Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    8—ትምህርት ከቤተሰብ ይጀምራል

    ልጆቻችን በመንታ መንገድ ላይ እንደቆሙ ሊታሰብ ይችላል፡፡ ራስን የመውደድና ራስን ያለመግታት ዓለማዊ ፈተናዎች እግዚአብሔር ለዳኑት የዘረጋውን መንገድ እንዲለቁ ያታልሏቸዋል፡፡ ሕይወታቸው ለበረከት ወይም ለመርገም መሆኑ የሚወሰነው በሚያደርጉት ምርጫ ነው፡፡ ብዙ ኃይል ስላላቸውና ችሎታቸውንም ለመሞከር ስለሚፈልጉ የጉልበታቸው መቀነሻ መንገድ ማግኘት አለባቸው፡፡ ንቃታቸው (ትጋታቸው) ለጥቅም ወይም ለጉዳት ሊሆን ይችላል፡፡CLAmh 37.1

    የእግዚአብሄር ቃል ትጋትን አይነቅፍም፤ ይልቁንስ በትክክል ይመራዋል፡፡ እግዚአብሔር ወጣቶች ከፍ ያለ ነገር እንዳይመኙ አያዝዝም፡፡ ሰውን የተከበረና እውነተኛ ክንውን ያለው እንዲሆን የሚያደርጉት ጠባዮች (ጥሩ ነገር የማከናወን ጥብቅ ምኞት፤ የማይበገር አሳብ፤ በኃይል መሥራት፤ ተስፋ አለመቁረጥ) መደፋፈር አለባቸው፡፡ በእግዚአብሔር ጸጋ ራስን ከመውደድ ወደተሻሉ ነገሮች መመራት አለባቸው፡፡CLAmh 37.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents