Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የሙሴ ትምህርት

    ሙሴ በግብጽ የተማረው ትምህርት በብዙ መንገድ ረድቶታል፡፡ ግን አድሜውን ሁሉ በበለጠ የጠቀመውን ትምህርት የገበየው በምድረበዳ በግ እረኛ ሆኖ ነው፡፡ ሙሴ በተፈጥሮ ችኩል ሰው ነበር፡፡ በግብጽ የታውቀ የጦር መሪ ስለነበርና ንጉሥና ህዝቡ ይወደው ስለነበረ ኩራትና ትምክህት ይሰማው ነበር፡፡ የህዝቡን ስሜት ስቦት ነበር፡፡ እስራኤልን በገዛ ኃይሉ ነፃ ለማውጣት አሰበ፡፡ የእግዚአብሔር ወኪል ለመሆን ግን የተለየ ትመህርት መማር ነበረበት፡፡ በጎቹን ወደ ተራራውና ወደ ለምልሙ መስክ ሲያሠመራ ሃይማኖትንና ቸርነትን ፤ ትዕግስትንና ትህትናን ለራሴ ብቻ አለማለትን ተማረ፡፡CLAmh 193.2

    ለደካሞቹ መጠንቀቅ፤ የታመሙትን ማስታመም፤ የጠፉትን መፈለግ፤ የደከሙትን መሸከም፤ ያረጁትንና የጎፈዩትን ማዘገም ተማረ፡፡CLAmh 193.3

    በዚህ ስራው ሙሴ ወደ ጠባቂዎች አለቃ ቀረበ፡፡ ከአስራኤል ቅዱስ ጋራ ተባበረ ከዚያ ወዲያ ትልቅ ነገር ለመፈጸም ማለሙን ተወ፡፡ አግዚአብሔር ያዘዘውን ብቻ በታማኝነት መፈጸም ፈለገ፡፡ በአከባቢው የእግዚአብሔርን መኖር ተገነዘበ፡፡ ተፈጥሮ በሙሉ ስለማይከሰተው አምላክ ያናግሩት ነበር፡፡ እግዚአብሔር ተጨባጭነት ያለው ሆኖ ተሰማው ፤ በጸሎት አማካይነት የአምላክ እውነተኛነት በበለጠ ታወቀው፡፡ በዘላለማዊ አምላክ ክንዶች ዘንድ መጠጊያ አገኘ፡፡CLAmh 193.4

    ይህን የሕይወት ለውጥ ካገኘ በኃላ የበጎች መጠበቂያ ከዘራውን ወደ በትረ መንግሥትነት እንዲለውጣት ከሰማይ ትዕዛዝ መጣለት፡፡ የበግ መንጋውን ትቶ የእስራኤል መሪ እንዲሆን ከአምላክ ዘንድ ተሾመ፡፡ መለኮታዊ መመሪያ ሲቀበል በራሱ የማይመካ፤ ድዳና አይነ አፋር ሆኖ ተገኘ ። የእግዚአብሔር አፈ-ጉባኤ ለመሆን በቂ አለመሆኑ ተስማው። ግን ሙሉ እምነቱን በአምላክ ላይ በመጣል የታዘዘውን ስራ ለመፈጸም ቆርጦ ተነሳ።CLAmh 193.5

    የሃላፊነቱ ከባድነት በጥብቅ እንዲያስብ አድረገው። ስለታዘዘ እግዚአብሔር ባረከውና ግሩም ተናጋሪ፤ ባለተስፋ፤ ታጋሽና ለሌላ ሰው ተሰጥቶ ለማያውቀው ስራ ገጣሚ ሆነ። ስለ እርሱ” እግዚአብሔርን ፊት ለፊት እንዳውቀው እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ ከዚያ ወዲህ በእስራኤል ዘንድ አልተነሳም” ተብሎልታል። (ዘዳግም 34፡10)CLAmh 194.1

    የሚሰሩት ስራ ያልተመስገነ የሚመስላቸውና ለከፍተኛ ኃላፊነት ጉጉት ያላቸው ሁሉ” ክብር ከምስራቅ ወይም ከምዕራብ ወይም ከምድር በዳ የለምና፤ እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና ይህን ያዋርዳል ይህንም ያከብራል።” የሚለውን አነጋገር አስተውል። (መዝሙር 75፡6-7)CLAmh 194.2

    ሰው ሁሉ በዘላዓለማዊ የሰማይ ዕቅድ ውሰጥ ድርሻ አለው። ያን ድርሻቸውን በሚገባ የማከናወናችን ጉዳይ ከእግዚአብሔር ጋር ለመተባመር በምናሳየው ታማኝነታችን ይወሰናል ።CLAmh 194.3

    ራሳችንን ከማሞካሸት መጠንቀቅ አለብን። የሚገባኝን ክብር አላገኘሁም በማለት አትባክኑ። በሥራዬ አልተመሰገንሁም፣ ስራዬ በጣም ከባድ ነው አትበሉ።CLAmh 194.4

    ክርስቶስ ለእኛ ሲል የተቀበለውን ስቃይ በማስታወስ ማጉረምረማችንን እንተው ከጌታችን የበለጠ አቀባበል ተደርጎልናል፡፡ “ለራስህ ታላቅ ነገር ትፈልጋለህን “(ኤርሚያስ 45፡5) ፡፡ መስቀሉን ከመሸከም ይልቅ አክሊል ለመድፋት የበለጠ ጉጉት ያላቸው ሰዎች በእግዚአብሔር ሥራ ተካፋይነት የላቸውም፡፡ እግዚአብሔር ሽልማት ከመቀበል ይልቅ ግዴታቸውን ለሟሟላት የሚተጉትን ሰዎች ይፈልጋል፡፡ ከክብር ይልቅ ጽናትን የሚወዱትን ሰዎች አምላክ ይፈልጋቸዋል፡፡CLAmh 194.5

    ትሁታንና ሥራቸውን አምላክ በሚወደው መንገድ የሚሠሩ ሰዎች ራሳቸውን ከፍ ከፍ እንደሚያደርጉት ልታይ አይሉም፡፡ ግን በሥራ ውጤት በኩል ከሆነ የትሁታኑ ይበልጣል፡፡CLAmh 194.6

    ራሳቸውን የሚያመጻዱቁ ሰዎች በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል በመደቀን ሥራቸው ዋጋ ቢስ ይሆናል፡፡CLAmh 194.7

    “ጥበብ ዓይነተኛ ነገር ናትና ጥበብን አግኝ ከሀብትህም ሁሉ ማስተዋልን አትርፍ ፡ ከፍ ከፍ አድርጋት እርሷም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፡፡ ብታቅፋትም ታከብርሃለች፡፡” (ምሣሌ 4፡7-8)CLAmh 194.8

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents