ተፈጽሞ አያውቅም ነበር፡፡ አየሩ በደስታና በድል አድራጊነት ድምፅ ተሞላ፡፡CLAmh 131.1

    በሽተኛው ሁሉ እስኪድን ድረስ የሱስ ሥራው ቀጠለ፡፡ ሕዝቡ ከቦታው የሄደውና በሲሞን ቤት አካባቢ ጸጥታ የሰፈነው ከእኩለ ሌሊት በኋላ ነው፡፡ ሥራ የበዛበት ቀን ካለፈ በኋላ የሱስ ዕረፍት አሰኘው፡፡ ግን ገና የከተማው ሰው እንደተኛ “ጧት ጎህ ሳይቀድ ተነስቶ የሱስ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ፡፡” ማርቆስ 1፡35CLAmh 131.2

    ጧት ሲነጋጋ ጴጥሮስና ጓደኞቹ የቅፍርናሆም ሰዎች ይፈልጉሃል እያሉ ወደ የሱስ መጡ፡፡ “ስለዚህ ተልኬያለሁና ለሌሎች ከተሞች ደግሞ የእግዚአብሔርን መንግስት ወንጌል እሰብክ ዘንድ ይገባኛል” አላቸው፡፡ ሉቃስ 4፡43CLAmh 131.3

    በቅፍርናሆም መንደር በታየው ግርግር ምክንያት የየሱስ አመጣጥ ዓላማ ትርጉም ሊያጣ ይችል ነበር፡፡ የሱስ ታምራት በማድረጉና ሥጋዊ ደዌን በመፈወሱ ሰዎችን ወደ እርሱ የማቅረብ ፍላጎት አልነበረውም፡፡ ሰዎች ወደ እርሱ እዲቀርቡ የሚፈልግ መድኅን መሆኑን ሲያምኑ ብቻ ነው፡፡ ሰዎች ምድራዊ መንግስት ሊመሠርት የመጣ ንጉሥ ነው ብለው ሊያምኑ ሲሞክሩ እስተሳሰባቸውን ከምድራዊ ነገር ወደ ሰማያዊ ይመልሰው ነበር፡፡ የምድራዊ ክንውንነት ለሥራው እንቅፋት ይሆን ነበር፡፡CLAmh 131.4

    ግዴለሽ የሆነው ሕዝብ ሁኔታ አስደነቀው፡፡ በኑሮው ራስን የማሞካሸት ስሜት አልነበረበትም፡፡ በሰው ልጅ ዘንድ በማዕረግ፣ ወይም በችሎታ አሳብቦ ሰውን ማክበር ቦታ አልነበረውም፡፡ ሰዎች ዝናንና ስም ለማትረፍ የሚጠቀሙባቸው ዘዴዎች ሁሉ በእርሱ ዘንድ ቦታ አልነበራቸውም፡፡ ከመወለዱ በፊት ብዙ መቶ ዓመታት ቀደም ብሎ እንዲህ ዓይነት ትንቢት ተነግሮለት ነበር፡፡CLAmh 131.5

    “አይጮህም ቃሉንም አያነሣም፤ ድምፁንም በሜዳ አያሰማም፤ የተቀጠቀጠን ሸንበቆ አይሰብርም፡፡ የሚጤስን ክር አያጠፋም፤ በዕውነት ፍርድን ያወጣል፡፡” ኢሳይያስ 42፡2፣3CLAmh 131.6

    ፈሪሣውያን በታይታ ሃይማኖታቸው፤ በአደባባይ ጸሎታቸው፤ በብዙ ምፅዋታቸው የተለዩ ሆነው ለመከበር ይፈልጉ ነበር፡፡ በውይይትና በክርክር አማካይነት መንፈሳዊነታቸውን ለማሳወቅ ፈለጉ፡፡CLAmh 132.1

    የልዩ ልዩ ሃይማኖት አባሎች በሰፊው ይጨቃጨቁ ነበር፡፡ የተማሩ የሕግ ሊቃውንትን በየጐዳናው ሲከራከሩ መስማት የተለመደ ነበር፡፡CLAmh 132.2

    የየሱስ ሕይወት ግን የእነርሱ ተቃራኒ ነበር፡፡ በየሱስ ዘንድ የታይታ ሃይማኖት፤ ዝናና ድጋፍ ለማግኘት መጣር ሲያልፍም አይነካው፡፡ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ተሸፍኖ ነበር፡፡ አብ በወልድ ባሕርይ ተገለጠ፡፡ የሱስ ሰዎች ሁሉ ይህን እንዲያስተውሉ ፈለገ፡፡CLAmh 132.3

    የጽድቅ ፀሐይ የሰዎችን ይዞታ ለማጥፋት በዓለም ላይ ደማቅ ሆኖ አልወጣም ነበር፡፡ ስለ የሱስ “እንደ ወገግታም ተዘጋጅቶ እናገኘዋለን” ተብሏል፡፡ (ሆሴዕ 6፤3) ፡፡ ጎህ የሚቀድ በጸጥታና በእርጋታ ነው፡፡ ጨለማን በመግፈፍ ዓለምን ሁሉ ይቀሰቅሳል፡፡ የጽድቅ ፀሐይም “ፈውስ በክንፎቹ” ይዞ ይወጣል፡፡ (ሚልክያስ 4፡2) ፡፡CLAmh 132.4

    “እነሆ ደግፌ የያዝሁት ባሪያዬ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ምርጤ በርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ፤ እርሱም ለአሕዛብ ፍርድ ያወጣል፡፡” (ኢሳይያስ 42፡1)CLAmh 132.5

    “የጨካኞችም ቁጣ እስትንፋስ ቅጥርን እደሚመታ ዐውሎ ነፋስ በሆነ ጊዜ መጠጊያ፤ ከውሽንፍር መሸሸጊያ፤ ከሙቀትም ጥላ ሆነሃል፡፡” (ኢሳይያስ 25፡4) ፡፡CLAmh 132.6

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents