Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በተሻለ ዕቅድ ሕይወትህን ምራ

    ባለ ትዳር ሁሉ በተሻለ እቅድ ለመመራት ይሞክር፡፡ የመጀመሪያው ዓላማህ የሚያስደስት ትዳር ለማቋቋም ይሁን፡፡ ሥራን የሚያቃልሉ፣ ጤንነትንና ምቾትን የሚያሻሽሉ መሣሪያዎች ይኑሩህ፡፡ “ከነዚህ ወንድሞቹ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት” (ማቴ 25፡40) በማለት ክርስቶስ እንድናስተናግዳቸው ያዘዘንን እንግዶች ለመቀበል ወስን፡፡ በቤትህ ውስጥ የሚገኙት ዕቃዎች በጣም ውድ ያልሆኑ፣ በቀላሉ የማይበላሹ፣ ንጹሕና ሲበላሹ ወይም ሲያረጁ ለመተካት ብዙ ገንዘብ ወጭ የማያስደርጉ መሆን አለባቸው፡፡ ፍቅርና በቃኝ ማለት ካለ ውድ ባልሆኑ ነገሮች ቤትን ለማስጌጥ ይቻላል፡፡CLAmh 20.4

    እግዚአብሔር ውብ የሆነውን ነገር ይወዳል፡፡ ሰማይንና ምድርን በሚያምሩ ነገሮች አጐናጽፏል፤ ልጆቹ በሠሯቸው ነገሮች ሲደሰቱ ሲያይ ያባትነት ደስታ ይሰማዋል፡፡ የቤቶቻችንን ዙሪያ በሥነ ፍጥረት ውበት እንድናስጌጥ ይመኛል፡፡CLAmh 21.1

    በገጠር የሚኖሩ ሁሌ ምንም ዓይነት ቢሆኑም በቤቶቻቸው ዙሪያ ትንሽ የሣር ሜዳ ጥቂት የጥላ ዛፎች፤ ቁጥቋጦችና አበባዎች ሊኖራቸው ይችላሉ፡፡ እንደዚህ ያሉት ነገሮች ከማንኛውም ሰው ሠራሽ ውበት የበለጠ ደስታ ይሰጣሉ፡፡ የቤተሰቡን ሕይወት ያድሳሉ፤ ከሥነ ፍጥረት ጋር ያዋድዳሉ፤ የቤተሰቡንም አባሎች እንዲፋቀሩና ወደ እግዚአብሔርም እንደዲቀርቡ ያደርጋሉ፡፡CLAmh 21.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents