Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ሃይማኖትና ትዳር

    ያለ ስጋት የጋብቻ አንድነት ሊቋቋም የሚችለው በክርስቶስ አማካይነት የተመሠረተ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ ሰብአዊ ፍቅር ጥንካሬውን ሊያገኝ የሚገባው ከመለኮታዊ ፍቅር ነው፡፡ ጥልቅ እውነተኛና ራስን ያለመውድደ ፍቅር ሊገኝ የሚችለው ክርስቶስ በነገሰበት ቦታ ብቻ ነው፡፡CLAmh 14.1

    ፍቅር ከክርስቶስ የምናገኘው የተከበረ ስጦታ ነው፡፡ ፍጹምና ቅዱስ የሆነ ፍቅር የሕይወት ደንብ እንጂ ስሜት አይደለም፡፡ እውነተኛ ፍቅር የያዛቸው ሰዎች የማያመዛዝኑ ወይም ዕውር አይደሉም፡፡ መንፈስ ቅዱስ ስለሚያስተምራቸው ከሁሉ አብልጠው እግዚአብሔርን፣ ጎረቤቶቻቸውንም እንደራሳቸው ያፈቅራሉ፡፡CLAmh 14.2

    ለማግባት የሚያስቡ ሁሉ እስከ ሕይወት ፍጻሜአቸው ድረስ የሚቆራኟቸውን ሰዎች የፍቅር ስሜትና እያንዳንዱን የጠባይ ዕድገት መመዘን አለባቸው፡፡ የጋብቻን አንድነት ለመመሥረት የሚወሰድ እርምጃ ሁሉ በእውነተኛነት፤ በታማኝነትና ባለማስመሰል፣ አንደዚሁም እግዚአብሔርን ለማስደሰትና ለማክበር በማሰብ ሊወሰድ ይገባዋል፡፡ ጋብቻ የአሁኑንም ሆነ የኋለኛውን ሕይወት የሚነካ ነገር ነው፡፡ እውነተኛ ክርስቲያን እግዚአብሔር የማይፈቅደውን እቅድ አያዘጋጅም፡፡CLAmh 14.3

    እግዚአብሔርን የሚፈሩ ወላጆች እንዳሉህ ከነርሱ ጋር ተመካከር፡፡ ተስፋህንና እቅድህን ሁሉ ግለጽላቸው፤ በሕይወት ልምምድ ካገኙት ትምህርት ተማር፤ ይህን ብታደርግ ከብዙ ችግር ትድናለህ፡፡ ከሁሉ የበለጠ ግን ክርስቶስን አማካሪህ አድርገው፡፡ ቃሉንም በጸሎት አጥናው፡፡CLAmh 14.4

    በእንደዚህ ያለ መሪነት አንዲት ልጃገረድ ልታገባው የሚገባት ወጣት ንጹሕ ጠባይ ያለው፣ ትጉህ እውነተኛ፣ እግዚአብሄርን የሚያፈቅርና የሚፈራ መሆን አለበት፡፡ አንድ ወጣት ሊያገባት የሚገባ ልጃገረድ የሕይወትን ቀንበር አብራ ለመሸከም የምትችል ጓደኝነትዋ የሚያነቃቃውና የሚያሻሽለው እንደዚሁም በፍቅርዋ የምታስደስተው መሆን አለበት፡፡CLAmh 14.5

    “አስተዋይ ሚስት ግን ከእግዚአብሄር ዘንድ ናት፡፡” “የባልዋ ልብ ይታመንባታል፡፡ ዕድሜዋን ሙሉ መልካም ታደርግለታለች፤ ክፉም አታደርግም፡፡” “አፍዋን በጥበብ ትከፍታለች፤ የርኅራኄም ሕግ በምላስዋ አለ፡፡ የቤትዋን ሰዎች አካሄድ በደህና ትመለከታለች፤ የሐኬትንም እንጀራ አትበላም፤ ባልዋ ደግሞ እንዲህ ብሎ ያመሰግናታል፤ መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡” “ሚስትን ያገኘ በረከትን አገኘ” ምሳሌ 19፡14፣ 31፣11፣12፣26-29፤ 18፡22CLAmh 15.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents